አውሮፓውያን በ18ኛው ክፍለ ዘመን ኢንዱስትሪዎቻቸውን ባስፋፉ ማግስት ጥሬ ሀብት ለመቀራመት እና ለምርቶቻቸው ማራገፊያነት አይናቸውን የጣሉት አፍሪካ ላይ እንደነበር የታሪክ መዛግብት እና ምfhራን ያስረዳሉ። እናም የአውሮፓ አገራት በበርሊኑ ጉባዔያቸው አፍሪካን በቅኝ ግዛት የመያዝ ሴራቸውን ዶለቱ። ለዚህ ቅርምታቸው ፍኖት እንዲሆናቸውም የአፍሪካን ካርታ ከፊታቸው ዘርግተው አገራትን እንደ ቅርጫ...