ህጋዊ የምዝገባ ሰነድ የናሙና ክፍሎች

ህጋዊ የምዝገባ ሰነድ. የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ፀሀፊ ሁሉንም የህጋዊ ሰውነት የምዝገባ ሰነዶችን የሚከተሉትን ጭምር ፋይል አድርጎ በጥንቃቄ ማስቀመጥ አለበት፡፡ • የክልሉን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ማቋቋሚያ አዋጅ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ • የመስኖ ልማት ለማልማት ስምምነት የተደረገበትና በተቆጣጣሪው አካል /ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ/ ተቋራጭ የተፈረመበት ሰነድ፣ • የመስኖ ውሃን ለማስተዳድር የተላለፈበትና የተፈረመበት ሰነድ/ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር እና በተቆጣጣሪው አካል/ • ማንኛውም የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ 3.3.3.2 ውሎች፣‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ከሌሎች አላላት ጋር አገልግሎቶችን ለማግኘት ወይም መሳሪያዎቸን ለመከራየት ውሎችን ሊይይዝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ማኅበሩ የመስኖ አውታሩን የጥገና ስራ ለመስራት በአካባቢው ካሉ ተቋረጮች ጋር ወይም ለማኅበሩ ስራ ፈጻሚዎች ስልጠና ለመስጠት ስልጠና ከሚሰጥ ተቋም ጋር የኮንትራት ውል ስምምነት ሊፈራረም ይችላል፡፡ ሌላው የተለየ ውል /የአገልግሎት ስመምነት/ በማህበሩ እና በውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ቢሮ ወይም የግል ተቋራጮች የተወሰነውን የዕድሳትና ጥገና ስራ ለመስራት የሚፈረም የውል ስምምነት ሊሆን ይችላል፡፡ የማኅበሩ ፀሀፊ ሁሉንም የተፈረመባቸውን የውል ሰምምነቶች በህጋዊ መዝገብ ፋይል አድርጎ መያዝ አለበት፡፡ የስራ አመራር ኮሚቴ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ መዝገብ እና የግጭት አፈታትና አወጋገድ ኮሚቴ መዝገብ፣ በማኅበሩ ተመራጭ የሆኑ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት፣የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት እና የግጭት አፈታትና አወጋገድ ኮሚቴ ስምና ዝርዝር መረጃዎች በስራ አመራር ኮሚቴ፣ በቁጥጥር ኮሚቴ፣ በግጭት አወጋገድና አፈታት ኮሚቴ መዝገብ ላይ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር በዓመታዊ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ወቅት የስራ አመራር ኮሚቴ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ እና/ወይም የግጭት አፈታትና አወጋገድ ኮሚቴ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት፣ የማኅበሩ ፀሀፊ ሁልጊዜም መዝገቡን ማስተካከል ይኖርበታል፡፡ የማኅበሩ ፀሀፊ ሁልጊዜም የተሻሻለውን የተመራጮች ዝርዝር መረጃ ለተቆጣጣሪው አካል/ለውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ/ መላክ አለበት፡፡ የስራ አመራር ኮሚቴ እና የቁጥጥር ኮሚቴ መዝገብ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ አለበት፣ • የስራ አመራር ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚቴ ተግባራት፣ • የተመራጭ አበላት ስም ዝርዝር፣ • የተመራጮች አድራሻ፣ • በማኅበሩ የመስኖ አገልግሎት ክልል መሬቱ የሚገኝበት ቦታ፣ እና • የተመረጡበት ቀን፣ የስራ አመራር ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚቴ ዝርዝር መረጃ የያዘ ሁሉም አባላትና አባል ያልሆኑ ተጠቃሚዎች እንዲያዩት በማኅበሩ ጽ/ቤት ወይም በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መለጠፍ አለበት፡፡ የስራ አመራር ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚቴ መዝገብ ምሳሌ በዕዝል- መ ቀርቧል፡፡ የተግባር መዝገብ /Techinical register/ የመሰኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የመስኖ አሰራርና ጥገና /O&M/ ኃላፊነት በሚረከብበት ወቅት፣ በመስኖ አገልግሎት ክልሉ የመስኖ አውታሩን አሰራርና ጥግና በቅልጥፍና እና በውጤት ለመፈፀም እንዲቻል አስፈላጊ የሆኑ ሙያዊ መረጃዎች /technical records/፣ ማኑዋሎች እና ካርታ መረከብ አለበት፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የሚከተሉትን ሰነዶች፣ ማኑዋሎች እና ካርታዎች መረከብና የማኅበሩ ፀሀፊ በቴክኒክ መዝገብ ፋይል አድርጎ እንዲይዝ ይመከራል፡፡ • ሁሉም በመስኖ አገልግሎት ክልል ውስጥ ያሉ የመስኖ አውታሩ ዝርዝር ቆጠራ /Inventory/ ከስምምነቱ በኋላ ማኅበሩ የአሰራርና ጥገና ስራ የሚከናወንባቸው ከመስኖ አውታሩ ጋር ተያያዥ የሆኑ ግንባታዎችን ጭምር ማለትም ለምሳሌ መቀልበሻ ቦዮች እና ድልድዮችን ጨምሮ፣ • የመስኖ አውታርና ተያያዥ ግንበታዎች ንድፍ /Drawings/ • የአሰራርና ጥገና /O&M/ ማኑዋል፣ • የመስኖ ተፋሰስ አናት ስራ /Headwork/ • የላይኛው የመስኖ አውታሩ የተጠለፈበትን ቦታ /location of headwork/ ካናሎች የሚገናኙበትን ሲስተም፣ የመቆጣጠሪያ ቦተዎቸን እና የመስኖ አውታሩን የአገልግሎት ክልል የሚያሳይ ካርታ/ዎች የጥገና መዝገብ /maintenance register/ የቴክኒክ ተጠያቂነት እና ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ፣ በመስኖ አገልግሎት ክልሉ የመስኖ አውታር እንክብካቤና ጥገና ስራዎች ጋር የተያያዙ ተግባራት አፈፃፀም ዝርዝር መረጃዎች በሙሉ በትክክል መያዝ በጣም ወሳኝ ...