የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ ዕቅድ የናሙና ክፍሎች

የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ ዕቅድ. በመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ የተለያዩ ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን፤ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኞችን የማዘጋጀትና የማሰራጨት፣ የመሰብሰቢያ ጊዜውን /በአንድ ጊዜ ወይም የተወሰነ የክፍያ መጠን በተለያየ ጊዜ/፣ የተሰበሰበው የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ አመዘጋገብ እንዲሁም ክፍያውን ባልከፈሉ ተጠቃሚዎች ላይ ስለሚወሰድ እርምጃ ዕቅዱ ማመላከት አለበት፡፡ የመስኖ ውሃ አገልግሎት ክፍያ ለማሰባሰብ አደረጃጀቱ ምን ይሁን? የክፍያ ጊዜው የደረሰ የመስኖ ውሃ አገልግሎት መቸ መሰብሰብ አለበት? የሚሉትን ሁሉ መያዝ አለበት፡፡ የቋሚ እና ጊዜያዊ ሰራተኛ ወይም የጉልበት ሰራተኛ ቅጥር ዕቅድ ዓመታዊ የስራ ዕቅዱ ምን ዓይነት ጊዜያዊ እና/ወይም ቋሚ ሰራተኛ እና የጉልበት ሰራተኛ ይቀጠራል፣ ለምን ያህል ጊዜ፣ የደመወዙን ሁኔታ ጭምር በሚገልጽ አግባብ መዘጋጀት አለበት፡፡ የኢንቨስትመንት እና የግዥ ዕቅድ፤ ዓመታዊ ዕቅዱ በበጀት ዓመቱ ውስጥ ምን የቢሮ እቃዎች፣ መሳሪያዎች እና ወይም መሽነሪ ሊገዛ እንደሚችል እና/ወይም ምን ኪራይ መከራየት እንደሚገባ፣እንዲሁም ማኅበሩ የመስኖ አውታሩን አቅም ለማሻሻልና ለመሳደግ ምን የኢንቨስትመንት ስራዎች ይሰራል የሚሉትን መግለጽ አለበት፡፡ የምርጫ እና የሰልጠና ዕቅድ አዲስ የስራ አመራር ኮሚቴ እና/ወይም የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ምርጫ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት የሚካሄድ ከሆነ በዓመታዊ ዕቅዱ መመላከት ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አዲስ ለተመረጡ የስራ አመራር ኮሚቴ እና የቁጥጥር ኮሚቴ እና/ወይም ቅጥር ሰራተኞች ስልጠና የመስጠት አስፈላጊነት በዕቅዱ መካተት ይኖርበታል፡፡