ዳኞች፡- 1. Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. Aቶ ሐጐስ ወለዱ
3. Aቶ ዳኜ መላኩ
4. Aቶ Aሰግድ ጋሻው
5. ወ/ት ሂሩት መለሰ
Aመልካቾች፡- 1ኛ. የሻረግ መንግሥቱ
2ኛ. ሰገዴ መንግሥቱ ተጠሪ፡- Eማሆይ የሻረግ ፈረደ
45 SCÒ - ¾ø^G’h TÁ%S 5Tp£w 45†øfi’ø~ Ñ˛k? - ¾SCÒ TÁ% uõC9 u?h †kvS’h ¾TSffCuh J~’@ - የõ/w/U/l 10001/2/m 1168m 1845m 1853
¾›T^ wh?^ф h6Sф æS9Wh ÖpSS õC9 u?h ¾›J~S ›æ6hŒk
†ÖsD ¾TEk ›vkS ¾›e æS9Wß kø68S u?h 5=Á4£hu~S SÑv6 uT5h Ák£u~hS h4 æCUa ¾fiT@S hS9C hõ†2 õC9 u?h ¾fiÖø~S ø~£’@ uæflC ¾hS9C ø£4 õC9 u?h hfi~ uSCÒ ks ITE6 uT5h ÁìTø~S ø~£’@ uæØøU ¾k£u ›u?ß፡፡
ዉሳኔ፡- uh65~ ÖpSS õC9 u?h ¾†fiÖø~ ø~£’@ ìS…6::
1. ø~5Ak Sw£hS u†æ5† u1675 æt£h ¾T˛9£9 4UU’h uæI’~ uk=J~ æt£h hCÑ~U ¾T˛fiÖø~ ¾ø~6 fi’9 £SffC uõ/w/U/l. 1845S u†æ5h† ¾T˛fiT ø~£’@ ¾5U፡፡
2. ¾TSSk£k4 Sw£h v5b9 /v5SF/ ¾I’ fiø~ ¾k=J~’~ Sw£h 9wC v5TØ£T 15 ¯æh hhA5 5?S SÑv26 ¾T˛6 fiø~ ŁS4=fiÖø~ 5=ÖSkxx ›Sk6U::
62
የሰበር መ.ቁ. 15631
ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. መንበረፀሐይ ታደሰ
2. ሐጐስ ወለዱ
3. ዳኜ መላኩ
4. Aሰግድ ጋሻው
5. ሂሩት መለሰ
Aመልካቾች፡- 1ኛ. የሻረግ መንግሥቱ
2ኛ. ሰገዴ መንግሥቱ ተጠሪ፡- Eማሆይ የሻረግ ፈረደ
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ መዝገብ ለሰበር ለቀረበው Aቤቱታ መነሻ የሆነው የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 364 በይግባኝ ደረጃ ቀርቦለት በነበረው ጉዳይ ሲያከራከር ቆይቶ የካቲት 16 ቀን 1996 ዓ/ም መረምሮ የሰሜን ጐንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የAሁኑ Aመልካቾች ተጠሪዋ የሟች Aባታችን የAቶ መንግሥቱ ዘወልዴን ቤት ሊያስረክቡን ይገባል በማለት ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የሰጠው ውሣኔ ነው፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዚህ ውሣኔው ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጐንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ክሱ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000 /1/2/ Eና 1845 መሠረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የወሰነው በሕጉ Aግባብ ነው በማለት Aጽንቶታል፡፡
Aመልካቾች Aባታችን Aቶ መንግሥቱ ዘወልዴ ከሞቱ በኋላ በውርስ ሊተላለፍልን የሚገባውን ቤት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት ተረክበን ተጠሪዋ ባይወልዱንም Eናታችን ናቸው ብለን በማሰብ Eንዲቀመጡበት ያደረግነውንና በAክብሮት ሣንጠይቃቸው የቆይነውን ንብረት Eንዲያስረክቡን በማለት ያቀረብነው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል በተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል
በሚል ለሰበር Aቤቱታ Aቅርበዋል፡፡ Aመልካቾች ንብረቱን ሣንጠይቅ የቆየነው በቤተዘመድ ግንኙነት ምክንያት ተጠሪዋን በመፍራትና በማክበር ስለሆነ ፍ/ቤቱ የይርጋውን ክርክር በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1853/1/ መሠረት ሊቀበለው Aይገባም ባዮች ናቸው፡፡
Aቤቱታው ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት Eንዲቀርብ በመወሰኑ በAመልካቾች በኩል የቀረበው ማመልከቻ ለAሁኗ ተጠሪ Eንዲደርሳቸው ተደርጐ ሐምሌ 18 ቀን 1996 ዓ/ም የተፃፈ መልስ Aቅርበዋል፡፡ Aመልካቾች በበኩላቸው የመልስ መልስ ሰጥተውበት ተከራክረዋል፡፡
በተጠሪዋ በኩል የቀረበው ክርክር ሲታይ Aመለካቾች Eኔን የEንጀራ Eናታቸውን በማክበርም ሆነ በመፍራት መብታቸውን ሣይጠይቁ ቆይተዋል ሊባል ስለማይችል ፍ/ቤት ይርጋ Aልቀበልም የሚልበት ምክንያት የለም የሚል ይዘት ያለው
ነው፡፡
ችሎቱም የAሁኑ Aመልካቾች ከ1962 ዓ/ም በፊት የሞቱትን የAባታችንን ቤት ይዘው የሚገኙት የAሁኗ ተጠሪ ሊያስረክቡን ይገባል በሚል ያቀረቡት ክሥ በይርጋ ቀሪ ሆኗል Aልሆነም፣ ፍ/ቤት ይርጋ Aልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት Aለ ወይንስ የለም የሚለውን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል፡፡
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጐንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤትም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የAሁኑ Aመልካቾች ከAባታችን በውርስ ሊተላለፍልን የሚገባውን ቤት የAሁኗ ተጠሪ ምንም Aይነት መብት ሣይኖራቸው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆን ይዘው ስለሚገኙ ሊያስረክቡን ይገባል በሚል ያቀረቡትን ክስ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1845 መሠረት በAሥር Aመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ሊወሰኑ የቻሉት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም ተደርጓል የተባለውን ውል መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ከሰነዱ Eንደሚታየው ግን ቤቱን የAሁኗ ተጠሪ ለቀው ለሟቹ ለAቶ መንግሥቱ ዘውልዴ ወራሾች ማሥረከባቸው Eና ሌሎችን ንብረቶችም ስለመከፋፈላቸው
ከመገለጹ በቀር የሟቹ የAባታቸው ሚስት በቤቱ Eየተጠቀሙበት ይቆዩ ወይም ይኑሩበት የሚል ነገር የለውም፡፡ ከዚህ ሌላ ቤቱ በሟች ሚስት ይዞታ ሥር ቆይቶ ወደፊት በዚህ ጊዜ ለወራሾች ያስረክባሉ የሚል የውል ቃል የለውም፡፡ በሰነዱ ላይ
የሰፈረው በሕግ የውል ትርጉም የሚሰጠው Aይደለም፡፡ ውል ማለት ደግሞ
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1675 ላይ Eንደተመለከተው ንብረታቸውን የሚመለከቱ ግዴታቸውን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል የሚደረግ ሥምምነት ስለሆነ በዚሁ መሠረት የውል ትርጉም የሚሰጠው ነገር ሣይኖር ውል Aለ የሚል መነሻ በመያዝ ይርጋን በሚመለከት ተፈፃሚ የሚሆነው ስለውሎች በጠቅላላው በሚለው የፍትሐብሔር ሕጉ ክፍል ተጽፎ የሚገኘው በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1845 ላይ የተመለከተው የAሥር Aመት ጊዜ ነው ብሎ መወሰን ትክክል Aይደለም፡፡ በAሁኑ Aመልካቾች በኩል የቀረበው የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም የተፃፈው ሰነድ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ጋራ በተያያዘ የሚያስነሣው የይርጋ ጥያቄ ስለሌለ በዚህ ጉዳይ የተጠቀሰው የይርጋ ሕግ Aግባብነት የለውም፡፡
በሌላም በኩል የAሁኗ ተጠሪ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ሲከራከሩ የነበሩት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም ተፃፈ የተባለውን ሰነድ መነሸ በማድረግ ብቻ ሣይሆን ቤቱ ከ1943 ዓ/ም ጀምሮ ባለማቋረጥ ግብር Eየከፈልኩበት ንብረቴ ሆኗል፣ ከሃያ ሰባት Aመት በላይ በስሜ ስገብርበት ቆይቼ የቤቱ የቦታ ይዞታም ሆነ የቤቱ ባለቤትነት ሥም በሥሜ ሊሆን ችሏል በሚል ምክንያት ጭምር ሲሆን Eነዚህ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መሆናቸውን ከመዝገቡ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከEነዚህ ፍሬ ነገሮች በመነሣት በሕጉ በኩል ያለው ሲታይ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1168/1/ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለEጅ /ባለይዞታ/ የሆነ ሰው የዚሁኑ ንብረት ግብር ባለማቋረጥ
15 ዓመት በሥሙ ከከፈለ የዚሁ ሀብት ባለቤት ይሆናል በሚል ደንግጐ ይገኛል፡፡ ሕጉ
ይርጋ Aዘል ስለሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለEጅ /ባለይዞታ/ የሆነው ሰው የዚህን ንብረት ግብር ባለማቋረጥ ለ15 ዓመት በሥሙ ከከፈለ ሌላ ይገባኛል የሚል ሰው Eንዲሰጠው ሊጠይቀው Aይችልም፡፡ በሕጉ ለባለይዞታው መብቱ ይረጋለታል፡፡ የAሁኗ ተጠሪም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ባለይዞታ በመሆን የዚሁኑ ንብረት ግብር
ባለማቋረጥ ከ15 ዓመት በላይ በሥማቸው ሲከፍሉ ስለቆዩ በሕጉ የዚሁ ሀብት ባለቤት ሆነዋል፡፡ የAሁኑ Aመልካቾች Aባት ከ1962 ዓ/ም በፊት የሞቱ ስለሆነ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተጠሪዋ ይዞታ ሥር የቆየውን ቤት ከሃያ ስምንት Aመት በኋላ Eንዲያስረክቧቸው ያቀረቡት ክሥ በይርጋ ቀሪ Aይሆንም በሚል የሚያቀርቡት
ክርክር ተቀባይነት የለውም፡፡
Aመልካቾች ክስ ሣናቀርብ የቆየነው ተጠሪዋ የሟቹ Aባታችን ሚስት በመሆናቸው በመፍራትና በማክበር በመሆኑ ፍ/ቤት ይርጋውን ሊቀበለው Aይገባም በሚል ያነሱትን ክርክር በተመለከተም በEርግጥ ፍ/ቤት ይርጋን Aልቀበልም የሚልባቸው ምክንያቶች Aሉ፡፡ Eነዚህ ምክንያቶች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1853 የተዘረዘሩት ሲሆኑ ከEነዚህ መካከል ባለገንዘቡ የሚፈልገውን ያልጠየቀበት ምክንያት ባለEዳውን የመፍራትና የማክበር ስሜት መኖር Aንዱ ነው፡፡ Aመልከቾች ከሃያ ስምንት Aመት በላይ ተጠሪዋ ቤቱን Eንዲያስረክቡን ሣንጠይቅ የቆየነው የAማታችን ሚስት ስለሆኑ Eንደ Eናት ስለምናያቸው የመፍራትና የማክበር ስሜት Aድሮብን ነው ይበሉ Eንጅ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት Aመለካቾች Aባታቸው ከሞቱ በኋላ የAባታችንን ንብረት Aካፍይን ወይም Aስረክቢን የሚል ጥያቄ Aንስተው ሽማግሌዎች ሰብስበው የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም በተፃፈ ሰነድ በተደረገ Eርቅ ንብረት መከፋፈላቸው መገለጹና በዚሁ ሰነድ Aማካኝነት ቤቱን ተረክበን ነበር ማለታቸው ሲታይ ከዚህ በኋላ ሣይጠይቁ የቆዩት ተጠሪዋን በመፍራትና በማክበር ምክንያት ነው ለማለት Aይቻልም በሚል ሣይቀበላቸው ቀርቷል፡፡ በAመልካቾች በኩል ተጠሪዋን የመፍራትና የማክበር
ስሜት ነበረ Aልነበረም ለሚለው ፍ/ቤት መፍራትም ሆነ ማክበር Aልነበረም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ወደ ፍሬ ነገር ጥያቄ ስለሚያመዝን በሰበር ደረጃ ሊመረመር Aይችልም፡፡ በሰበር ደረጃ ሊታይ የሚችለው የሥር ፍ/ቤት የመፍራትና የማክበር
ስሜት መኖሩን Aረጋግጦ ይርጋን Aልቀበልም ለማለት የሚያስችል የሕግ ምክንያት
Aይደለም በሚል ወስኖ ቢገኝ ነው፡፡ ስለዚህ Aመልካቾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ ሕግ ቀሪ መሆኑ ቢረጋገጥም ፍ/ቤት ይርጋውን Aልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት Aለ በሚል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም፡፡
ከፍ ሲል Eንደተገለፀው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ/ም በተፃፈው ሰነድ በAመልካቾችና በAሁኗ ተጠሪ መካከል ቤቱን በሚመለከት የተደረገ የውል ስምምነት Eንዳለ Aድርጐ በመመልከት ይህንኑ መነሻ በመድረግ ለተነሣው የይርጋ ጥያቄ የሚመለከተው የይርጋ ሕግ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የAሥር Aመት ጊዜ ነው ማለቱ የተሣሣተ ሆኖ ቢታይም ክሱ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1168 Aንፃር ሲመረመር በይርጋ ቀሪ ከመሆን የሚድን ሆኖ
ስላልተገኘ በውጤቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ መወሰኑ ተቀባይነት የሚሰጠው ነዉ፡፡
ው ሣ ኔ
1. በAሁኑ Aመልካቾች በኩል የቀረበው ክሥ በይርጋ ቀሪ መሆኑ ስለተረጋገጠ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡
2. በዚህ መዝገብ በተደረገው ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
ጉዳዩ ስለተወሰነ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት፡፡