Contract
የሰ/መ/ቁ. 43888 መጋቢት 23 ቀን 2002ዓ.ም
ዲኞች፡- ተገኔ ጌታነህ
ሑሩት መሇሰ ብርሃኑ አመነው አሌማው ወላ ዓሉ መሏመዴ
አመሌካች፡- አቶ ፀሏይ ወንዴም - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1/ አቶ አያሇው መሇስ - አሌቀረቡም
2/ ወ/ት ፌሬህይወት - ተመስገን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዮን ፌርዴ ሰጥተናሌ፡፡
ፌ ር ዴ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የውሳኔ አፇፃፀም የሚመሇከት ነው፡፡ ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፌፌሌን መነሻ ያዯረገ ሲሆን ግራ ቀኙ በአይነት ሇመከፊፇሌ ከስምምነት ሇመዴረስ አሇመቻሊቸውን ጠቅሶ በጨረታ ተሸጦ ውጤቱ እንዱቀርብ ሲሌ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፌተኛ ፌርዴ ቤት በአፇፃፀም መዝገብ የሰጠውን ትዕዛዝ የክሌለ ጠቅሊይ ፌርዴ ቤት እና የክሌለ ጠቅሊይ ፌርዴ ቤት ሰበር ሰሚ ችልቶች በማጽናታቸው አመሌካች ሇዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዋሌ፡፡
አመሌካች የካቲት 26 ቀን 2001ዓ.ም ጽፇው ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የውርስ ሏብቱን ስመሏብት ወዯ ስማቸው ሇማዞር ያቀረቡትን አቤቱታ ፌርዴ ቤት ትዕዛዝ ሳይሰጥበት ማሇፈ እና የቤቱ ዋጋ በባሇሙያ ወይም በሽማግላ ሳይገመት ቤቱ በወር በሚያስገኘው የኪራይ ገቢ መነሻ በጨረታ እንዱሸጥ መዯረጉ መብታቸውን እንዯሚጎዲ ጠቅሰው ንብረቱን በስምምነት ሇመሸጥ ወይም ሇማከራየት እንዱችለ እንዱወሰን አመሌክተዋሌ፡፡
ይህ ችልትም አቤቱታውን ከመረመረ በኋሊ የስር ፌ/ቤት አፇፃፀሙን የሰራው በተከራከሪ ወገኖች ፇቃዴ እና በውሳኔው መሠረት መሆን ያሇመሆኑን ሇመመርመር ተጠሪዎችን አስቀርቧሌ፡፡ አንዯኛ ተጠሪ ጥር 25 ቀን 2002ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መሌስ በውሳኔው መሠረት ቤቱን ማስረከቡን ገሌጿሌ፡፡ ሁሇተኛ ተጠሪ ጥር 3 ቀን
2002ዓ.ም በጽሐፌ በሰጡት መሌስ ከአመሌካች ጋር ወራሽ መሆናቸውን ጠቅሰው ቤቱን በአይነት ሇመከፊፇሌ አመቺ አሇመሆኑን አመሌካች እያወቁ ቤቱን ይዞ አፇፃፀሙን ማጓተት ተገቢ አሇመሆኑን ጠቅሰው ቤቱ በጨረታ ተሸጦ ገንዘቡን እንዱካፇለ እንዱወሰን አመሌክተዋሌ፡፡
የግራ ቀኙ ክርክር እና የጉዲዩ አመጣጥ ከሊይ የተመሇከተው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩን መርምረናሌ፡፡
በዚህ ፌ/ቤት ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በዚህ ፌ/ቤት ምሊሽ የሚያሻው ነጥብ ግራ ቀኙ ንብረቱን በስምምነት ሇመከፊፇሌ ያሌቻለ እንዯሆነ የጨረታው ሽያጭ መነሻ ዋጋ ተብል የተወሰዯውን አግባብነት እንዯሚከተሇው መርምረናሌ፡፡
ከከፌተኛው ፌ/ቤት ትዕዛዝ መረዲት እንዯተቻሇው የጨረታ መነሻ ዋጋ ተብል የተጠቀሰው ብር 16,527.29(አስራ ስዴስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሰባት ከሃያ ዘጠኝ ሣንቲም) ቤቱን የቅደስ ጊዮርጊስ ቢራ ማከፊፇያ የተከራየበት ግምት መሆኑ ነው፡፡ ይህ ገንዘብ የቤቱ የአመት የኪራይ ዋጋ ስሇመሆኑ አመሌካች በአቤቱታቸው ገሌፀዋሌ፡፡ ተጠሪዎች ይህ ሏሰት ነው አሊለም፡፡ ይህ ፌሬ ነገር ሲታይ ቤቱ በሏራጅ እንዱሸጥ ሲወሰን የቤቱ ዋጋ ተብል ሉወሰዴ የሚገባው የኪራይ ዋጋ ማሇት እንዲሌሆነ መረዲት የሚያዲግት አይዯሇም፡፡ አፇፃፀሙን የያዘው ፌ/ቤት ግን የኪራይን ዋጋ ሇቤቱ ሽያጭ የጨረታ መነሻ ዋጋ አዴርጎ ወስድታሌ፡፡ በፌ/ብ/ሔግ ቁጥር 1083 እና ተከታዮቹ ዴንጋጌዎች የውርስ ንብረት ግምት አፇፃፀም ተመሌክቷሌ፡፡ በዚህ ዴንጋጌ መሠረት የንብረቱ ግምት በወራሾች ስምምነት ሉወሰን የሚችሌ ሲሆን ከስምምነት ካሌዯረሱ እነሱ በመረጧቸው የሽምግሌና ዲኞች አሉያም ፌ/ቤቱ በሚመርጣቸው የሽምግሌና ዲኞች ሉገመት እንዯሚችሌ ተጠቅሷሌ፡፡ ይህም ካሌተቻሇ በፌ/ብ/ሔግ ዴንጋጌ ቁጥር 1084 መሠረት በባሇሙያ እንዱገመት ማዴረግ ይገባሌ፡፡
ይህ ግምት የሚከናወነው የንብረቱን ይዞታ እና የገቢያ ዋጋ ሇማመሌከት እንዯሆነ መረዲት ይቻሊሌ፡፡ በተያዘው ጉዲይ ፌ/ቤቱ የንብረቱ ግምት ነው ብል የኪራይ ዋጋ ግራ ቀኙ የተስማሙበት ነው በማሇት ሇሽያጭ መነሻ ዋጋ ግምት አዴርጎ መውሰዴ አግባብ ሆኖ አሊገኘነውም፡፡
ስሇሆነም በዚህ ገረዴ ፌ/ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ የግራ ቀኙን መብት የሚያጣብብ ከመሆኑ አንፃር እንዱሁም በሔጉ ከተመሇከተው አግባብ ውጪ በመሆኑ መሠረታዊ የሔግ ስህተት የተፇፀመበት ሆኖ አግኝተናሌ፡፡
ስሇሆነም ሉታረም ይገባሌ ብሇናሌ፡፡ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናሌ፡፡
ው ሳ ኔ
1. የምሥራቅ ጎጃም ከፌተኛ ፌርዴ ቤት በመ/ቁ 25564 የሰጠው የአፇፃፀም ትዕዛዝ እና የአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅሊይ ፌርዴ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ቁ 01020 የሰጠው ትዕዛዝ በፌ/ብ/ሥ/ሥ/ሔ/ቁ 348/1/ መሠረት ተሽሯሌ፡፡
2. ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የውርስ ንብረት ዋጋ በግራ ቀኙ ስምምነት አሉያም በባሇሙያ ተገምቶ እንዱቀርብ በማዴረግ የሏራጅ ሽያጭ እንዱዯረግና በውጤቱም መሠረት እንዱያስፇጽም መዝገቡ በፌ/ብ/ሥ/ሥ/ሔግ ቁጥር 343/1/ መሠረት ሇምሥራቅ ጎጃም ከፌተኛ ፌ/ቤት እንዱመሇስ አዝዘናሌ፡፡
3. የዚህ ፌ/ቤት ውጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ፡፡ መዝገቡ ተዘግቷሌ ይመሇስ፡፡ ይፃፌ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዲኞች ፉርማ አሇበት፡፡
ሶ/በ