Consent and Release for Students to be Filmed/Phtographed/Interview and use of Image/Voice
Consent and Release for Students to be Filmed/Phtographed/Interview and use of Image/Voice
/School Work (Amharic)
ለትምህርት ቤት አገልግሎት፣ ተማሪዎች በፊልም እንዲቀርጹ/ፎቶግራፍ እንዲነሡ/ቃለ መጠይቅ እንዲሰጡ እና ለምስል/ለድምጽ አገልግሎት ተግባር መስማማት እና መፍቀድ
አኔ ከዚህ ቀጥየ፣ ለዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣ ለሠራተኞቹ እና ወኪሎቹ፣ የዲስርቲክት ኦፍ
ኮሎምቢያ፣ ለተኪዎቹ፣ እና ወኪሎቹ፣ የልጄን _ ምስሉን እና /ወይንም ድምፁን እንዲቀርጹ እንዲቀዱ፣ የኪነ ጥበብ ሥራውን
እና/ወይንም የጽfhፍ ሥራዎቹን በቪዲዮ እንዲቀዱ፣ በዲጅታል ሚዲያ እና በሌላም በኤልክትሮኒክስ ወይንም በኅትመት ሚዲያ እንዲቀርጹ ወይንም በማተሚያ እን ዲያትሙ እና እንዲህ ያለውንም ቀረጻ በራሳቸው ፍላጎት እና በሚፈቅዱትም መልክ እንዲያዘጋጁ ፈቃድ ሰጥቻለሁ። የጽfhፍ ፈቃድ ካልተስጠ በስተቀር የልጄ ሙሉ ስም፣ አድራሻው እና የሕይወት ታሪኩ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንደማይሆን እገነዘባለሁ።
በተጨማሪ የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ( ) እና የየዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ፣ ተተኪዎቻቸው እና ተመዳቢዎቻቸው፣ የልጄ ምስል እና/ ወይንም ድምጽፅ በኤንተርኔት፣ በአጫጭር በራሪ ጽfhፎች እና ቤሌሎችም የብዙኅን መገነኛ ዘዴዎች እንዲገለገሉበት፣ ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ፈቃድ ሰጥቻለሁ።
ከዚህ ቀጥየም ዲሲፒኤስ እና ሠራተኞቹ፣ ወኪሎቹ እንዲሁም የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ አስተዳደር፣ ተተኪዎቻቸው፣ እና ተመዳቢዎቻቸው ማንቸውም በሌ ምስል እና/ወይንም ድምፅ፣ የጥበብ ሥራዎች እና/ወይንም የጽfhፍ ሥራዎች፣ ከማናቸውም የይገባኛል ጥያቄዎች፣ ጥፋቶች፣ ወጭዎች፣ ክፍያዎች፣ እነም ሆንኩ ልጄ እነዚህን በሚመለከት ያሉንን ጥያቂዎች ከዚህ በኋላ ከተጠያቂነት ነጻ እናደርጋለን። ይህ ስምምነት እና ፈቃድ የመስጫ ቅጽ የተፈረመበት ዕማትን ተከትሎ በአለው የበጋ የትምህርት ወቅት ጊዜ ድረስ ዋጋ ይኖረዋል።
የዚህ መብት የመስጠት ተግባር፣ ሕጋዊ እና የጸና ስምምነት እንደሆነ እገነዘባለሁ። (አንዱ ላይ ምልክት ያድርጉ)
እስማማለሁ
አልስማማም
የተማሪው ስም፣ ያትሙ የወላጅ/ሕጋዊ አሳዳጊ ወይም ተማሪው (ጎልማሳ ከሆነ) ፊርማ ቀን
ለውትድርና መልማዬች መረጃዎች እንዳይሰጥ ለማገድ የመምረጥ አማራጭ መብት (ከ7–12 ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች)
እንደ ዲሲፒኤስ ያሉ፣ የክልል የትምህርት ወኪሎች ወይም (LEA)፣ ጥያቄዎች በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ የተማሪው ወላጅ/ሕጋዊ ሞግዚት (ወይም ለአቅመ አዳም የደረስ ተማሪ ከሆነ፣) የተማሪ መረጃዎች ይፋ እንዳይወጡ የሚፈልጉ መሆናቸውን አስቀድመው በጽfhፍ ያቀረቡ እስካልሆኑ ድረስ፣ ለውትድርና አገልግ ሎት መልማዮች፣ የሁለተኘ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሁሉ፣ ስም፣ አድራሻ፣ እና የስልክ ቁጥር እንዲሰጡ ፊድራላዊው ሕግ ያዛል። እንዲህ ዐይነቱ ቀደም ብሎ በወላጅ/ሕጋዊ ሞግዚት (ወይም ለአቅመ አዳም የደረሰ ተማሪ) የሚደረግ የመብት ማስገንዘብ ተግባር፣ በ 30 ቀናት ውስጥ መካሄድ ያለበት ሲሆን፣ ይህም ከዚህ በታች ተመለክቶ በቀረበው ተገቢነት ባለው አማራጭ ላይ ምልክት አድርጎ ከፈረሙበት በኋላ ቅጹን ለዲሲፒኤስ በማቅረብ ሊከናወን ይችላል።
እንደ ወላጅነቴ/ሕጋዊ አሳዳጊነቴ፣ ከዚህ በታች ስለተጠቀሰው ተማሪ፣ መረጃዎቹ ይፋ እንዲወጡ መፍቀዴን ለብቻ በጽfhፍ የገለጽኩ ካልሆነ በስ ተቀር፣ ዲሲፒኤስ፣ የልጄን ስም፣ አድራሻ፣ እና የስልክ ቁጥር፣ ለጦር ኃይሎች አገልግሎቶች፣ ለውትድርና መልማዬች፣ ለአገልግሎት አካዳሚዎች ወይም ለውትድርና ትምህርት ቤቶች የተማሪው መረጃ እንዳይሰጥ እጠይቃለሁ።
አቅመ እዳም እንደደረሰ (18 ዓመት እድሜ እንደሞላው) ተማሪ፣ መረጃዎች እንዲሰጡ ለብቻ የስምምነት ፈቃድ ካልሰጠሁ በስተቀር፣ ዲሲፒኤስ ለጦር ኃይሎች አገልግሎቶች፣ ለውትድርና መልማዬች፣ ለአገ ልግሎቶች፣ ለአገልግሎት አካዳሚዎች ወይም ለውትድርና ትምህርት ቤቶች የተማሪው መረጃ እንዳይሰጥ እጠይቃለሁ።
የተማሪው ስም፣ ያትሙ የወላጅ/ሕጋዊ አሳዳጊ ወይም ተማሪው (ጎልማሳ ከሆነ) ፊርማ ቀን
መድልዎ አልባ ማስታወቂያ። በስቴት እና በፌድራል ሕጎች መሠረት፣ የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ይሆናል ተብሎ በሚገመት በዘር፣ በቀለም፣ በሀይማኖት ወይንም በእምነት፣ የመጡበትን ብሄር፣ ጾታን፣ እድሜን፣ ትዳር መያዝ አለመያዝን፣ የጾታ ፍላጎት ዝንባሌን፣ ወይም ለመሆን የሚፈልጉትን የጾታ ምርጫ ዝንባሌን፣ ገጽታን ወይንም መልክን፣ በቤተሰብ ውስጥ ያለውን ይዞታዊ አቋምን፣ በቤተሰብ ኃላፊነት መያዝ ያለመያዝን፣ የትምህርት ደረጃን፣ የፖለቲካ አቋም እና ዝንባሌን፣ የዘር መረጃን፣ የሆነ እክልን (Disabilities)፣ የገቢ ምንጭን፣ በቤ
ተሰብ ውስጥ በሚፈጠር የእርስ በእርስ አለመግባባት ምክንያት ተጠቂ ሆኖ መገኘትን፣ ለመኖሪያነት በሚመርጡት ክልል ወይም ለኑሮ በሚመረጥ የሥራ ዐይነት፣ መድልዎ አያደርግም። ስለዚህ
ደንብ ሙሉ ይዘት እና ተጨማሪ መረጃ xxxx://xxxx.xx.xxx/xxx-xxxxxxxxxxxxxx.xxx።