የለውጤታማ ቅጣት ቅድመ ሁኔታዎች የናሙና ክፍሎች

የለውጤታማ ቅጣት ቅድመ ሁኔታዎች. /Conditions for Effective sanctions/ ህግን በጣሱ ተጠቃሚዎች የቅጣት እርምጃዎች መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ ነገርግን ቅጣቱ የሚወሰድባቸው ግለሰቦች ላይወዱትና ሊቃወሙት ይችላሉ፡፡ ቅጣት ሁልጊዜም ውጤታማና ሊሳካ የሚችለው፤ • ቀስ በቀስ ወይም ደረጃ በደረጃ፣ • ሊታመን በሚችል እና • ተፈጻሚነት ሲኖረው ነው፡፡ ቀስ በቀስ ወይም ደረጃ በደረጃ የሚወሰድ ቅጣት፣ ቀስ በቀስ ወይም ደረጃ በደረጃ የሚወሰድ ቅጣት የሚያመለክተው ከጥፋቱ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ፣ ተከታታይና እያደገ/እየከበደ የሚሄድ የእርምጃ አወሳሰድ ሰርዓት ነው፡፡ ሳይታሰብበት በተለያዩ አጋጣሚዎች የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ ባልከፈለ/ች ተጠቃሚ ላይ ወዲያውኑ ቅጣት ማሳረፍ የሚያመጣው ውጤት ጥሩ ሊሆን ስለማይችል ተጠቃሚው ያልከፈለውንና ጊዜው ያለፈበትን የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ እንዲከፍል ግፊት ለማድረግ በጽሁፍ ማሳወቅ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ተጠቃሚው/ዋ ይህንን የጽሁፍ ማስታወቂያ ካልተቀበለ/ች፣ የአገልግሎት ክፍያው እየጨመረ የሚሄድ ይሆናል፡፡ ያልተከፈለን የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ እንዲከፈል ለማድረግ የመጨረሻ እርምጃ ክፍያው እስካልተከፈለ ድረስ ለሚያለማው መሬት የመስኖ ውሃ አገልግሎት መከልከል ሊሆን ይችላል፡፡ ሊታመን የሚችል ቅጣት፣ ቅጣት ሊታመን የሚችል መሆን አለበት፡፡ ማለትም አጥፊው በሚወሰደው ቅጣት ሊሰማው ወይም ተጽዕኖ ሊያሳድርበትና ሁሉም ተጠቃሚዎች ህጉን ካላከበሩ ቅጣቱ ተግባራዊ ሊሆን እነደሚችል ሊያውቁትና በእምነት ሊቀበሉት ይገባል፡፡