ተቀምጦለት ማቅረብ የናሙና ክፍሎች

ተቀምጦለት ማቅረብ. አለባቸው፡፡ • የስራ አመራር ኮሚቴው ውሳኔዎች እንዲታወቁ በማኅበሩ ጽ/ቤት እና/ወይም አብዛኛው ተጠቃሚ በሚገኝበት መንደር እንዲለጠፉ በማድረግ ሁሉም እንዲያውቀው ማድረግ፣ • የማኅበሩ ቁጥጥር ኮሚቴ የሂሳብ አመዘጋገቡን፣ ሰነዶች እና አጠቃላይ የገንዘብ አጠቃቀሙን በተወሰነ የጊዜ ገደብ መቆጣጠር፡፡ • የቁጥጥር ኮሚቴው የጠቅላላ ጉባኤውን በመወከል የፀደቀውን ዓመታዊ በጀትና የስራ ዕቅድ መገምገምና እንዲፀድቅ ማድረግ፣ • ዓመታዊ ሪፖርት ከፋይናንስ መግለጫዎች ጋር እንዲሁም ዓመታዊ የስራና የበጀት ዕቅድ በሊቀመንበሩ አመካኝነት እንዲቀርብ በማድረግ በማኅበሩ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ስብስባ በተገኙ አባላት አብላጫ ደምጽ ማጽደቅ፣ • የግልፀኝትና ተጠያቂነትን ለማረገገጥ አንደኛው መንገድ ደግሞ ውጤታማ የሆነ የጠቅላላ ጉባኤ፣ የስራ አመራር ኮሚቴ እና የቁጥጥር ኮሚቴ ስብሰባዎች ማካሄድ ነው፡፡ • የስራ አመራር ኮሚቴው ቢያንስ በየወሩ አንድ ጊዜ በቋሚነት ስብሰባ ሊኖረው ይገባል፡፡ ? የስልጠናው ተሳታፊዎችን በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውስጥ ምን አይነት ሰብሰባዎች ናቸው መካሄድ አለባቸው የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ሀሳብ እዲሰጡበት በማድረግ የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም ነጭ ሰሌዳ ላይ ይጻፉ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ማኅበሩ የሚከተሉት የስብሰባ ዓይነቶች ሊኖሩት ይገባል፡፡ • የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መካሄድ አለበት፣ • ምንም እንኳ በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ የሚገለጽ ቢሆንም፣ የቁጥጥር ኮሚቴና የግጭት አስወጋጅ ኮሚቴዎች በየሶስት ወሩ በተለያየ ጊዜ ስብሰባ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 3.1.2 የስብሰባዎች ዓለማ ፣‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበርን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት የማኅበሩ አባላት እንዲሁም ተመራጭ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላትና የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት በታቀደ የስብሰባ ቀን መገናኘትና መወያየት ይኖርባቸዋል፡፡ • መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ ለመገምገም እና ለመወያየት እንዲሁም በሚከተሉት ጉዮች ውሳኔዎችን ለመወሰን፣ o የታቀዱ፣ በሂደት ላይ ያሉ ተግባራትን በሚመለከት o ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን o በመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገና ስላሉ ችግሮች o የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎችን ማኅበር አመራር o ከማኅበሩ ስራ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት • በውስጥ ችግሮች ላይ ለመወያየትና ተገቢውን መፍትሄ ለመፈለግ፣ • የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብና የወስጥ መተዳደሪያ ደንብ በሚጥሱ አባላት ወይም አባል ባልሆኑ ተጠቃሚዎች ሊወሰድ የሚገባውን ቅጣት ለመወሰን፣ • በዓመታዊ የጠቅላላ ጉባኤ ወቅት የስራ አመራር ኮሚቴ አባላትንና የቁጥጥር ኮሚቴ አባላትን ለመምረጥ፣ ስለሆነም በአንድ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውስጥ ተጠያቂነትና ግልፀኝነትን ለማሰፈን ቋሚ የሆነ ወይም መደበኛ ስብሰባ በሚከተሉት ምክንያቶች አስፈላጊ ነው፡፡ • የዕለት ከዕለት ተግባራትን የሚያከናውኑ ተመራጮች/ማለትም ሊቀመንበር፣ ፀሀፊና ገንዘብ ያዥ/ ሌሎች የኮሚቴ አባላት ስለ ተግባራት አፈፃፀም እና ባህሪ በወርሃዊ ስብሰባ ወቅት ለመግለጽ፣ • የስራ አመራር ኮሚቴው ስለወሰናቸው ውሳኔዎች፣ ስለ ተከናወኑ ተግባራትና የአተገባበሩን ሂደት በማኅበሩ ዓመታዊ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ለመግለጽ፣ • የቁጥጥር ኮሚቴው የሰራቸውን የቁጥጥር ስራዎች ውጤት በማኅበሩ ዓመታዊ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በሪፖርት ለማቅረብ፣ 3.1.3 የውጤታማና ፍሬያማ ስብሰባዎች ደንብ‌ ? የስልጠናው ተሳታፊዎችን ውጤታማና ፍሬያማ ስብሰባዎቸን ለማካሄድ አስፈላጊ ደንቦች ምን ምን ናቸው የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ሀሳብ እዲሰጡበት በማድረግ የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም ነጭ ሰሌዳ ላይ ጻፍ፣ የታቀዱ ስብሰባዎች ውጤታማና ፍረያማ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚከተሉት ደንቦች በትክክል ተግባራዊ መደረግ አለባቸው፣ • የመወያያ አጀንዳዎችን ማዘጋጀት፣ • ተገቢ የስብሰባ ቦታና ቀን መምረጥ፣ • የሰብሰባ ጥሪ ማስተላለፍ፣ • ስለስብሰባው በቂ ዝግጅት ማድረግ፣ • ስብሰባውን በአግባቡ መምራት፣ • ሪፖርቶችን ለተሰብሳቢዎች በጥሩ ሁኔታ ማቅረብ፣ • ውሳኔዎችን በድምጽ ማጽደቅ፣ • የስብሰባው ተሳታፊዎች መልካም ስነምግባር፣ • የስብሰባውን ሂደት እደተግባራቱ ቅደም ተከተል በስምምነት ማደረጃት፣ • የሁሉም ተሳታፊ የነቃ ተሳትፎ መኖር እና • የስብሰባ ቃለ-ጉበኤ መያዝ 3.1.3.1 የመወያያ አጀንዳዎችን ማዘጋጀት፣‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ሊቀመንበርና ፀሀፊ የመወያያ...