Contract
ዳኛ፡ ጅሬኛ ዴቲ
አመልካቾች፡- 1. አቶ ታምራት ሰቦቃ ዳባ -
2. ወ/ሮ ሰላማዊት አደፍርስ ሞላ - ተጠሪ፡- የለም -
መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ሲሆን ተመርምሮ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
ው ሳ ኔ
ለዚህ ውሳኔ መነሻ የሆነው አመልካቾች መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ ግራቀኙ ህዳር 08 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ባህል መሰረት ጋብቻ ፈፅመን ጋብቻውን በክብር መዝገብ አስመዝግበናል፡፡ አመልካቾች ጋብቻ ከፈፀምን በኋላ በትዳር ውስጥ በቆየንበት ጊዜ ውስጥ ህፃን ማርያማዊት ታምራት ሰቦቃ ዕድሜ 14፣ ህፃን አዶኒያስ ታምራት ሰቦቃ ዕድሜ 12 እና ህፃን ማርኮን ታምራት ሰቦቃ እድሜ 6 የሆናቸው ልጆችን ወልደናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ልዩ ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን አፍርተናል፡፡ ሆኖም አመልካቾች በትዳር ከቀጠልን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን አምነንበት መጋት
25 ቀን 2014 ዓ.ም የስምምነት ፍቺ ውል ያደረግን በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ያቀረብነውን የስምምነት ፍቺ እንዲያፀድቅልን በማለት ጠይቀዋል፡፡ ከአቤቱታቸው ጋር የሰውና የሰነድ ማስረጃ ዝርዝር አያይዘው አቅርበዋል፡፡
በአመልካቾች መካከል ህዳር 08 ቀን 1998 ዓ.ም የተፈጸመ ጋብቻ ስለመኖሩ አመልካቾች በሰነድ ማስረጃነት ያቀረቡትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የተሰጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ሰነድ ያስረዳል፡፡
ፍ/ቤቱ አመልካቾች መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ያደረጉትን የስምምነት ፍቺና የንብረት ክፍፍል ውል ስምምነት ሲመረምር አመልካቾች ፍቃዳቸውን የሰጡበት እንዲሁም ከህግና
ከሞራል የማይቃረን በመሆኑ እንዲሁም በትዳር መካከል ያፈሯቸውን ልጆች ጥቅም ባስከበረ መልኩ ያደረጉት መሆኑን ስለተረዳ ፍርድ ቤቱ አመልካቾች መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም የፈፀሙትን የፍቺና የንብረት ክፍፍል ስምምነት 02(ሁለት) ገፅ በተሻሻለው የኢ.ፌ.ድ.ሪ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 80(1) መሰረት አፅድቆ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ት ዕ ዛ ዝ
1. አመልካቾች መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ያደረጉት የፍቺ እና የንብረት ክፍፍል ስምምነት 2/ሁለት/ ገጽ የፍርድ ቤቱ ማህተም አርፎበት ከውሳኔው ጋር ለግራ ቀኙ ይሰጥ፡፡
2. መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡