ዲጂታል ድሪመርስ የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያ የተጠቃሚ ስምምነት SY2023 - 2024
AMHARIC
ዲጂታል ድሪመርስ የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያ የተጠቃሚ ስምምነት SY2023 - 2024
የ DeKalb ካውንቲ ት/ቤት ዲስትሪክት በቅድመ መዋዕለ ህጻናት 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የበይነመረብ ግንኙነት መሳሪያ ለቤተሰብ ይመድባል (SY 2023 – 2024)። የበይነመረብ ግንኙነት መሳሪያዎች የ DCSD (የDeKalb ካውንቲ ትምህርት ዲስትሪክት) ንብረት ሆነው ይቆያሉ እና ከድስትሪክቱ እና/ወይም ከዓመቱ የመሰብሰቢያ ሂደት ሲወጡ መመለስ አለባቸው።
መሳሪያው የሚሰጣቸው ተማሪዎች በዚህ ሰነድ ውስጥ የሚገኘውን መመሪያ እንዲሁም ባህሪይ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ የወጡ የት/ቤት፣ መማሪያ ክፍል እና የት/ቤት አውራጃ ፖሊሲ እና አሰራር መከተል አለባቸው፡፡
ማነጋገር የሚችሉት ሰው: ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች አሉዎት እባክዎን የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ያነጋግሩ።
የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያ የተጠቃሚ ስምምነት
መሳሪያውን መቀበል
መሳሪያው ከመሰጠቱ በፊት ወላጆች እና ተማሪዎች ይህን ስምምነት ፈርመው መመለስ አለባቸው፡፡ መሳሪያውን መመለስ
በትምህርት አመቱ መጨረሻ ላይ መሳሪያው ለት/ቤቱ ይመለሳል፡፡ በ DCSD ት/ቤቶች የሚሰጠው መሳሪያ ጥቅም ለሌላ ሰው አይተላለፍም እንዲሁም ተማሪው መሳሪያውን በሰጠው ት/ቤት መማር ሲያቆም ያበቃል፡፡
በማንኛውም ምክንያት ከት/ቤቱ የተዛወረ፣ ያቋረጠ፣ የተባረረ ወይም የወጣ ተማሪ ባቋረጠበት/በወጣበት ቀን መሳሪያውን መመለስ አለበት፡፡
መሣሪያውን መመለስ ያልቻለ ተማሪ ማንኛውንም መለዋወጫዎች የመሳሪያውን ሙሉ የመተካት ወጪ ለመክፈል ይገደዳል፣ እንዲሁም የክፍል ካርዶች፣ ግልባጮች፣ ዲፕሎማዎች ወይም የዕድገት ሰርተፍኬቶች እድሳት እስኪደረግ ድረስ ታግዶ ይቆያል።
ብልሽት እና መጥፋት
መሳሪያ ለተማሪ በተሰጠበት ወቅት ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት ቢበላሽ፣ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ የተማሪው ወላጅ/አሳዳጊ በዚህ ሰነድ ላይ የተገለጸውን ቅጣት ይከፍላሉ፡፡
ቸልተኝነት
በተመሳሳይ የትምህርት ዓመት መሣሪያ ብዙ ጊዜ ጉዳት ከደረሰበት የአውራጃው አስተዳደር የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያውን ሙሉ መተካትን ጨምሮ የድርጊቱን ውሳኔ ይወስናል።
ሀላፊነት ያለበት የመሳሪያ ተጠቃሚ
ሁሉም በዲስትሪክት የተሰጡ መሳሪያዎች ተጠቃሚዎች በዲስትሪክት ፖሊሲ እና የአሰራር መመሪያዎች ውስጥ የተገለጹትን የሚጠበቁ ነገሮች መከተል አለባቸው IFBGA: ሀላፊነት የተሞላው የ Enterprise Network, JD አጠቃቀም: የተማሪ ስነ-ስርአት/የተማሪ ስነ- ምግባር ደንብ እና JS: የተማሪ ቅጣቶች እና ክፍያዎች። እነዚህን ደንቦች አለመከተል የስነስርአት ቅጣቶችን ያስከትላል፡፡ ሁሉም የዲስትሪክቱ ፖሊሲዎች በ xxx.xxxxxxxxxxxxxxx.xxxይገኛሉ፡፡
እነዚህ መሣሪያዎች በዲስትሪክቱ የተጣሩ የ CIPA ማሟያ ናቸው እና ለትምህርታዊ ዓላማዎች ብቻ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ተማሪ ከት/ቤት ቀጠና ውጪ በሚሆንበት ወቅት ስለመሳሪያው አጠቃቀም የቁጥጥር ሀላፊነት የሚወስደው ወላጅ ነው፡፡ ተማሪዎች መሳሪያውን በመጠቀም በማንኛውም ሰአት እና በየትኛውም ቦታ ተገቢ ያልሆነ ባህሪይ ማሳየት ወይም የተከለከሉ ነገሮችን ማግኘት አይችሉም ፡፡ ት/ቤት ውስጥ ወይም ውጪ ተማሪዎች መሳሪያውን ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ ለማድግ ከተጠቀሙበት የስነ-ምግባር ወይም የህግ ቅጣት ይከተላቸዋል፡፡
ሚስጥራዊነት
በዲስትሪክቱ የተሰጠ መሳሪያዎች የ DCSD ንብረት ሆነው ይቆያሉ። እንደዚሁም በመሣሪያው ላይ የሚደረግ ማንኛውም ነገር የግል አይደለም። ይህ ማለት የ DCSD ሰራተኞች በማንኛውም ቦታ በዲስትሪክቱ የተሰጠ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያን በመውሰድ አጠቃቀሙን ሊያዩ ይችላሉ፡፡
የ DeKalb ካውንቲ ትምህርት ቤት ዲስትሪክት ሁሉንም የህጻናት የኦንላይን የግላዊነት ጥበቃ ህግ (COPPA)፣ የህፃናት የኢንተርኔት ጥበቃ ህግ (CIPA) እና የቤተሰብ ትምህርት መብቶች እና ግላዊነት ህግ (FERPA) እውቅና ይሰጣል።
DeKalb County ት/ቤት አውራጃ የተማሪን የቤት ኔትወርክ፣ መሳሪያ ወይም የኢንተርኔት ግንኙነት አይቆጣጠርም፡፡ ዲስትሪክቱ በዲስትሪክቱ የተሰጠ መሳሪያ አጠቃቀም ይቆጣጠራል፡፡ በተጨማሪም በዲስትሪክቱ የተሰጠ መሳሪያ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ DCSD መገኛ ቦታ ይከታተላል፡፡
ወርሃዊ የመሳሪያዎች አጠቃቀም
የ DeKalb ካውንቲ ት / ቤት ዲስትሪክት መሳሪያዎችን በየወሩ ይከታተላል፡፡ ዲስትሪክቱ አነስተኛ አጠቃቀም ካስተዋለ ፣ ት / ቤቱ ምን ዓይነት እርዳታ መስጠት እንደሚችል ለማየት ትምህርት ቤቱ ወላጆችን ያነጋግራቸዋል፡፡ አጠቃቀሙ ዝቅተኛ ከሆነ ወይም ተቀባይነት ያለው የአጠቃቀም ስምምነት ከተጣሰ ቤተሰብ መሳሪያውን እንዲመልስ ዲስትሪክቱ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው።
መሳሪያው ቢበላሽ፣ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ የገንዘብ ቅጣት
ለተማሪው በተሰጠበት ጊዜ መሣሪያው እና/ወይም መገልገያዎቹ ከጠፉ ወይም ከተሰረቁ፣ ሆን ተብሎም ይሁን በቸልተኝነት ተማሪው እና ወላጅ/አሳዳጊ የሚከተሉትን ክፍያዎች የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው፡
የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያ መተካት
የጠፋ/የተሰረቀ/ከጥገናው በላይ የተጎዳ | • ሙሉ ምትክ ክፍያ (ከ $ 43.75 እስከ $240.00 የመሣሪያው መገኘት ላይ በመመስረት) |
የሚጠገን-ጉዳት | • ጉዳት የደረሰባቸው መሳሪያዎች በቤት ውስጥ ጥገና እንደሚሰሩ ለማወቅ በ DCSD ቡድን ይገመገማሉ። ከመጠገን በላይ ከተበላሸ ሙሉ ምትክ ክፍያ ያስፈልጋል። ከላይ ይመልከቱ፡፡ |
*የመሳሪያ ሙሉ መተኪያ ክፍያ የሚያካትተው መሳሪያውን፣ ሁሉንም ተያያዥነት ያላቸው እቃዎች፣ የሶፍትዌር ፈቃድ እና መጫኛን ነው፡፡
የስርቆት:
መሳሪያው ለተማሪው በተሰጠበት ወቅት ከተሰረቀ ተማሪው፣ ወላጅ/አሳዳጊ የሚከተሉት ሀላፊነቶች አሉባቸው፡
• የትምህርት ቤት አስተዳደርን ማሳወቅ
• የፖሊስ ዘገባ ማቅረብ
• ሙሉ ምትክ ክፍያ መክፈል
ከት/ቤቱ በሚዛወሩበት/በሚወጡበት ጊዜ መሳሪያን ወይም መለዋወጫዎችን መመለስ አለመቻል፡
መሳሪያን ወይም ማናቸውንም መለዋወጫዎችን ሳይመልስ የሚዘዋወር ወይም የሚለቅ ተማሪው የኢንተርኔት የግንኙነት መሣሪያ ሙሉ ምትክ ክፍያ የመክፈል ሃላፊነት አለበት።
የወላጅ ፈቃድ መስጫ እና ነጻ ማድጊያ
ከስር በመፈረም በዚህ ሰነድ ውስጥ የሚገኙትን መመሪያዎች ማንበብዎትን እና መረዳትዎን እንዲሁም ለተማሪዎች መሳሪያ መሰጠቱን መቀበልዎትን ያረጋግጣሉ፡፡ የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያ የ DCSD ንብረት እንደሆነ እና ከዲስትሪክቱ ሲለቁ እና / ወይም የዓመቱ መሰብሰብ ሂደት ሲጠናቀቁ መመለስ እንዳለበት ይገነዘባሉ። ተማሪው መሳሪያውን በሚይዝበት ወቅት መሳሪያው እና ተያያዥነት ያላቸው እቃዎች ላይ ለሚደርስ መበላሸት፣ መጥፋ ወይም መሰረቅ ሀላፊነት እንደሚወስድ ተረድተዋል እንዲሁም በዚህ ሰነድ ላይ የተገለጸውን የገንዘብ ቅጣት ለመክፈል ተስማምተዋል፡፡
ከትምህርት ቤት ውጭ በሚሆኑበት ጊዜ የተማሪውን የመሳሪያ አጠቃቀም ለመቆጣጠር ብቸኛው ሃላፊነት የእርስዎ እንደሆነ እና መሣሪያው ለትምህርታዊ ዓላማዎች ብቻ የሚያገለግል መሆኑን ተረድተው ተስማምተዋል። ተማሪዎች መሣሪያውን ተገቢ ላልሆኑ ወይም ለተከለከሉ ተግባራት ከተጠቀሙ የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተረድተዋል ፡፡
ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት መሳሪያውን በአግባቡ ባለመጠቀም፣ በመጉዳት፣ በመነካካት፣ በመቁረጥ ወይም በማበላሸት ለሚደርስ ብልሽት DeKalb County አውራጃው ሀላፊነት እንደማይወስድ እርስዎ እና ተማሪው ተረድተዋል፡፡ ማንኛውም የ DeKalb ካውንቲ ት/ቤት ዲስትሪክት የበይነመረብ ተቀባይነት አጠቃቀም ስምምነትን የማያሟላ ማንኛውም ተጠቃሚ ተማሪ በአከባቢው የት/ቤት አስተዳደር ቅጣቶች እርምጃዎች ይወሰዳል። የተማሪ ህግ መጣስ ጥቅሞችን የማግኘት መብትን ከማሳገድ እና ከማቋረጥ ባሻገር ተገቢ የስነ-ምግባር እርምጃ ሊያስከትል ይችላል፡፡
የወላጅ/አሳዳጊ ስም
(እባክዎ ይጻፉ):
ወላጅ/አሳዳጊ
ፊርማ፡ ቀን:
የተማሪ ስምምነት እና ፊርማ
1. ለት/ቤት የተሰጠውን መሳሪያዬን እከባከባለሁ፡፡
a. ጉዳትን ለመከላከል ሶኬቶች እና አገናኝ ገመዶች መሳሪያው ላይ በጥንቃቄ መሰካት አለባቸው፡፡
b. መሳሪያዎች በጭራሽ ባልተቆለፈ ሳጥን፣ መኪና ወይም በማንኛውም ቁጥጥር በሌለበት ቦታ መተው የለባቸውም፡፡
c. ማንኛውም የሶፍትዌር/ሀርድዌር ጉዳዮችን በ Incident IQ – የተማሪ የእርዳታ ዴስክ ፖርታል በኩል ያሳውቁ፡፡
d. መሳሪያውን በማይጠቀሙበት ወቅት ጥበቃ በሚደረግለት፣ ቁጥጥር የሚደረግበት ሙቀት ባለበት ሁኔታ ውስጥ ያስቀምጡት፡፡
2. ት/ቤት የሰጠኝን መሳሪያ ለሌላ ሰው በፍጹም አላውስም፡፡
3. ምግብ እና መጠጦች ከመሣሪያዬ ራቅ አደርጋለሁ።
4. የእኔንም ሆነ በማንኛውም የት/ቤት ውስጥ የተቀመጠ መሳሪያን አልበታትንም፣ ጄይልብሬክ ወይም ሀክ አላደርግም፡፡
5. በመሳሪያዬ ላይ ምንም አይነት ጥገና ለማድረግ አልሞክርም።
6. ት/ቤቴ የሰጠውን መሳሪያ አብሮት በተሰጠው መያዣ ብቻ በመያዝ ጥንቃቄ አደርግለታለሁ፡፡
7. ት/ቤቴ የሰጠውን መሳሪያ ት/ቤት፣ ቤት ውስጥ ወይም በማንኛውም ቦታ የምጠቀመው ተገቢ በሆነ እና የት/ቤቱን ደንብ ባከበረ መልኩ ነው፡፡ መሣሪያዬን አግባብ ባልሆነ መንገድ ከተጠቀምኩ በት/ቤቴ የቅጣት እርምጃ ሊወሰድብኝ ይችላል፡፡
8. ትምህርት ቤት በተሰጠው መሳሪያ ላይ ማስዋቢያዎችን (እንደ ተለጣፊዎች፣ ማርከሮች፣ ወዘተ) አላስቀምጥም። ት/ቤት በሰጠው መሳሪያ ላይ የሚገኝ የሲሪያል ቁጥር መለጠፊያን አልጥም/አላበላሽም፡፡
9. በት/ቤት የተሰጠው መሣሪያዬ በማንኛውም ጊዜ ያለማስታወቂያ ለምርመራ እና ቁጥጥር ተጋላጭ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ። መሳሪያው ላይ የምሰራው ወይም መሳሪያውን የማደርገው ነገር ሁሉ ሚስጥር አይደለም፡፡
10. የእኔን የይለፍ ቃል ለመምህር ወይም ከት/ቤት ለመጣ አዋቂ ሰው ወይም ለእኔ ወላጅ/አሳዳጊ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ሰው አልሰጥም፡፡
11. የኢንተርኔት ግንኙነት መሣሪያ የ DCSD ንብረት እንደሆነ እና ከዲስትሪክቱ ሲለቀቅ እና / ወይም የዓመቱ መሰብሰብ ሂደት ሲጠናቀቅ መመለስ እንዳለበት ተረድቻለሁ።
12. መሣሪያዬን ብጎዳ ወይም ከጠፋብኝ ወይም ከተሰረቀ መሣሪያውን የመተካት ወጪ እንደሚኖርብኝ አውቃለሁ። በመሳሪያው አጠቃቀም ስምምነት እና በተማሪው ስምምነት ላይ ባሉት ደንቦች እስማማለሁ፡፡
የተማሪ ስም
(እባክዎ ይጻፉ):
የተማሪ ፊርማ፦ ቀን: