ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ መገለጫ ባህርያት. በፕሮጄክት ዝግጅት የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ የሚካሄዱና ከመኖሪያቸው ሊፈናቀሉ የሚችሉ ሰዎችን ተሳትፎ ጨምሮ፣ የቤተሰብና የቤት ቆጠራ፣ ተጋላጭ ቡድኖችን የሚመለከት መረጃን ጨምሮ የማሕበረ-ኢኮኖሚዊ ጥናቶችን ግኝቶች መዘርዘር፡፡ ተግባር 8፡ ብቁ መሆን፡ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሰዎችንና ለካሳና ሌሎች የዳግም ሰፈራ ድጋፎች ብቁ የሚሆኑባቸውን መስፈርቶች አግባብነት ካላቸው ቀነ ገደቦች ጋር ማስቀመጥ፡፡ ተግባር 9፡ የኪሳራ ግምትና ካሳ፡ የመተኪያ ወጪያቸውን ለመሸፈን የኪሳራ ዋጋን ለመገመት ጥቅም ላይ የዋለውን ስነ-ዘዴ መግለጽ፤ በሃገር ውስጥ ሕግ መሰረት የተጠቆሙ የካሳ ዓይነቶችና ደረጃዎችን እና ለጠፉ ንብረቶች የመተኪያ ዋጋ ለማሳካት የሚያስፈልጉ ተጨማሪ እርምጃዎችን መግለጫ ማካተት፡፡ ተግባር 10፡ የመፈናቀል መጠን፡ ጉዳዩ የሚነካቸው ሰዎች፣ ቤተሰቦች፣ መዋቅሮች፣ የመንግስት ሕንጻዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የሰብል መሬቶች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ወዘተ… ብዛትን ማጠቃለል፡፡ ተግባር 11፡ ባለ መብት ማድረጊያ ማዕቀፍ፡ በጉዳዩ የተነኩ ሰዎችን ምድቦች በሙሉ እና የቀረቡላቸውን አማራጮች ቢቻል በሰንጠረዥ መልክ የሚያሳይ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፡፡ ተግባር 12፡ የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ የመመለሻ እርምጃዎች፡ የተፈናቃይ ሰዎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ወይም ወደ ቀድሞ ለመመለስ የሚያገለግሉ የተለያዩ እርምጃዎችን መግለጽ፡፡ ተግባር 13፡ የዳግም ሰፈራ ቦታዎች፡ የቦታ መረጣ፣ የቦታ ዝግጅትና የቦታ ለውጥ፣ ታሳቢ የተደረጉ አማራጭ የማዛወሪያ ቦታዎችን ዝርዝርና የተመረጡተን ቦታዎች ማብራሪያ፣ በአስተናጋጅ ማህበረሰቦች ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖን ማካተት፡፡ ተግባር 14፡ የመኖሪያ ቤት መሰረተ ልማትና ማሕበራዊ አገልግሎቶች፡ መኖሪያ ቤት፣ መሰረተ ልማት (ለምሳሌ፡- የውሃ አቅርቦት፣ መጋቢ መንገዶች)፣ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች (ለምሳሌ፡ ት/ቤቶች፣ የጤና አገልግሎቶች) ለማቅረብ (ወይም የሰፋሪዎቹን ወጪ ለመሸፈን) ዝርዝር ዕቅዶችን፤ ለአስተናጋጅ ሕዝቦች ተመጣጣኝ አገልግሎቶች መቅረባቸውን የሚያረጋግጡ ዕቅዶች፤ ለእነዚህ ተቋማት የሚያስፈልጉ ማንኛውም የሳይት ልማት፣ ምህንድስና እና የአርክቴክቸር ዲዛይን ስራዎች፡፡፡ ተግባር 15፡ የቅሬታ አቀራረብ ሒደቶች፡ ከዳግም ሰፈራ የሚመነጩ ግጭቶችን በሶስተኛ ወገን ለመፍታት ዋጋው ተመጣጣኝና ተደራሽ የሆነ አሰራር መዘርጋት፤ እንዲህ ዓይነት የቅሬታ አቀራረብ ስርዓቶች የፍትሕ ዳኝነት እና የማህበረሰብና ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች መኖራቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተግባር 16፡ ድርጅታዊ ኃላፊነቶች፡ የሰፈራ እርምጃዎችን የመውሰድና አገልግሎቶችን የማቅረብ ኃላፊነት ያለባቸውን ኤጄንሲዎች መለየትን ጨምሮ ድርጅታዊ ማዕቀፍን መዘርጋት፤ በትግበራው ሒደት ውስጥ በሚሳተፉ ኤጄንሲዎችና ወሰነ-ስልጣናት መካከል ተገቢው ቅንጅት መፈጠሩን ለማረጋገጥ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ ተግባሪ ኤጄንሲዎች የሰፈራ ተግባራትን ቀረጻና ትግበራ የማከናወን አቅማቸውን ለማጠናከር የሚያስፈልጉ ማናቸውም እርምጃዎች (ቴክኒካዊ ድጋፍን ጨምሮ)፤ በፕሮጄክቱ ስር የቀረቡ አገልግሎት መስጫ ተቋማትንና አገልግሎቶችን የማስተዳደር ኃላፊነትን ለአካባቢው ባለስልጣናት ወይም ሰፋሪዎች ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ሁኔታዎችና አግባብነት ሲኖረውም እንዲህ ዓይነት ሌሎች ኃላፊነቶችን ከሰፈራ ተግባሪ ኤጄንሲዎች ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ሁኔታዎች፡፡ ተግባር 17፡ የትግበራ የጊዜ ሰሌዳ፡ ከዝግጅት እስከ ትግበራ ድረስ ያሉትን ሁሉንም የሰፈራ ተግባራት የሚሸፍን የትግበራ የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት፣ ለሰፋሪዎችና አስተናጋጆች እንደሚቀርቡ የሚጠበቁ ጠቀሜታዎች የሚደርሱባቸውንና የተለያዩ የድጋፍ ዓይነቶች የሚተገበሩባቸውን ቀናት ማካተት፡፡ ይህ የጊዜ ሰሌዳ የሰፈራ ተግባራት ከአጠቃላዩ ፕሮጄክት ትግበራ ጋር እንዴት እንደሚተሳሰሩ ማመልከት አለበት፡፡ ተግባር 18፡ ወጪ እና በጀት፡ ለሁሉም የሰፈራ ተግባራት የወጪ ግምቶችን፣ የዋጋ ግሽበት መጠን፣ የሕዝብ ቁጥር ዕድገትና ሌሎች መጠባበቂያዎችን፤ የወጪዎች ጊዜ ሰሌዳ፤ የገንዘብ ምንጭ፤ ከተግባሪ ኤጄንሲዎች ወሰነ-ስልጣን ውጭ ባሉ አካባቢዎች ገንዘብ በወቅቱ እንዲለቀቅና የሰፈራ ወጪ አሸፋፈን አደረጃጀቶችን የሚያሳይ ሰንጠረዥ ማዘጋጀት፡፡ ተግባር 19፡ ክትትል፣ ግምገማ እና ሪፖርት አቀራረብ፡ ተግባሪ ኤጄንሲ የሚያካሂዳቸውን የሰፈራ ተግባራት ለመከታተል የሚያስችሉ ስርዓቶችን በመዘርጋት የተሟላና ምክንያታዊ መረጃ መኖሩን ለማረጋገጥ በገለልተኛ ታዛቢዎች መደገፍ፤ የሰፈራ ተግባራትን ግብዓቶችና ውጤቶችን ለመለካት የአፈጻ...