መልመጃ የናሙና ክፍሎች

መልመጃ. ሥልጠናው ከተሰጠና ውይይት ከተደረገበት በኋላ ሰልጣኞች በጨበጡት ዕውቀት መሰረት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎችን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ የቅጣት ዓይነቶችን ጨምሮ በማዘጋጀት የመለማመድ ዕድል ማግኘት አለባቸው፡፡ ወይም መክፈል የሚገባቸውን የመስኖ ውኃ አገልግሎት ክፍያ በወቅቱ ያለመክፈል ሁኔታ ሊያስከትል ይችላል፡፡ 🗐 ከስልጠናው በኋላ ሰልጣኞች የውስጥ መተዳደሪያ ደንብን አስመልክቶ መሰረታዊና ውጤታማ የሆኑ የቅጣት አይነቶችን ጭምር የያዘ በአጭሩና ዋናዋና ጉዳዮችን የሚያብራራ ማኑዋል ለሁሉም የስልጠናው ተሳታፊዎች መሰጠት አለበት፡፡ ማኑዋል-3 አስተዳደረዊ አመራር‌ 3.1 ስብሰባዎችን ማቀድ፣ ማካሄድና መምራት፣‌ ዓላማ፣ የስልጠናው ተሳታፊዎች በራሳቸው የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውስጥ የስብሰባ ዕቅድ አዘገጃጀት፣ አተገባበር እና አመራር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ለማድረግ ነው፡፡ ርዕሶች፣ • አስተዳደራዊ አመራር መግቢያ o የጥሩ ስራ አመራር መርሆዎች o ግልጽነትና ተጠያቂነት • የስብሳባ ዓይነቶች • የስብሰባዎች ዓላማ • የቀልጣፋና ውጤታማና ስብሰባዎች ህግጋት/ደንቦች o የመወያያ አጀንዳ ማዘጋጀት o ተስማሚ የስብሰባ ቦታ እና ቀን o የስብሰባ ጥሪ ማስተላለፍ/ማሳወቅ o የስብሰባ ዝግጅት ማድረግ o ውጤታማ የመድረክ አመራር o የሪፖርት አቀራረብ o የተሳታፊዎች መልካም ስነምገባር o ውሳኔዎችን ለማጽደቅ የድምጽ አሰጣጥ o የስብሰባ አደረጃጀት /Structured meeting/ o የተሳታፊዎች የነቃ ተሳትፎ o የሰብሰባ ቃለጉባኤ አዘገጃጀት • የስብሰባው ተሳታፊዎች፡- የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአመራር እና የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት • የሰልጠና መሳሪያዎች፡- ፍሊፕ ቻርት፣ ማኑዋልና መልመጃ/ጭውውቶች • የሚያስፈልግ ጊዜ፡- 3፡30 /ሶስት ሰዓት ተኩል/ 3.1.1 አስተዳደራዊ አመራር መግቢያ‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የሚመሰረተው በግለሰቦች የጋራ ፍለጎት በዋናነትም የመስኖ መሬታቸውን ለማልማት በሚፈልጉ ሰዎች ነው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር በቂ አገልገሎት ለተጠቃሚዎች ለመስጠት በተለይም በማኅበሩ አገልግሎት ክልል ውስጥ በበቂ መጠንና እና ፍትሃዊ የመስኖ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል የእለት ከዕለት ተግባራትን የሚያከናውኑ አመራር አባላት ከጠቅላላው አባላት ውስጥ እንዲመረጡ ይደረጋል፡፡ ማኅበሩን በአግባቡ ለመምራት የተመረጡ አመራር አካላት በአብዛኛው በአባላት እምነት የተጣለባቸውና ኃላፊነታቸውን ሊወጡ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አመራር አካላት በተጠቃሚዎች በተለይም በአባላት ዘንድ ሙሉ ታማኝነታቸው ሊረጋገጥ የሚችለው ሁሉም የማኅበሩ ጉዳዮች ግልጽና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ ሲፈፀሙና ሁሉም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት በማኅበሩ እየተሰራ ያለውን ስራ ምን እና እንዴት እየተሰራ እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ሲገነዘቡ ብቻ ነው፡፡ 3.1.1.1
መልመጃ. ስልጠናው ከተሰጠና ውይይት ከተደረገበት በኋላ አስልጠኙ አንዴት ዓመታዊ የስራ ዕቅድ እና/ወይም ዓመታዊ ሪፖርት ሊዘጋጅ እንደሚችል ማሳየት አለበት፣ • አሰልጠኙ እንዴት ሊዘጋጅ እንደሚችል ካሳየ በኋላ ሰልጣኞች ባገኙት ክህሎት መሰረት ዓመታዊ የስራ እቅድ እና/ወይም ዓመታዊ ሪፖርት አንዲያዘጋጁ በመጠየቅ መለማመድ ይኖርባቸዋል፡፡ የዓመታዊ ሪፖርት አቀራረብ ሞዴል ፎርም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ 🗐 ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ስለ ዓመታዊ የስራ ዕቅድ፣ ዓመታዊ በጀት እና ዓመታዊ ሪፖርት በቀላል አቀራረብ ሊያብራራ የሚችል ማኑዋል ለሁሉም ሰልጣኞች መሰራጨት ይኖርበታል፡፡ የዓመታዊ ሪፖርት አቀራረብ ሞዴል ፎርም