መልመጃ /Exercise/ የናሙና ክፍሎች

መልመጃ /Exercise/. ስልጠናው ከተሰጠና ውይይት ከተደረገበት በኋላ ሰልጣኞች ባገኙት አዲስ ዕውቀት መሰረት ስለኮሙዩኒኬሽን በጭውውት መልክ /as role play/ እንዲሳተፉ እድል ማግኘት ይገባቸዋል፡፡ አንዱ አማራጭ ለመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የኮሙዩኒኬሽን ዕቅድ ሰልጣኞቹ እንዲያዘጋጁ መልመጃ መስጠት ነው፡፡ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውስጥ በግንኙነት ድክመት ምክንያት ሊመጡ ከሚችሉት ችግሮች መካከል ዋናው በማኅበራቸው ላይ አመኔታ ማጣት እና በውሃ ተጠቃሚዎች መካከል አለመተማመን ከማስከተሉም በላይ በመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገና/እንክብካቤ በርካታ ጎጂ ውጤት ሊያስከትል ይችላል፡፡ 🗐 ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ስለ ውስጣዊና ውጫዊ ኮሙኒኬሽን ዋና ዋና ጉዳዮችን በአጭሩ ሊገልጽ የሚችል ማኑዋል እንዲያገኙ አድርግ፡፡ 2.3 ግጭት አወጋገድና እና እርቅ /Conflict resolution and arbitration/‌ ዓላማ • የስልጠናው ተሳታፊዎች በውስጥና በውጭ አለመግባባትን ወይም ግጭትን ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን፣ ግጭትን እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ የውስጥና የውጭ ግጭቶች ሲከሰቱ መፍትሄ ለማስጠት መከተል ባለባቸው ሂደቶች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ነው፡፡