አብይተግባር 4፡የሴቶችና ሕፃናት መብቶች አተገባበር የተሻለ እንዲሆን ማስቻል የናሙና ክፍሎች

አብይተግባር 4፡የሴቶችና ሕፃናት መብቶች አተገባበር የተሻለ እንዲሆን ማስቻል. የሕፃናት መብቶች በማሳደጊያዎች፣ በጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በማረሚያ ቤቶች እና ሌሎች ተቋማት መከበራቸውን በመከታተል ምከረ ሃሳቦችን መስጠትና አፈጻጻማቸውን መከታተል በተመለከተ የሚከተሉት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ • በማረሚያ ቤቶች ያሉ ሴቶችና አብረዋቸው የታሰሩ ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዳሊቲ ማረሚያ ቤት በተደረገው ክትትል ግኝት መነሻ የተሰጠው ምክረ-ሃሳብ አተገባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ ያለውን ለውጥና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ መሻሻሉን ለማረጋገጥ የክትትልና የግፊት ስራ ተሰርቷል። የዚህም ክትትል ስራ ውጤቶች፡-