ሥራን ማስተላለፍ ማቋረጥ ወይም መሰረዝን በተመለከተ. 9.1 አሰሪው ባለቤት ሥራውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የሥራውን ጊዜ ቢያሸጋግር፣ ቢያቋርጥ ወይም ቢሰርዝ አማካሪው ሥራው እስካቆመበት ጊዜ ድረስ የተሠራው ሥራ ተሰልቶ የሚገባውን ክፍያ ሊከፍለው ይገባል፡፡ በነዚህ ምክንያቶች ሥራው መቋረጥ ቢያስፈልግ ባለቤቱን ለአማካሪው የ20 ቀናት ቅድመ ማስታወቂያ ይሰጣል፡፡ በተመሳሳይም አማካሪው ሥራውን ማቋረጥ ቢኖርበት ለባሌቱ በ20 ቀናት ቅድመ ማስታወቂያ ይሰጣል ፣ የግንባታውን ስራ ለአሰሪው ያስረክባል ፡፡
9.2 የግንባታ ስራው በየምዕራፎቹ መጠናቀቅ መሃል፣ ለቀጣዩ ምዕራፍ አሰሪው ባለቤት ክፍያን ባለመልቀቅ ምክንያት ስራው ከሶስት ወር በላይ ቢቋረጥ ይህ ውል እንደተቋረጠ ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱ ወገኖች በሚስማሙበት መሰረት ውሉ ሊታደስ ይችላል፡፡