ሐምሌ 22 ቀን 2AAA ዓ.ም. ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ
ሐምሌ 22 ቀን 2AAA ዓ.ም. ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ
Aቶ ሐጎስ ወልዱ ወ/ት ሒሩት መለሠ Aቶ መድሕን ኪሮስ Aቶ ፀጋዬ Aስማማው
Aመልካች፡- የIትዮጵያ መድን ድርጅት - Aትናቦን ነጋሳ ቀረበ፡፡ ተጠሪ፡- መኮንን መስፍን ከጠበቃ በሻዳ ገመቹ ጋር ቀረበ፡፡
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
ጉዳዩ የመድን ዋስትና ውልን መነሻ ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡ ከሣሽ የነበረው የAሁኑ ተጠሪ በAመልካች ላይ ክስ የመሠረተው ተከሣሽ የመድን ዋስትና የገባለት የሠ.ቁ. 3-282A4 A.A. የሆነ መኪናዬ በመገልበጥ ምክንያት ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ተከሣሽም በገባው ግዴታ መሠረት ከወደቀበት ቦታ Aስጎትቶ በማምጣት በሪከቨሪ ክፈሉ ያስገባው ቢሆንም፤ በመጨረሻ ግን ሊያስጠግንልኝ Aልቻለም፡፡ ስለዚህ በገባው የውል ግዴታ መሠረት መኪናውን Aስጠግኖ Eንዲያስረክበኝ ወይም የመኪናውን ሙሉ ዋጋ Eንዲከፍለኝ መኪናው የንግድ መኪና በመሆኑ Eና ተከሣሽም በተገቢው ጊዜ ለመጠገን ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ የተቋረጠ ጥቅም ታስቦ Eንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ነው፡፡ Aመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ የመድን ዋስትና ውል መግባቴ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን መኪናው የተገለበጠው በውሉ የተደረገውን ስምምነት በመጣስ ተሳቢ ሲጎትት በነበረበት ጊዜ በመሆኑ
ኃላፊነት የለብኝም፡፡ የመድን ዋስትና ውሉ የተቋረጠ ገቢ Eንዳይጠየቅ የሚከለክል በመሆኑ የተቋረጠ ጥቅምን በሚመልከት የቀረበው ክስ
ተቀባይነት የለውም፡፡ በተቋረጠ ጥቅም ስም የተጠየቀው የገንዘብ መጠንም የተጋነነ ነው በማለት ተከራክሮAል፡፡ ክሱን ያስተናገደው ፍ/ቤትም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ተከሳሽ በገባው ውል መሠረት የደረሰውን ጉዳት የመካስ ኃላፊነት Aለበት፡፡ ስለዚህ መኪናውን Aስጠግኖ ወደነበረበት በመመለስ ለከሣሽ ያስረክብ፣ በገባው የውል ግዴታ መሠረት መኪናውን ለማስጠገን ፈቃደኛ ባለመሆኑ የተቋረጠውን ጥቅም ብር 56,3AA ይክፈል
በማለት ወስኖAል፡፡ ከዚህ በኋላ መጀመሪያ Aመልካች ውሣኔውን በመቃወም
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ ተጠሪም በበኩሉ በተቋረጠ ጥቅም ስም የተወሰነው ገንዘብ AንሶAል በሚል መስቀለኛ ይግባኝ AቅርቦAል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በሁለቱም በኩል የቀረቡትን ይግባኞች መሠረት በማድረግ ክርክሩን ሰምቶAል፡፡ በመጨረሻም Aመልካች የደረሰውን ጉዳት የመካስ ኃላፊነት Aለበት፡፡ በመሆኑም መኪናውን Aስጠግኖ ለተጠሪ ያስረክብ፡፡ Eንደዚሁም ተቋረጠውን ገቢ ብር 275,AAA ይክፈል በማለት ወስኖAል፡፡ የAሁኑ የሰበር Aቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው፡፡
Eኛም Aመልካች ኀዳር 18 ቀን 1999 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን Aቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪን Aስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል፡፡ Aቤቱታው በሰበር ችሎት Eንዲታይ የተወሰነው Aመልካች ለደረሰው ጉዳት ኃላፊ በመደረጉም ሆነ የተቋረጠ ጥቅም Eንዲከፍል የተሰጠውን ውሣኔ የሕግ Aግባብ ለመመርመር ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ Aቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ Eና ከሕጉ ጋር Aገናዝበን መርምረናል፡፡
በAመልካች Eና በተጠሪ መካከል የመድን ዋስትና ውል ስለመኖሩ Aላከራከረም፡፡ ዋስትና የተገባለት መኪና በስራ ላይ Eንዳለ መገልበጡንና በዚህ የመገልበጥ Aደጋ የተነሣም ጉዳት የደረሰበት መሆኑም Aከራካሪ
Aይደለም፡፡ Aመልካች ውሉን መሠረት በማድረግ መኪናውን ከወደቀበት ቦታ Aስጎትቶ በማምጣት ወደ ረከቨሪ ክፍሉ ካስገባው በኋላ ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት የለብኝም በማለት ነው ወደ ክርክር የገባው፡፡ ክርክሩን በየደረጃቸው
የሰሙት የስር ፍ/ቤቶችም Aመልካች ኃላፊነት የለብኝም ለማለት በመከራከሪያነት ያነሳውን ነጥብ Eግምት ውስጥ በማግባት ክርክሩን ከመምራታቸውም በላይ፣ በግራ ቀኝ ወገኖች በኩል የተቆጠሩትን
ማስረጃዎችንም ሰምተዋል፡፡ በመጨረሻም ማስረጃዎቹን በማመዛዘን በተሻለ ሁኔታ ያስረዳው ተጠሪ Eንደሆነ በመገንዘባቸው የAመልካችን ክርክር ውድቅ Aድርገዋል፡፡ Aመልካች የደረሰውን ጉዳት የመካስ ኃላፊነት Eንዳለበትም
Aረጋግጠዋል፡፡
Eንደምንመለከተው Aመልካች ኃለፊነት የለብኝም ለማለት በመከራከሪያነት ያነሳው ነጥብ በግራ ቀኝ ወገኖች ከቀረበው ማስረጃ Aንፃር ታይቶ Eና ማስረጃውም ተመዝኖ Eልባት AግኝቶAል፡፡ የሰበር ችሎት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጡትን ውሣኔዎች Aግባባነት ሊመረምር የሚችለው በሕግ Aተረጓጎም ረገድ መሠረታዊ ስህተት Aለ ሲባል ነው፡፡ በያዝነው ጉዳይ Eንደምናየው ግን Aመልካች ያቀረበው Aቤቱታ በማስረጃ Aመዛዘን ረገድ ስህተት ተፈጽሞAል ከሚል ያለፈ Aይደለም፡፡ በመሆኑም ከፍ ሲል በሰጠነው ምክንያት የምንመረምረው ሆኖ Aላገኘነውም፡፡ በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለትም Aልቻልንም፡፡
ከዚህ በመቀጠል የመረመርነው ተጠሪ በክሱ ከጠየቀው ገንዘብ በላይ Eንዲከፈለው ተወስኖለታል በማለት Aመልካች ያቀረበውን Aቤቱታ ነው፡፡ ተጠሪ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው የክስ ማመልከቻ የተቋረጠ ጥቅም በማለት Eንዲከፈለው የጠየቀው ገንዘብ ብር 13A,4AA
/Aንድ መቶ ሰላሳ ሺህ Aራት መቶ ብር/ Eንደነበር ከመዝገቡ Aረጋግጠናል፡፡ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ይህን መነሻ በማድረግ Eና የመኪናው
የዓመት ገቢ ነው ያለውን መጠን Eግምት ውስጥ በማግባት Aስልቶ የተጠየቀው ብር 13A,4AA ያነሰ ገንዘብ Eንዲከፈል ወስኖAል፡፡ ተጠሪም
በክሱ የጠየቀውን የገንዘብ መጠን ሳይለውጥ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የወሰነው ገንዘብ Aንሶኛል በማለት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ AቅርቦAል፡፡ በመሆኑም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ገንዘቡ ያንሳል ወይስ
Aያንስም የሚል ጭብጥ በመያዝ በEርግጥ ተጠሪ ከመኪናው በዓመት
የሚያገኘው ገቢ ወይም ጥቅም ምን ያሕል Eንደሆነ ለማጣራት በራሱ በኩል ማጣራቱና ማስረጃም መስማቱ ትክክል ነው፡፡ በዚህ ረገድ ፍ/ቤቱ ስህተት ፈጥሮAል ማለት የሚቻለው ተጠሪ ከጠየቀው በላይ ገንዘቡን ወደ ብር 275,AAA ከፍ Aድርጎ በመወሰኑ ነው፡፡ በመሆኑም ይህኛውን የውሣኔው ክፍል ሊታረም የሚገባው ሆኖ Aግኝተነዋል፡፡
በመጨረሻም የመድን ዋስትና ውሉ የተቋረጠ ጥቅም Eንዳይጠይቅ ይከለክላል የሚለውን የAመልካች ክርክር ተመልክተናል፡፡ በEርግጥ በውሉ ላይ ይህን መሰል ስምምነት ስለመደረጉ የተካደ Aይደለም፡፡ ነገር ግን Aመልካች መኪናውን Aስጎትቶ ካመጣና Aስጠግናለሁ በሚል Eሳቤ ሪከቨሪ ክፍሉ Aስገብቶ ከቆየ በኋላ ለማስጠገን ፈቃደኛ Aይደለሁም በማለቱ ተጠሪ ወደ ክስ Eንዲያመራ Aስገድዶታል፡፡ መኪናው በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ በመሆኑ በመቆሙ ምክንያት በተጠሪ ላይ ከፍተኛ ኪሣራ Eንደሚደርስ የሚያከራክር Aይደለም፡፡ Aንድ ተዋዋይ ወገን Eንደ ውሉ ሳይፈጽም ቢቀርና
በዚህ ምክንያትም በሌላኛው ተዋዋይ ወገን ላይ ጉዳት ቢደርስ የመካስ ኃላፊነት Eንዳለበት በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1771/2/ የተቀመጠው ድንጋጌ በግልጽ ያመለክታል፡፡ በያዝነው ጉዳይ Eንደምናየው Aመልካች Eንደ ውሉ ለመፈጸም
ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ በተጠሪ ላይ ጉዳት Eንዲደርስ ምክንያት ሆኖAል፡፡
ከዚህ የተነሣም Eንደ ውሉ ይፈጽማል የሚል ግምት ተይዞ የተቀመጠውን የውሉን Aንድ Aንቀጽ በመጠቀም ኪሣራውን ከመክፈል ነፃ ሊሆን የሚችልበት የሕግ ምክንያት የለም፡፡ በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት