ይህ በጀት MCPSን ቀጣይ እድገቱን ለማሰተዳደር ፣ ማስተመርንና መማርን ለማሻሻል፣ የግኝት ክፍተትን ለማጥበብ፣ እና ተማሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ለሚጠበቅባቸው ለማዘጋጀት ስልታዊ የሙአለንዋይ ፈሰስ ለማድረግ ያስችለዋል።
የትህርት ቦርድ የ2015 በጀት ዘመን የስራ ማስኬጃ በጀት አፀደቀ
የMontgomery County ትምህርት ቦርድ ለMCPS $2.28 ቢልዮን የስራ ማስኬጃ በጀት ለ2015 በጀት ዘመን ጁን 17 ላይ አፀደቀ። የ2015 በጀት ዘመን በጀት ካለፈው የበጀት ዘመን የ2.3 በመቶ—ወደ $51.3 ሚልዮን አካባቢ—ጭማሪ ሆኖ ይገኛል።
ይህ በጀት MCPSን ቀጣይ እድገቱን ለማሰተዳደር ፣ ማስተመርንና መማርን ለማሻሻል፣ የግኝት ክፍተትን ለማጥበብ፣ እና ተማሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ለሚጠበቅባቸው ለማዘጋጀት ስልታዊ የሙአለንዋይ ፈሰስ ለማድረግ ያስችለዋል።
በፌብሩዋሪ ወር፣ ቦርዱ የ$2.32 ቢልዮን በጀት—የ4 በመቶ እድገት ከአሁኑ በጀት— ጠይቆ ነበር። በሜይ ወር፣ የMontgomery County ምክር ቤት ከትምህርት ቦርድና ከSuperintendent Xxxxxx X. Xxxxx ጋር በመሆን የ$2.28 ቢልዮን በጀት ለማቅረብ ስምምነት ላይ ተደረሰ። ለትምህርት ስርአት መንቀሳቀሻ እጥረት ለመሸፈን ምክር ቤቱ ከመጠባበቂያ ፈንድ/ካዝና ይጠቀማል። ስምምነቱ ለወደፊት የMCPS ለጡረተኛ ጥቅሞች የሚውል በግምት $27 ሚልዮን ከመጠባበቂያ ካዝና ይወስድና ወደሚመጣው አመት የስራ ማስኬጃ በጀት ያውለዋል። እነዚህ ገንዘቦች ከዲስርትሪክቱ ጠቅላላ አገልገሎት ገንዘብና ከጤና እንክብካቤ ሂሳቦች ጋር ይደማራል/ይቀላቀላል።
አብዛኛው በጀት እያደገ በመሄድ ላይ የሚገኘውን የተማሪዎች ቁጥር የሚሰጠውን የአገልግሎቶች ደረጃ ለመጠበቅ MCPSን ያስችለዋል ተቀጣይ የመካካሻና የጥቅማጥቅሞች ውጭዎችንም ይሸፍናል። የተማሪ ድጋፍ አገልግሎቶች ለማሻሻል የሚያስፈልጉ ገንዘቦች፣ ተክኖሎጂን ለመጨመር፣ የማህበረሰብ ሽርክናዎች ለማሳደግ፣ እና የመምህር አመራር ለማስፋፋት፣ በስልታዊ ማሻሻያነት በጀቱ $12.5 ሚሊዮን አካቷል። ከእነዚህ የሙአለንዋይ ፈሰሶች አብዛኛዎቹ በንባብና በሂሳብ የመማርያ ክፍሎችን መጠን ለመቀነስ 15 የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት Focus መምህራን መጨመር፤ በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዎች የሚሰጡትን አገልግሎቶች ለማሻሻል፤ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ተማሪዎች
ለማገልገል ሁለት ቅድመ-ሙአለህፃናት ክፍሎች መጨመርን በመሳሰሉ የግኝት ክፍተትን በማጥበብ ላይ በቀጥታ የሚያተኩሩ ናቸው።
በተጨማሪ በጀቱ ከፍተኛ ችግር ወዳላቸው ለመዘዋወር ወይም እዚያው ለመቀጠል ለሚፈልጉ ውጤታማ መምህራን እገዛዎች በሚያቀርበው “Career Lattice” የተባለውን አዲሱን ፕሮግራም ማካሄጃ ገንዘብ ያቀርባል። ይህ ረጅም ተሞክሮ ያላቸውን መምህራን እውቅና ለመስጠትና በመምህር አመራር ቦታዎች ለማስቀመጥ አንድ እድል ነው።
በ2016 በጀት ዘመን፣ የዲስትሪክቱን ተከታታይ ሀላፊነቶች ለመወጣት፣ ከእድገቱ ጋር ኣብሮ ለመጓዝ፣ እና MCPS የግኝት ክፍተተን እንዲዘጋ በሚያግዙ ስልቶች ሙአለንዋይ ፈሰስ ማድረግ ለመቀጠል በሚመጣው አመት የተደረጉ ያንድ ገዜ ወጭዎች ለመተካት፣ MCPS ቢያስ ቢያንስ $135 ሚልዮን እንደሚያስፈልገው ይጠብቃል/ይገምታል።
ለ2014-2015 MCPS የመጠባበቂያ ቀን መቁጠርያ ይከተላል
በ2014-2015 የትምህርት አመት በአስችኳይ ሁኔታ ት/ቤቶች ለተዘጉባቸው የትምህርት ቀኖች MCPS መተኪያ እንዲያደርግ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ MCPS ለ2014-2015 የተፈቀደውን የመጠባበቂያ ቀን መቁጠርያ ይከተላል።
በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምርያ ማስወገጃ ካልተሰጠ በስተቀር፣ MCPS በትምህርት አመቱ ማብቂያ ላይ ቀኖች ይጨምራል። MCPS በበአላት አይከፍትም፣ የስፕሪንግ እረፍት አይቀንስም ወይም በድርድር ስምምነት የተደረሰባቸው የባለሙያ ቀኖችን አይሰርዝም።
የትምህርት ቦርድ የ2014–2015 የት/ቤት ቀን መቁጠርያን ኖቨምበር 12 2013 አፀደቀ፤ ይህም የተመሰረተው በ184 የተማሪዎች መማርያ ቀኖችና ለመምህራን በ193 ቀኖች ነው።
የመጠባበቂያ ፕላኑ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዝግ ቀኖች ከአራት ቀኖች በላይ ከሆኑ መቼ መተካት እንዳለባቸው የሚያመለክትው፣ እንደሚከተለው ነው፡- የትምህርት አመቱ በአስቸኳይ ሁኔታ ምክንያት ቢደናቀፍና ት/ቤቶች—
• 5 ቀኖች ቢዘጉ—የትምህርት አመቱ በአንድ ቀን ወደ ሰኞ፣ ጁን 15 2015
ይራዘማል፤
• 6 ቀኖች ቢዘጉ—የትምህርት አመቱ በሁለት ቀኖች ወደ ጁን 15 እና ጁን 16 2015 ይራዘማል፤
• 7 ቀኖች ቢዘጉ—የትምህርት አመቱ በሶስት ቀኖች ወደ ጁን 15፣ 16 እና 17 2015
ይራዘማል፤
• 8 ቀኖች ቢዘጉ—የትምህርት አመቱ በአራት ቀኖች ወደ ጁን 15፣ 16፣ 17 እና 18 2015 ይራዘማል፤
• 9 ቀኖች ቢዘጉ—የትምህርት አመቱ በአምስት ቀኖች ወደ ጁን 15፣ 16፣ 17፣ 18
እና 19 2015 ይራዘማል፤ የትምህርት አመት ቀን መቁጠርያ
በደውል ቀኖች በቀረቡ የለውጥ ሀሳቦች Superintendent ላለመግፋት ያሳስባል
Superintendent Xxxxxx X. Xxxxx ስለ ትምህርት መስጫ መጀመርያና መዝጊያ ሰአቶች፣ የደውል ሰአቶችም ተብለው የሚጠሩት፣ በቀረቡት ለውጦች፣ እነሱን በተግባር ላይ ለማዋል ከ$20 ሚልዮን በላይ ወጪ እንደሚጠይቅና ከህብረተሰቡም የተምታታ አስተያየት በመቅረብ ላይ መሆኑን በመጥቀስ፣ MCPS እንዳይገፋባቸው ሀሳብ በማቅረብ ላይ ይገኛል። ምንም እንኳን ለ2016 በጀት ዘመን በዲሰምበር ባቀረበው ሀሳብ የስራ ማስኬጃ በጀት ተጨማሪ ገንዘብ ለመያዝ እቅድ ባይኖረውም፣ Xx. Xxxxx ጉዳዩን ወደፊት ተመልሶ የመመልከት ሁኔታን ክፍት አድርጎታል።
ጁን 17፣ የትምህርት ቦርድ Xx. Xxxxx የደወል ሰአቶችን ለመለወጥ አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ አማራጮች እንዲያዳብርና የተከለሱት አማራጮች ለ2016 በጀት ዘመን የስራ ማስኬጃ በጀት ጥያቄ ውይይት ወቅት እንዲደርሱ እንዲያደርግ ጠይቆታል።
ባለፈው ኦክቶበር፣ MCPS የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መጀመርያ ሰአት 50 ደቂቃዎች ዘግይቶ እንዲጀምር፣ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች 10 ደቂቃዎች ወደፊት እንዲያሸገሽግ፣ እና የኤሌሜንታሪ ት/ቤት በ30 ደቂቃዎች እንዲራዘም Xx. Xxxxx አሳስቦ ነበር። ይህ ሀሳብ የተመሰረተው፣ የትምህርት መጀመርያ ሰአቶች፣ በተለይም በ2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በተማሪዎች ጤናና አጠቃላይ ደህንነት ያለውን ተፅእኖ ባጠናው፣ በ2013 Bell Times Work Group (የደወል ሰአቶች የስራ ጓድ) ዘገባ መሰረት ነበር።
Xx. Xxxxx የMCPS ሰራተኞች በቀረበው ህሳብ የህዝቡን አስተያየት እንዲሰበስቡና ወጪዎችንና በስራ አፈፃፀም የሚኖረውን ተፅእኖ በጥልቅ እንዲያመዛዝኑ ጠይቋል። በተጨማሪም አንድ ቡድን በኤሌሜንታሪ ት/ቤት ተጨማሪዎቹ 30 ደቂቃዎች ምን አገልግሎት ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ እንዲያጠና ጠየቀ።
ጁን 10 ቀን፣ Xx. Xxxxx በሺዎች ከሚቆጠሩ የማህበረሰብ አባላት ስፋት ያለው አስተያየት አጭር ጥንቅር እና የቀረበው ሀሳብ ሊያስከትል የሚችለው የመጓጓዣ፣ መብራትና ውሀ የመሳሰሉ አገልግሎቶች እና የሰራተኛ ወጭዎችን ያካተተ ዘገባ ይፋ አደረገ።
ከኦክቶበር እስከ አፕረል ድረስ፣ MCPS ስለ ቀረበው የደወል ሰአቶች በሺዎች ከሚቆጠሩ የMCPS ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ወላጆች፣ እና የማህበረሰብ አባላት አስተያየቶች ሰበሰበ። የህዝብ አስተያየት በተለያየ መንገድ ነው የተሰበሰበው፣ ከእነዚህም፡-
• 676 ሰዎች የተሳተፉባቸው አራት የማህበረሰብ መድረኮች እና ሌሎች በሰራተኞች የተመሩ 960 ሰዎች በተጨማሪ የተገኙባቸው ውይይቶች፤
• በ15,300 ላልጆች፣ ከ45,000 በላይ ተማሪዎች፣ እና 15,000 ሊደርሱ በሚችሉ ሰራተኞች የተሞሉ መጠይቆች፤
• ሰባሰባት "ጎረቤት ለጎረቤት" የውይይት ቡድኖች፤ እና
• በMCPS የደወል ሰአቶች መክተቻ ሳጥኖች የተላኩ ከ740 በላይ ኢሜይሎች።
የMCPS ማህበረሰብ ስለቀረበው ሀሳብ አንድ ብቸኛ የሆነ አስተያየት አልነበረውም። ወላጆች ከሁሉም በላይ ሀሳቡን ወደውት ነበር፣ በጥናቱ ከተሳተፉት 78 በመቶዎቹ በDr. Starr የቀረበውን ሀሳብ ደግፈዋል። ቢሆንም፣ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች (50 በመቶ) እና ሰራተኞች (51 በመቶ) በሀሳቡ ላይ እኩል በእኩል ተከፋፍለዋል። የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች (70 በመቶ) እና ሰራተኞች (65 በመቶ) ሀሰቡን ወደውታል። ቢሆንም የኤሌሜንታሪ ት/ቤት ተማሪዎች 30 በመቶ እና ሰራተኞች 30 በመቶ ብቻ የሰአት ሽግሽጉን ሲደግፉ አብዛኛዎች ተማሪዎችና ሰራተኞች የደወል ሰአቶችን ለውጥ ተቃውመዋል።
የት/ቤት አውቶቡሶች ዙራቸውን ለማከናወን በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው ታስቦ የኤሌሜንታሪ ት/ቤት የትምህርት ቀን በ30 ደቂቃ የማራዘሙ ጉዳይም ትርጉም ያለው ቅሬታም አስከትሎ ነበር። የኤሌሜንታሪ የትምህርት ቀን ቢራዘም ኖሮ፣ ተማሪዎች እረፍት ወይም ተጨማሪ መዝናኛ ጊዜ፣ የአካል ማጠንከርያ፣ ወይም ለኪነጥበባት ጊዜ ይኖራቸዋ የሚል ሀይለኛ አስተሳሰብ ነበር።
ለተጨማሪ መጓጓዣ፣ ሰራተኞች አና የአገልግሎት ወጪዎች የቀረቡት ለውጦች ቢያንስ
$21.5 ሚሊዮን በየአመቱ እንደሚያስወጡ ዘገባው ያመለክታል። ይህ 57 መደበኛ የት/ቤት አውቶቡሶችንና የልዩ ትምህርት ተማሪዎችና የማግኔት ፕሮግራም ተከታታዮችን የሚያገልግሉ 96 ተጨማሪ አውቶቡሶች መግዣና ማንቀሳቀሻ $12.9 ሚልዮንን ያካትታል።
በኤሌሜንታሪ የትምህርት ቀን 30 ደቂቃ መጨመር የሚያስከትለው ወጪ መጠን ከሰአት አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ነው። ለምሳሌ፣ ለኪነጥበብ፣ ሙዚቃ እና/ወይም የአካል ማጠንከርያ ትምህርት ክፍሎች መጨመር በአመት በግምት $46 ሚልዮን የሚያስወጡ ሲሆን፣ የእረፍት ወይም የምሳ ጊዜ ማራዘም በአመት $8 ሚሊዮን ያስወጣል።
Xx. Xxxxx በMCPS የተማሪ ምዝገባ በአመት በ2,500 ተማሪዎች የሚያድግ መሆኑን፣ እናም ስኬትን ለማረጋገጥ በየአመቱ ተጨማሪ ተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፎችና አገልግሎቶች ይፈልጋሉ ብሏል። በዚያው ደረጃ አገልግሎቶች በማደግ ላይ የሚገኝ የተማሪዎች ቁጥር አሁን ባለበት ደረጃ አገልግሎቶች ለማቅረብ ብቻ ተጨማሪ መገልገያዎች ይጠይቃል እናም አዳዲስ ሀሳቦችን ለማስተናገድ የገንዘብ መጠንንም ውሱን ያደርጋል። ለምሳሌ፣ የ2015 በጀት ዘመን በጀት የግኝት ክፍተትን ጥያቄ የመግጠም አዲስ ሀሳቦች እና መምህራንና ተማሪዎችን ለአዲስ ስርአተ ትምህርትና አዳዲስ ግምገማዎች ለማዘጋጀት $12.5 ሚሊዮን ብቻ አካትቷል።።
የ2015 በጀት ዘመን በጀትን ለመደጎም የካውንቲው ምክር ቤት የተጠቀመበትን የአንድ ጊዜ ወጪ ለመተካት፣ የዲስትሪክቱን ተከታይ ግዴታዎች ለመወጣት፣ እና ዲስትሪክቱ የግኝት ክፍተትን ለመዝጋት በሚያግዘው ስልቶች የሙአለንዋይ ፈሰስ ለማድረግ MCPS በ2015 በጀት ዘመን የስራ ማስኬጃ በጀት ቢያንስ $15 ሚልዮን ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ከአሁኑ እንደደረሰበት Xx. Xxxxx አመለከተ።
$340 ሚልዮን እናም ይቀጥላል፡- የ2014 ተመራቂዎች አዲስ ክብረወሰን አስመዘገቡ
የMontgomery County Public Schools (MCPS) የ2014 ተመራቂዎች ብዙ ነገሮች አሏቸው።
የ2014 ተመራቂዎች እስካሁን የ$338.9 ሚልዮን የኮሌጅ ስኮላርሺፖች አግኝተዋል—ይህም ካለፈው አመት የ$40 ሚልዮን ጭማሪ ነው። ተጨማሪ መረጃ እንደተገኘ የስኮላርሺፖች ጠቅላላ መጠን በሚመጡት ሳምንቶች እንደሚያድግ ይጠበቃል።
የ2014 ተመራቂ አባሎች ለግንባር ቀደም አካዴሚያዊ አፈፃፀምና የማህበረሰብ ተሳትፎ በርካታ የላቁ ስኮላርሺፖች ተቀብለዋል። MCPS የዩ.ኤስ. ፕረዚደንታዊ ምሁር ተብለው ከተሰየሙት ከሁለት የሜሪላንድ ተማሪዎች አንዱ፤ አምስት ተማሪዎች good-through-
graduation ከBill and Xxxxxxx Xxxxx Foundation ተቀበሉ19 ተማሪዎች የተሟላ የPosse ስኮላርሺፖች ተቀበሉ፣ እናም 163 ተማሪዎች የNational Merit ስኮላርሺፖች የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ሆነው ተሰየሙ።
የ2014 ተመራቂዎች ተጨማሪ ፍፃሜዎች አሏቸው። ከነዚህም ውስጥ፡-
- 49 የNational Merit ስኮላርሺፕ አሸናፊዎች
- 42 የNational Hispanic Recognition የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች
- 7 የNational Achievement (ብሄራዊ ግኝት) ስኮላርሺፕ አሸናፊዎች
-193 በIvy League ት/ቤቶች ተቀባይነት
የMCPS የኮሌጅ ምዝገባ መጠን ከስቴት ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ነው።
የMCPS ተመራቂዎች 80 በመቶ የሚደርሱ ከተመረቁ በ16 ወራት ውስጥ ኮሌጅ እንደሚመዘገቡ—በሜሪላንድ ስቴት ውስጥ ሁለተኛው ከፍተኛ—መሆኑን የስቴት መረጃዎች ያሳያሉ።
ለMCPS ተመራቂዎች በ2012 የ16-ወር ምዝገባ መጠን 18.4 በመቶ ነው፣ ይህም ከስቴቱ በስምንት ነጥቦች ከፍ ያለ ነው - በሜሪላንድ ረፖርት ካርድ ድርጣብያ xxx.xxxxxxxxxxxx.xxx በሚገኘው የኮሌጅ ምዝገባ አሀዞች መሰረት።
ሶስት ሩቦች የሚደርሱ አፍሪካዊ አሜሪካዊ የMCPS ተመራቂዎች (74.8 በመቶ) ከተመረቁ በ16 ወሮች ውስጥ ኮሌጅ ይመዘገባሉ፣ እና የሂስፓኒክ ተማሪዎች ደሞ 62.8 በመቶ። እነዚህ መጠኖች ከሜሪላንድ ስቴት በላይ ሲሆኑ፣ ነጭ (86 በመቶ) ወይም ኢሲያዊ (84.6 በመቶ) ስለሆኑ የMCPS ተማሪዎች ጋር ሲወዳደሩ ዝቅተኛ ናቸው።
በሜሪላንድ 16-ወር ኮሌጅ ምዝገባ MCPS ልዩ ትምህርት አገልገሎት የሚያገኙ ተማሪዎች (60.6 በመቶ) አንደኛ ደረጃ እና ነፃ- ና የቅናሽ-ዋጋ ምግብ አገልግሎቶች ለሚያገኙ (65.3 መቶ) ሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ ይዞ ይገኛል።
Xx. Xxxxx የኮሌጅ ምዝገባ አሀዞች የሚያደፋፍሩ መሆናቸውን ገልፆ፣ ነገር ግን በምዝገባ አሀዞች ክፍተት እንዳለ እና ዲግሪ የሚያገኙት ሁሉም ተማሪዎች አለመሆናቸውን እውቅና ሰጠ። በአንድ የMCPS ዘገባ መሰረት፣ ኮሌጅ ከተመዘገቡት የዲስትሪክቱ ምሩቃን ውስጥ ሁለት ሲሶዎቹ በስድስት አመቶች ውስጥ ዲግሪ ያገኛሉ።
ጡረተኞቻችንን ማክበር
የትምህርት ቦርድ እና Superintendent Xxxxx ጁን 5 በተከበረው አመታዊ የጡረታ እውቅናና ግብዣ 518 ጡረተኞችን አክብረዋል። ለMCPS ተማሪዎች ባደረጉት መስዋእትነት የተሞላው አገልግሎት ለማመስገን የአድናቆት የምስክር ወረቀቶች ለጡረተኞቹ ተሰጥቷል። የ2014 ጡረተኞች ዝርዝር ተመልከቱ። ዝርዝሩ የጡረተኛውን ስም፣ የመጨረሻ ስራ መደብ እና የMCPS አገልግሎት አመቶችን ያካትታል።
አምስት ጡረተኞች በBulletin፣ የMCPS ሰራተኞች ዜና መፅሄት የማይረሱ ተሞክሮዎችን፣ የወደፊት ፕላኖችናና የምክር ቃላት አጋሩ። ቃለ-መጥይቆቻቸውን እዚህ ያንብቡ።
የሂሳብ ትምህርትን አፈፃፀም ለማሻሻል Superintendent ፕላን አቀረበ
የተማሪዎችን አፈፃፀም በሂሳብ ለማሻሻልና በዚህ አይነተኛ አካባቢ በእንጥልጥል የሚገኘው የግኝት ክፍተትን ለመጋፈጥ Superintendent Xxxxxx Xxxxx xx xxxx-ነጥብ ፕላን እያቀረበ ነው። የሱ ፕላን በአገር አቀፍ የሂሳብ ፈተናዎች የተማሪዎችን አፈፃፀም ጉዳይ ሲያጠና የነበረ የስራ ቡድን ግኝቶች ምላሽ ነው። የMCPS Semester Exam Work Group (የግማሽ አመት ፈተና የስራ ቡድን) ስብሰባ የጀመረው ባለፈው አመት ሲሆን የሚያካትተውም ወላጆች፣ መምህራን፣ ርእሰ-መምህራን፣ አስተዳዳሪዎች፣ የማህበረሰብ አባላት፣ እና ሌሎችን ነው። ቡድኑ በካውንቲ-አቀፍ የ2ኛ ደረጃ የግማሽ አመት ፈተናዎች በተማሪዎች አፈፃፀም ላይ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ታሳቢዎችን እንዲያገናዝብ Dr. Star ጠየቀ።
የስራ ቡድኑ ጉዳዮችን አገናዝቦ በተለያዩ ቁልፍ መስኮች—የስርአተ-ትምህርት አቅጣጫና የፈተና ይዘት፤ የትምህርት ሰአትን በላቀ ሁኔታ መጠቀም፤ የኮርስ ዝግጁነት፣ አማራጮች፣ እና አመዳደብ፤ የአቋም ግምገማዎች፤ እና የመጨረሻ ፈተናዎች አላማና ክብደት—የውሳኔ ሀሳቦችን አቀረበ። ስለ ሂሳብ አፈፃፀም ቅሬታዎችና የግኝት ክፍተቶችን ስለማጥበብ የትምህርት አመቱን በሞላ ስራ ተሰርቷል። ያን ስራ በመቀጠል፣ በሂሳብ የተማሪዎችን ግንዛቤና አፈፃፀም ተማሪን የሚያሻሽል በቡድኑ የቀረቡትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚደግፍ ባለ አምስት-ነጥብ ፕላን Xx. Xxxxx አስተዋውቋል። ከነዚህ የውሳኔ ሀሳቦች ጥቂቶቹ፣ በ2016 በጀት ዘመን ጀምሮ፣ በወደፊት በጀቶች የሚደጎሙ ይሆናሉ።
የቀረቡት የውሳኔ ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው፡-
• የሂስብ ስኬትን በጥዋቱ መጀመር—የሂሳብ ባለሙያነት በኤሌሜንታሪ ደረጃ ማስፋፋት
• የመውደቅን ኡደት መሰባበር—የSecondary Articulation Policiesን እንደገና ማገናዘብ።
• ከሂሳብ ጋር ለሚታገሉ ተማሪዎች ኢላማ ያለው ድጋፍ ማድረግ—የምርመራ ትምህርት መሳርያዎችና ጣልቃመግባትን ማበልፀግ
• የሰራተኛ ችሎታን መገንባት—ከሂሳብ ጋር ወደ ሚታገሉ ተማሪዎች መዳረሻ ሞያዊ ማሳደጊያ መፍጠር
• የላቁ መምህሮቻችንን ባለሙያነት እንደ ቅስቀሳ መሳርያ መጠቀም—የተማሪና የመምህር መገልገያ እንደ ቤተመፃህፍት የመጣቀሻ ምንጭ አድርጎ መጠቀም
ለመካከለኛና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የመተዋወቂያ እለት ኦገስት 21 እንዲሆን ተወሰነ
የተማሪዎች የመተዋወቂያ እለት ሀሙስ፣ ኦገስት 21 እንዲሆን ተመደበ። ከልጅዎ ት/ቤት የተወሰነ ማረጃ በሰመር ወራት ይፈልጉ። የመተዋወቂያ ቀን የሚመጣው የትምህርት አመት አስተማሪዎቻቸውን ለማግኘት፣ ስለ ክፍል ትምህርቶች ፕሮግራም በተጨማሪ ለመማር፣ እና ተማሪዎች ለትምህርት መጀመርያ ቀን ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለመካከለኛና ለ2ኛ ደርጃ ት/ቤት ተማሪዎች አንድ እድል ነው። ትምሀር ሰኞ፣ ኦገስት 25 ይጀምራል።
ለተጨማሪ መረጃዎችና የት/ቤት ፕሮግራሞችን በሚመለከት ጥያቄዎች ካሉ የልጅዎን ት/ቤት ይገናኙ።
የሰመር እድሎች ለወጣት ልጆች (Teens)
የMontgomery County መዝናኛ የዘልማድ ሰመር ካምፖች ለሰለቻቸው ነገር ግን ከሌሎች ቢጤዎች (teens) ጋር ለመገናኘት እድል ለሚፈልገው ወጣት አንድ ትልቅ አማራጭ አለው። Summer Teen Escape Travel Program (የሰመር ወጣት መሽሎኪያ ጉዞ ፕሮግራም) ሰላማዊ፣ እንደ Hershey Park፣ Kings Dominion፣ እና Rehoboth Beach የመሳሰሉ የመዝናኛ መድረሻዎች የሚመሩ ጉዞዎች ያካተተ የአንድ ሳምንት ካምፕ መደቦች ያቀርባል
ፕሮግራሙ ጁን 30 ይጀምራል እናም አራት የአንድ-ሳምንት መደቦች ያቀርባል። መነሻ ቦታዎች White Oak፣ Xxxxxxx Xxxxxxxx፣ Potomac እና Germantown የማህበረሰብ መዝናኛ ማእከሎች እና Olney Manor Recreational Park ያካትታል። Summer Teen Escapes እድሜአቸው ከ13-16 ለሆኑ ወጣቶች ክፍት ነው። ምዝገባ xxxx.xxxxxxxxxxxxxxxxxx.xxx/xxx ይገኛል። ለተጨማሪ መረጃ፣ 000-000-0000 ደውሉ።