ማህበረሰቡ በት/ቤቶች ድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ ክትትል እንዲያደርግና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል የአሠራር ዘዴ. ማህበረሰቡ በትምህርት ቤቶች አሰራር ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአካባቢው ማህበረሰብ በትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት አስተቃቀድና አጠቃቀም ላይ ቁልፍ ድርሻ እንዲኖረው ተደርጎ በአተገባበር መመሪያው በግልጽ ተቀምጧል። ከዚህ አንጻር፦ • በትምህርት ሚኒስቴርና እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ለክልሎች የተላከውን ጠቅላላ የገንዘብ መጠን እንዲሁም ለእያንዳንዱ ክልልና ወረዳ የሚከፋፈለውን የገንዘብ መጠን የሚያሳዩ ደብዳቤዎች ቅጂዎች በግልጽ እንዲቀመጡና ለህብረተሰቡ በሚታዩበት አግባብ ለዚሁ በተዘጋጀው የማስታወቂያ ቦርድ እንዲለጠፉ ማድረግ መኖር፡፡ • ሁሉም ትምህርት ቤቶች . በየዓመቱ ጥቅምት 21 (እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 31) ላይ የድጎማ በጀታቸውን እነዲያገኙ ማድረግና መከታተል • ወረዳዎች ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት መሣሪያዎችን በማሟላት ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ ተብሉ የተመደበውን ተጨማሪ የትምህርት ቤቶች ድጎማ በጀት እንዲደርሳቸው ማድረግ፡፡ • የት/ቤቶች የድጎማ በጀት አመዳደብ፣ አአጠቃቀም ላይ ክትትልና ግምገማ ማካሄድ/የክልል ትምህርት ቢሮዎች እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮዎች በትምህርት ሚኒስቴር የተመደበውን የት/ቤቶች ድጎማ በጀት መጠን ትክክለኛነት ማረጋገጥ፡፡ • የክልል ትምህርት ቢሮዎች ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ትምህርት ማጠናከሪያ የተላከው 2% ተጨማሪ የት/ቤቶች ድጎማ ተማሪዎቹ የሚገኙባቸውን ወረዳዎችና ት/ቤቶች ባላቸው ዕውቀት/መረጃ መሠረት በመለየት ገንዘቡ ደርሶ በተገቢው ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፡፡ • ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ያሉዋቸው ወረዳዎች ከሌሎች ወረዳዎች በተለየ ሁኔታ ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ወረዳዎቹ ለዚሁ ጉዳይ የተመደበው የድጎማ በጀት የተመዘገቡ ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ብዛት መሠረት በማድረግ ተማሪዎቹ ለሚገኙባቸው ት/ቤቶች መላክ ይኖርባቸዋል፡፡ • ከዚህ በተጨማሪ የክልል ትምህርት ቢሮዎች አካታች የሆነ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት ለማጠናከርና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት መሣሪያዎች አቅርቦትን ለማሻሻል በሚረዳ መልኩ ገንዘቡን ለሁሉም ወረዳዎች የማዳረስ ነፃነት/መብት አላቸው፡፡ • የክልል ትምህርት ቢሮዎች ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚመደበው ተጨማሪ ገንዘብ ለምን ተግባር ማዋል እንደሚገባ ከወሰኑ በኋላ ገንዘቡ ለእያንዳንዱ ወረዳ የተደለደለበት አሠራር፣ ተግባርና የገንዘብ መጠን መረጃ/ሰነዶች አደራጅተው ማስቀመጥ ይገባቸዋል፡፡ • የክልል ትምህርት እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብበር ቢሮዎች ልዩ ፍላጎት ላላቸው ህፃናት የተመደበውን ገንዘብ ወረዳዎች ዘንድ በወቅቱ መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ አደራጅተው መያዝ ይጠበቅባቸውል።፡፡