የተግባራት አፈጻጸም ትንተና. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ2014 በጀት ዓመት የአስራ አንድ ወራት (ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም.) ያከናወናቸዉ የተለያዩ ተግባራት አፈጻጸም ዝርዝር በተለያዩ የስራ ክፍሎች ተከፋፍሎ እንደሚከተለው ቀርቧል። የእያንዳንዱን የስራ ክፍል የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ በማስከተል የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር በሠንጠረዥ ቀርቧል፡፡ ይህም ተሻሽሎ ከቀረበው የ2014 ዓመታዊ የድርጊት መርሃ-ግብር አንፃር የዕቅድ አፈጻጸም ንጽጽር ለማድርግ ያስችላል። ባለፉት አስራ አንድ ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
1.1 ባለመብቶች እና ሲቪል ማህበራት መብታቸውን ለማስከበር የሚያስችላቸው ዕውቀትና አቅም መገንባት 1.2 የጎለበተ የባለግዴታዎች የሰብአዊ መብቶች የማክበር፣ የመጠበቅና የማሟላት አቅምና ቁርጠኝነት