Contract
የመተግበሪያ ስምምነት ቅጽ
ይህ የመተግበሪያ ስምምነት ቅጽ ታትሞ፣ ተፈርሞ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤትዎ ላለ የኤሲኢኤስ አካዳሚክ አሰልጣኝ መሰጠት ያለበት ጃኑዋሪ 13 ቀን 2023 ሳያልፍ ነው።
ፈቃዴን የምሰጠው ለኤሲፒኤስ ፕሮግራም አጋሮች በኔ ወይም በልጄ የትምህርታዊ መረጃ ከኤሲፒኤስ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ፣ የአይኢፒ/504 እቅድ መረጃ፣ ትራንስክሪፕቶች፣ ገንዘብ ነክ እርዳታ መረጃዎች እና ሌሎች የአካዳሚክ መረጃዎችን ጨምሮ ያሉትን መረጃዎች እንዳስፈላጊነታቸው እንዲያጋራ እና እንዲገልጽ ነው።
የግንኙነት ፈቃድ፥ የተለያዩ የመገናኛ መንገዶቻችን የሚጨምሩት፣ ነገር ግን በነሱ የማይወሰኑት፣ ዩኤስ ሜይል፣ ኢሜይል፣ የስልክ ጥሪዎች፣ የጽሁፍ መልእክቶች፣ የቪዲዮ ኮንፈረንስ (ለምሳሌ ዙም) እና የማህበራዊ መገናኛ ሚዲያዎችን ነው። ፈቃድዎን በአክብሮት የምንጠይቀው እነዚህን የተለያዩ መንገዶች በተቻለ መጠን ተጠቅመን ከወላጅ ጠባቂ እና ተማሪ ጋር ለመገናኘት ሲሆን፣ እኚህም ተማሪዎቻችን ለኮሌጅ እና ለኑሮ ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ተማሪዎቻችንን ለመመልመል እና ፕሮግራም ለማሰናዳት ወሳኝ ናቸው። ይህንን ቅጽ በመፈረም፣ ለኤሲኢኤስ ፕሮግራም የሚያቀርቡት ፈቃድ እነዚህን የተለያዩ የመገናኛ መንገዶች በመጠቀም ወላጆችንን፣ ጠባቂዎችን እና ተማሪዎችን ከኤሲኢኤስ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ ለማግኘት ነው።
ወደ ኤሲኢኤስ ፕሮግራም ቅበላ ካገኘሁ በሁዋላ፣ ለልጄ የምፈቅደው የሞንትጎመሪ ኮሌጅ (ኤምሲ)ማመልከቻን እንዲሞላ እና ለኤምሲ መረጃዎች ተደራሽ እንዲሆን ይህም ለኤሲኢኤስ ፕሮግራም ብቁ ሆኖ እንዲቆይ ነው። ሞንትጎመሪ ኮሌጅ መረጃዎች በኤሲኢኤስ ፕሮግራም በሙሉ ለመሳተፍ ይጠየቃሉ። ተማሪዎች ከፕሮግራሙ ሊወገዱ የሚችሉት የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ማመልከቻዎችን ከኤሲኢኤስ አሰልጣኛቸው ጋር ካልሞሉ ነው። ሁሉም የኤሲኢኤስ ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ኮሌጅ (ኤምሲ)ማመልከቻን መሙላት ሲጠበቅባቸው ነገር ግን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተመረቁ በሁዋላ ኤምሲ ለመግባት አይገደዱም።
የኤሲኢኤስ ፕሮግራም ሁሉንም ማመልከቻዎች በተናጠል የማየት እና ተጨማሪ የግል እና ትምህርታዊ ሁኔታዎችን በማካተት የመጨረሻውን የመግቢያ ውሳኔ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው። የኤሲኢኤስ ፕሮግራም ለሌላ አካል ግለሰብን የሚገልጽ መረጃ አያካፍልም፤ ወይም ያለተማሪው ወላጅ የቀደመ ፈቃድ ለሌላ አላማ አያጋራም።
ይህ የመተግበሪያ ስምምነት ቅጽ የኤሲኢኤስ ፕሮግራም ማመልከቻ አካል ሲሆን ነገር ግን የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ወይም በዩኒቨርሲቲስ ኦፍ ሼዲ ግሮቭ ባሉ ማንኛውም ፕሮግራሞች ማመልከቻ አይደለም።
የምገነዘበው ማመልከቻ መላክ ወደ ኤሲኢኤስ ፕሮግራም ተቀባይነት ማግኘትን አያረጋግጥም። ተማሪ ኤምሲፒኤስ መታወቂያ ቁጥር፥
ተማሪ ስም፥ ወላጅ ጠባቂ ስም፥
ተማሪ ፊርማ፥ ወላጅ ጠባቂ ፊርማ፥
ቀን፥ ቀን፥
ወላጆች/ጠባቂዎች፥ ስለ ኤሲኢኤስ ፕሮግራም ያሉትን ሁሉንም ግንኙነቶች እርስዎ እና ልጅዎ እንደሚቀበሉ ለማረጋገጥ እባከዎትን የሚከለተለውን መረጃ ያቅርቡ። የመኖሪያ አድራሻ፥
ከተማ፥ ስቴት፥ ዚፕ ኮድ፥
ወላጅ የእጅ ስልክ፥ ወላጅ ኢሜይል፥
በኢሲኢኤስ ፕሮግራም ለመሳተፍ ምንም ወጪ አይጠይቅም።