አብይ ተግባር 5፡ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጠናከረ ግንኙነት መፍጠር. የአጋርነት ስራችን ከማጠናከር አኳያ ከዩኤን ውሜን (UN WOMEN) ጋር በቀጣይነት በትብብር ለመሥስራት የሚያስችል የጋራ ምክክር ተካሂዶ፣ በመጪው ጊዜ በጋራ የሚሠሰሩ ሥራዎች የተለዩ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት የተሻሻለ የጽንሰ ሐሳብ ሰነድ (concept note) ተዘጋጅቷል። በመቀጠልም ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነድ ለመቅረጽ ስምምነት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ከሴቭዘችልድረን (Save the Children) ጋር ፕሮጀክት የመገምገምና የመከለስ ሥራ ተከናውኗል። ከሲቪል ማህበራት ጋር የትብበር ስራዎችን በተመለከተም በሴቶች እና በሕፃናት መብቶች ዙሪያ በአጋርነት ለመስራት ከሚችሉ ተቋማት ጋር የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ምክክር የተደረገ ሲሆን በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎችን የመለየት ጅማሮ ተካሂዷል። በመሆኑም ተለይተው የወጡትን የጋራ ስራዎች ከክፍሉ አመታዊ ዕቅድ ጋር በማጣጣም የሚተገበርበትን ሁኔታ በቀጣይ ለማመቻቸት ታቅዷል። • የሰብአዊ መብቶች አያያዝ አቤቱታ አቀራረብ እና የምርመራ ሥርዓት ማሻሻያ መመሪያ ዝግጅትንና ተመሳሳይ ጥናቶች፣ የሴቶችና ሕፃናት መብቶችን የሚመለከቱ ክትትሎች፣ መግለጫዎች፣ ምክረ ሃሳቦች በሚዘጋጁበት ጊዜ በመሳተፍ የቴክኒክ ድጋፍ ለተለያዩ የኮሚሽኑ የስራ ክፍሎች በመስጠት በትብብርና በቅንጅት ሰርቷል። • በሴቶች እና በሕፃናት መብቶች ላይ ከሚሰሩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አካላት ጋር በመስራት ረገድ ጥረቶችን ለማጠናከር ከአፍሪካ የሕፃናት መብቶችና ደህንነት ኮሚቴ ጋር ተገቢውን የስራ ግንኙነት መፍጠር አንዱ ጉዳይ መሆኑ ታምኖበት ጥረቶች ተጀምረዋል።በዚህም መሰረት ኢሰመኮ በኮሚቴው ዘንድ የአጋርነት ደረጃ (affiliate status) ለማግኘት የሚያስችለውን ማመልከቻ ለማቅረብ አስፈላጊ ሰነዶች የኢሰመኮን እና ስራ ክፍሉን ተግባራት የሚያትት አጭር ዘገባን ጨምሮ ተጠናቅሮ ለኮሚቴው ተልኳል፡፡ በተጨማሪም ለአፍሪካ የሰዎች እና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን መደበኛ ጉባዔ ስለሴቶች እና ሕፃናት መብቶች ጉዳዮች አጭር ዘገባ በጽሑፍ ቀርቧል፡፡ ኮሚሽኑም የአጋርነት ደረጃ አግኝቷል። አብይ ተግባር 6፡በሴቶችና ሕፃናት መብቶች ላይ የተሻለ ተቋማዊ አቅም መገንባት • በሕፃናት መብቶች ክትትል መመሪያ ዝግጅት፣ ትግበራ እና አቅም ግንባታ ዙሪያ የሚከተሉት ተግባራት ተከናውነዋል፡- o ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የሕፃናት መብቶች ድንጋጌዎች በስራ ላይ መዋላቸውን ለመገምገም እና ለመከታተል የሚያስችል የክትትል መመሪያ በአማካሪ ተዘጋጅቶ በኮሚሽኑ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ግብዓት ተወስዶ የተሻሻለ ረቂቅ ሰነድ ቀርቧል። የተዘጋጀውንም የክትትል መመሪያ በመጠቀም በጅግጅጋ በወንጀል የተጠረጠሩ ሕፃናትን አያያዝ አስመልክቶ ክትትል በማድረግ የሙከራ ትግበራ ተካሂዷል። o ቀደም ብሎ ተዘጋጅቶ የነበረውን የሕፃናት መብቶች የክትትል መመሪያ ከዓለም አቀፍ የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን በተጨማሪ ከአፍሪካ የሕፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር አንጻር ዳግም በመቃኘትና ያልተካተቱ ተጨማሪ ተቋማትን በማካተት በተከለሰው የክትትል መመሪያና መሣሪያ ሰነድ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችል ውይይት ተካሂዶል። በውይይቱም 25 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በውይይቱም ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችሉ ግብዓቶችን ለማግኘት ተችሏል። o በሕፃናት መብቶች ክትትል መመሪያና መሣሪያ ላይ ለኮሚሽኑ የክትትልና የሕፃናት መብት ባለሙያዎች የ3 ቀን ስልጠና ተሰጥቷል። በዚሁ ስልጠና 21 (4 ሴቶች) ሰልጣኞች ተሳትፈዋል። በስልጠናው ወቅት የሰብአዊ መብቶች ክትትል ተግባራዊ ሂደት፣ የሕፃናት መብቶች ስምምነት ክትትል መመሪያና መሣርያ እንዲሁም ሪፖርት አቀራረብ ላይ መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ እያንዳንዱ ባለሙያ በሕፃናት መብቶች ዙሪያ ክትትል ለማድረግ በሚያስብበት ጊዜ በቅድመ ዝግጅት ወቅት ታሳቢ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ የቡድን ውይይት ተደርጓል። የውይይቱ ውጤትም በመድረክ እንዲቀርብ ተደርጎ ለእያንዳንዱ ክትትል የቅድመ ዝግጅት ስራ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። በትግበራ ወቅት ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችና ችግሮችም ተለይተው ወጥተዋል። o ፆታዊ ትንኮሳን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የፖሊሲና አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ሂደትን በተመለከተ ከኮሚሽኑ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ከተውጣጡ ሰራተኞች ጋር ውይይት ለማካሄድና እንዲሁም የጸረ- ፆታ ትንኮሳ ረቂቅ ፖሊሲ፤ የስርዓተ ፆታን ያካተተ የሴ...