Peter Tatian እና Diane Glauber
የሜትሮፖሊታን ዋሽንግተን ክልላዊ የፍትሃዊ የቤቶች እቅድ አስፈፃሚ ማጠቃለያ
Xxxxx Xxxxxx እና Xxxxx Xxxxxxx
መግቢያ
የፍትሃዊ መኖሪያ ቤቶች እንቅፋቶች
ሰዎች በብዙ ምክንያቶች በዚህ ክልል ውስጥ ለመኖር ይመርጣሉ - ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያክል፣ ጤናማ ሰፈሮች፣ ጥሩ ትምህርት ቤቶች እና የስራ እድል። ነገር ግን ብዙዎቹ የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች እድሎችን በተመለከተ እኩል አይስተናገዱም። ይህ በተለይ ነጭ ላልሆኑ ነዋሪዎች፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና አካል ጉዳተኞች እውነት ነው።
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቁር፣ ተወላጆች እና ነጭ ያልሆኑ (BIPOC) ሰዎች ያሉባቸው አካባቢዎች አብዛኛውን ጊዜ ከፍ ያለ የድህነት መጠን የሚታይባቸው እና የጥሩ ትምህርት ቤቶች፣ ጤናማ ሰፈሮች፣ መጓጓዣ እና የስራ እድሎች የማግኘት እድል ተደራሽነት አናሳ የሆነባቸው ናቸው።
በክልላችን ያሉ ብዙ የአካባቢ መስተዳድሮች አስተማማኝ እና ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ ዋና ዋና እርምጃዎችን ወስደዋል። ከወሰዷቸው እርምጃዎችም ውስጥ፦
• የገንዘብ ድጋፍ መጨመር
• የዞን ለውጦችን ማድረግ
• በአዳዲስ ልማቶች ላይ ድህንነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ የመኖሪያ ቤት የአዲስ ልማት መስፈርት ውስጥ እንዲካተት ማድረግ
ከዚሁ ጎን ለጎን ግን ክልሉ በአካባቢው የመኖሪያ ቤቶች ዋጋ እና የቤት ኪራይ ጭማሪ ሳቢያ የመፈናቀል ስጋትን የሚያባብስ አዲስ የንግድ ልማት ኢንቨስትመንት መሳቡን ቀጥሏል። በተጨማሪም፣ ለልማት የሚሆን መሬት ለማግኘት እና በሜትሮፖሊታን ዋሽንግተን ክልል ውስጥ ለመገንባት የሚያስፈልገው ከፍተኛ ወጪ፣ አብዛኛው የሚገነባው አዳዲስ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ለብዙ ነዋሪዎች ከአቅም በላይ ይሆናል ማለት ነው። እነዚህ የገበያ ሃይሎች አብዛኛውን ጊዜ በማሕበረሰባዊ ተቃውሞ፣ ወይም ይበልጥ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ የመኖሪያ ቤቶች ወይም የቤቶች ቁጥር ለመጨመር ሙከራ ሲደረግ ከነዋሪዎች በኩል የሚነሳው የNot in My Backyard (NIMBY) (በጓሮዬ አይደረግም) ተቃውሞ የሚታጀቡ ናቸው፣ እነዚ ሁሉ ለክልሉ ፈተናን የሚደቅኑ ናቸው።
የክልሉ የፍትሃዊ መኖሪያ ቤቶች ዕቅድ
ከዩኤስ የቤቶች እና የከተማ ልማት መመሪያ (U.S. Department of Housing and Urban Development (HUD)) የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የክልል እና የአካባቢ መስተዳድሮች የፍትሃዊ የመኖሪያ ቤቶች እቅድ ማቅረብ አለባቸው። የተለያዩ እቅዶችን ከማዘጋጀት ይልቅ ስምንት ማህበረሰቦች በአንድነት ሆነው ከ Public Housing Authorities (PHAs) (የህዝባዊ ቤቶች ባለስልጣን) እና ከሌሎች ጋር በክልላዊ ዕቅድ ላይ ሠርተዋል።
ውጤቱም የሜትሮፖሊታን ዋሺንግተን የፍትሓዊ መኖሪያ ቤቶች ምርጫ እንቅፋቶች ክልላዊ ትንተና ነው። ወደ HUD ከመላኩ በፊት እያንዳንዱ አከባቢያዊ መስተዳድር ሊያጸድቀው ይገባል።
ዋሺንግተን ዲሲ እና በአከባቢው የሚገኙ ማሕበረሰቦች በክልላዊ ዕቅድ ላይ በጋራ መስራት ከጀመሩ 25 ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህም ከ 2022 እስከ 2026 ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው፣ ይህም በነዚህ ክልላዊ ግቦች ላይ በጋራ መስራታችንን እንደምንቀጥል የሚያረጋግጥ ነው።
• የፍትሓዊ መኖሪያ ቤት መስፈርቶችን ማሟላት
• ደህንነታቸው የተጠበቀ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ የመኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት ያለውን ዕድል የተሻለ ማድረግ
• ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቦታዎች ላይ ኢንቨስትመንት እና የሃብት ፍሰትን መጨመር
• የነዚህ መኖሪያ መንደሮች ተደራሽነት ማሻሻል
• ቀደም ሲል የነበሩ እና አሁንም ላይ ያሉ የመለያያት አካሄዶችን ማሸነፍ
• ፍትሓዊ የሆነ የመኖሪያ ቤት ምርጫን ማስተጋባት
• ይበልጥ አቃፊ የሆኑ ማሕበረሰቦችን መፍጠር
የፕሮጀክት ቡድኑ
የፕሮጀክት ቡድኑ Metropolitan Washington Council of Governments (“COG”) የመሰረቱ ከ 8-24 የሚሆኑ አከባቢያዊ መስተዳድሮች ተወካዮችን በአባልነት የተካተቱበት ነው።
• City of Alexandria, VA
• Arlington County, VA
• District of Columbia
• Fairfax County, VA
• City of Gaithersburg, MD
• Loudoun County, VA
• Montgomery County, MD
• Prince William County, VA
ከዚህም በተጨማሪ ለዚህ ዘገባ/ሪፖርት አስተዋጽኦ ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፦
• በፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫ ከተጎዱ ነዋሪዎች ጋር የሚሰራ የአካባቢ ቡድኖች የማህበረሰብ አማካሪ ኮሚቴ
• ከFairfax County, VA, the District of Columbia, and the City of Alexandria, VA የመጡ የ
PHA አጋሮች
• ለአብዛኛዎቹ የእቅዱ ቴክኒካል ስራዎች፣ ሎጅስቲክስ፣ የውሂብ ትንተና እና ውህደት እና የመፃፍ ሃላፊነት የነበረው የአማካሪ ቡድን። ቡድኑ በህግ በተደነገገው የሲቪል መብቶች የህግ ባለሞያዎች ኮሚቴ እንደዚሁም የከተማ ኢንስቲትዩት፣ Xxxxx የከተማ ትብብር እና የHUD የቴክኒክ ድጋፍ አጋር የኢንተርፕራይዝ ማህበረሰብ አጋሮችንም አካቷል።
የማህበረሰብ ተሳትፎ
ከዚህም በተጨማሪ የፕሮጀክት ቡድኑ ነዋሪዎች እና ሌሎች በእቅዱ የተጎዱ ሰዎች በሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጧል። ቡድኑ ነዋሪዎች በአካባቢያዊ የመኖሪያ ቤት ውሳኔዎች ላይ ድምጽ እንዲኖራቸው በሚያደርጉ መንገዶች ላይ መመሪያ በሚሰጠው የ2015 Affirmatively Furthering Fair Housing rule ላይ ተመስርቷል።
ያዘጋጀነው ዕቅድ ለክልላችን ነዋሪዎች ተመሳሳይ ነገር ማድረጉን ልማረጋገጥ፣ እኛ፦
• እነሱን እና ሌሎች ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ሃሳባቸውን እና ምክሮቻቸውን እንዲያካፍሉን ጠይቀናል
• ከዚህ ያገኘነውን መረጃ የውሂብ ግኝቶችን ለማረጋገጥ እና የመረጃ ክፍተቶችን ለመለየት ተጠቅመንበታል
• ሃሳቦቻቸውን እና አስተያየታቸውን በዕቅድ ውሳኔዎች እና ውጤቶች ላይ አካተናል
• የዕቅዱን የመጨረሻ ድምዳሜዎች እና ምክረ ሃሳቦችን ቅርጽ በምናስይዝበት ጊዜ ድምጻቸውን ግምት ውስጥ አስገብተናል።
ባለድርሻ አካላት እንዴት ተሳታፊ እንደሆኑ
ከጁላይ 2021 እስከ ማርች 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ ከ 1200 በላይ የሆኑ ኤጀንሲዎች፣ ቡድኖች እና ግለሰቦች የክልሉ የፍትሃዊ መኖሪያ ቤቶች ዕቅድ ሂደት ተሳታፊ ነበሩ። የፕሮጀክት ቡድኑ በCOG፣ በአከባቢ መስተዳድር እና በማህበረሰብ አማካሪ ኮሚቴ አባላት ተለይተው የታወቁትን ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር በጋዜጣ፣ በድረ-ገጾች እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የህዝባዊ ማስታወቂያዎችን አውጥቷል። በማዕከልነት የሚያገለግል ድረ-ገጽ xxx.xxxxx.xxx/xxxxxxxxxxx ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤትን የተመለከተ መረጃ፣ የዕቅድ ሰነዶች እና የስብሰባ ማሳወቂያዎችን የያዙ መረጃዎችን እና ማስፈንጠሪያዎችን የይዛል።
እናም እነዚህ ዘዴዎች ህዝቡ ሰለ ዕቅዱ እንዲያውቅ እና በነዚህም በኩል ያለውን አስተያየት እና ሃሳብ እንዲያቀርብ ለማድረግ ረድተዋል፦
• ክልላዊ የትኩረት ቡድኖች። ጁላይ 2021 ላይ Challenging Racism ከተባለ ከ በቨርጂኒያ ውስጥ ከሚገኝ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ጋር ሶስት መርሃ-ግብሮችን አካሂደናል። እነዚህ መርሃ-ግብሮች ላይ ወደ 400 የሚሆኑ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በመኖሪያ ቤት፣ በመጓጓዣ፣ ትምህርት፣ አከባቢ እና ዘር ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እና መረጃዎች የያዙ ነበሩ።
• አከባቢያዊ የትኩረት ቡድኖች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች። በ2021 አራተኛው ሩብ ጊዜ የትኩረት ቡድኖችን እና ህዝባዊ ስብሰባዎችን በስምንቱም ክልሎች አካሂደናል። ተሰብሳቢዎቹ የቀረቡ ዘገባዎችን ሰምተው በትንንሽ የውይይት ቡድኖች ላይ ተሳትፈዋል። ርእሶች ፍትሃዊ የቤቶች ሂደት፣የቤቶች መረጃ እና ተዛማጅ የቤት ጥናቶችን ያካተቱ ነበሩ።
• የዳሰሳ ጥናት። ከጁላይ 2021 እስከ ፌብሩዋሪ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ወደ 3,000 የሚጠጉ ነዋሪዎች ለዳሰሳ ጥናት ምላሽ ሰጥተዋል። በተመጣጣኝ ዋጋ በሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶች እኛ በማግለል ላይ ያላቸውን ተሞክሮ አካፍለዋል።
• ቃለ-መጠይቆች። ከፍትሃዊ የመኖሪያ ቤቶች እና የሰብአዊ መብቶች ቡድኖች እና ከግል የመኖሪያ ቤት ኢንዳስትሪው የመጦ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባላድርሻ አካላትን እኛ ውሳኔ ሰጪ አካላትን ጨምሮ እስከ 50 የሚሆኑ ሰዎች ቃለ-መጠይቅ አካሂደናል። ከቀደምት እና ከተመራጭ የህዝባዊ ባለስልጣናት እና የለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች መሪዎችም ጋር ተነጋግረናል።
• ሌሎች የትኩረት ቡድኖች። ከላይ ከተጠቀሱት ተግባራት የተገኙ ውጤቶችን ከገመገምን በኋላ ከተወሰኑ ቡድኖች በተለይም ከስፓኒሽ ተናጋሪዎች፣ ስደተኞች እና LGBTQ+ ማህበረሰቦች፣ አዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞች የበለጠ መረጃ ለመሰብሰብ ወስነናል። እነዚህን ነዋሪዎች ከሚወክሉ የአከባቢ ቡድኖች ጋር የሰራን ሲሆን፣ በ ማርች 2022 ላይ ከአምስት ተጨማሪ የትኩረት ቡድኖች ጋር መርሃ-ግብሮችን አካሂደናል።
በኮቪድ-19 የተነሳ አብዛኛዎቹ ስብሰባዎች ቨርቹዋል ነበሩ። ማንኛውም በአካል የተደረጉ ስብሰባዎች በመንግስት መሥሪያ ቤቶች የተከናወኑ ሲሆን ለሁሉም ተደራሽነት ለማረጋገጥ የፌዴራል መስፈርቶችን አሟልተዋል፦
• የስብሰባ ቦታዎች የአሜሪካን የአካል ጉዳተኞች አዋጅን ያከበሩ ነበሩ።
• ድረ-ገጾች እና ስብሰባዎች የመልሶ ማቋቋም አዋጅ ክፍል 508 ን ያከበሩ ነበሩ። የኤሌክትሮኒክስ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆን ይጠይቃል። ይህ የእይታ ወይም የመስማት ችግርን ይጨምራል።
• የእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር ለማይችሉት የስፓኒሽ አስተርጓሚዎች እና ሌሎች አገልግሎቶች ቀርበዋል።
ሳጥን 1 ከእነዚህ ተግባራት ያገኘናቸውን የተወሰኑ ግኝቶቻችንን ያካትታል። ለበለጠ መረጃ፣ ወደ የዕቅዱ የማህበረሰብ ተሳትፎ ክፍል xxx.xxxxx.xxx/xxxxxxxxxxx ይሂዱ።
ሳጥን 1
ከማህበረሰብ ተሳትፎ እንቅስቃሴዎች የተገኙ ግኝቶች ማጠቃለያ
▪ የዳሰሳ ጥናቱን ካጠናቀቁት ውስጥ 83.6% የሚሆኑት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ቤት ለማግኘት አስቸጋሪ ነበር ብለዋል።
▪ 13% መድልዎ ገጥሟቸዋል፤ ከነሱ 41% ያህሉ አከራዮችን ወይም የንብረት አስተዳዳሪዎችን ተጠያቂ አድርገዋል።
▪ የአካባቢ የትኩረት ቡድኖች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ የተሳተፉት ለፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ዋና ዋናዎቹ ሶስት እንቅፋቶች የሚከተሉት ናቸው ብለዋል፦
- በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ የመኖሪያ ቤት እጥረት
- የመንግስት ውድቀት
- የዘር መድልዎ
▪ ሶስት ዋና ያሏችወ መፍትሔዎችም፦
- የባህል እና የቋንቋ ብቃት ያላቸው ተጨማሪ ፕሮግራሞች እና ሰራተኞች
- ለአካል ጉዳተኞች የመኖሪያ ቤት ተደራሽነት
- የመኖሪያ ቤት የገንዘብ ድጋፎችን የማግኘት ዕድል
▪ ተጨማሪ ወሳኝ መፍትሔዎች፦
- ስፓኒሽ ተናጋሪ የመኖሪያ ቤት አማካሪዎች እና የአካባቢ መስተዳድር ባለስልጣናት
- እንደ አረብኛ፣ አማርኛ እና ቻይንኛ ባሉ ቋንቋዎች የፕሮግራም መረጃ
- ለአረጋውያን በቦታቸው እንዲቆዩ የሚያደርጉ አማራጮች እና ፕሮግራሞች
- አከራዮች/የንብረት ባለቤቶች አስፈላጊ የሆኑትን ምክኒያታዊ አቅርቦቶች ማሟላት
- የቤት እጦትን ለመከላከል ለ LGTBQ እና ለትራንስ ወጣቶች የሚቀርቡ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች
ቀደም ሲል የነበሩ ግቦችን መገምገም
ከዚህ በተጨማሪ ክልላዊው የፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ዕቅድ ስምንቱ የአካባቢ መስተዳድሮች ቀደም ሲል በፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት እቅዶች ወይም ሪፖርቶች ላይ የተቀመጡትን ግቦች መድረስ ላይ ያስያቱን እድገት ይገልፃል። ክስር የተወሰኑ ምሳሌዎች ተቀምጠዋል። ለተጨማሪ መረጃ፣ የዕቅዱን የበፊት ግቦች ግምገማ ክፍልን ይመልከቱ።
• የአሌክሳንድሪያ ከተማ። ከተማዋ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ አጋሮቿ አንድ ላይ በጃኑዋሪ 2014 እና ጁን 2022 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ 774 መኖሪያ ቤቶችን ገንበተዋል ወይም ጥገና አካሂደዋል። ይህም በአዲስ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ውስጥ 151 ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ክፍሎችን የሚያካትት ነው። ከዚህም በተጨማሪ የባለብዙ ቤተሰብ ዞን ለመፍጠር ከተማዋ በ2019 የዞን ክፍፍል ህጎችን ቀይራለች። የንብረት ባለቤቶች እና ገንቢዎች የረጅም ጊዜ እና በጣም ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ለመገንባት እና ለማቆየት ማበረታቻ ያገኛሉ።
• አርሊንግተን ካውንቲ። ካውንቲው ከአካባቢው መካከለኛ ገቢ 60% ወይም ከዚያ በታች ለሚያገኙ ቤተሰቦች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ጨምሯል። እነሱም፦
- የካውንቲውን የተመጣጣኝ ቤቶች ኢንቨስትመንት የገንዘብ ድጋፍ ለውጠዋል
- ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን ክፍሎች ከመንግስት ድጎማ ውጪ መጥፋትን ለመከላከል የቤቶች ጥበቃ ዲስትሪክቶችን ፈጥረዋል
- ገንቢዎች የበለጠ ቁጥር ያላቸው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ ቤቶችን በመገንባት ፈንታ ተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶችን እንዲገነቡ ለማስቻል የጉርሻ ጥግግትን ተጠቅመዋል
• ኮለምቢያ ዲስትሪክት። የዲስትሪክቱ Department of Housing and Community Development (DHCD) (የቤቶች እና የማሕበረሰብ ልማት መምሪያ)፦
- በ2017 እና 2019 በ Qualified Allocation Plan (QAP) (ብቁ የሆነ የምደባ እቅድ) እና በ
Consolidated Request for Proposals (RFP) (ተዋሃደ የውሳኔ ሃሳቦች) ላይ ለውጦችን አድርጓል።
እነዚህም ለውጦች DHCD የፌዴራል እና የአካባቢ አቅምን ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት የገንዘብ ድጋፎችን በመጠቀም ያለውን ልዩነት ለመቀነስ እና የወደፊትም እንዳያጋጥም ለማስቀረት አስችለዉታል።
- የገንዘብ ድጋፍ ውሳኔዎችን በሚወስኑበት ጊዜ ንብረቱ የት እንደሚገኝ እና ለህዝብ ባቡር ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ግምት ውስጥ ያስገባሉ። ይህ የፕሮጀክት ስፖንሰሮች ከፍተኛ ዕድል ባለባቸው ሰፈሮች ውስጥ ተመጣጣኝ ቤቶችን ለመገንባት ወይም ለማቆየት የሚያስችላቸውን ማበረታቻ እንዲያገኙ ያደርጋል። እነዚህም ወንጀል እና ድህነት ዝቅተኛ የሆኑባቸው አካባቢዎች ናቸው። በከፍተኛ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶች እና የስራ ዕድሎች የተሻለ ተደራሽነትም አላቸው።
• ፌርፋክስ ካውንቲ። ካውንቲው በቤቶች ገበያ ውስጥ አድሎአዊ አሰራርን ለመለየት የሙከራ መርሃ ግብር አዘጋጀ። ሙከራዎቹን ለማካሄድ በ 2019 ከ Equal Rights Center (የእኩል መብቶች ማዕከል) ጋር ውል ፈጽሟል። ኢሜይል፣ ስልክ እና የአካል ሙከራዎችን አካተዋል። ማዕከሉ የኢሜል፣ የስልክ እና በአካል የቀረቡ ሙከራዎችን ውጤት ለመተንተን ከካውንቲ ሰራተኞች ጋር ሰርቷል። በሚከተሉት ምክሮች እና ዘገባ ላይም አብረው ሠርተዋል፦
- ከሰኔ 2019 እስከ ማርች 2021 ድረስ 122 ሙከራዎች ተደርገዋል። 93 የኪራይ ፈተናዎች ነበሩ፣ 25 በዘር ላይ፣ 55 በብሄራዊ ማንነት እና 13 በአካል ጉዳተኞች (መስማት የተሳናቸው) መሰረት ያደረጉ ነበሩ። 15ቱ የብድር እና 14 በዘር ላይ መሰረት ያደረጉ የሽያጭ ለመምራት የተካሄዱ ሙከራዎች ነበሩ።
- ኦገስት 2021 ላይ በኪራይ፣ ሽያጭ እና በብድር ገበያው ላይ 119 ሙከራዎችን ተደርገዋል
• ገይተርስበርግ ከተማ። ከተማዋ የተገደበ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች የማገልገል አቅሟን በሚከተሉት መንገዶች አሻሽላለች።
- በድረ-ገጿ ላይ ለሚገኝ መጠቀሚያ ሁሉ የ ቋንቋ ትርጉም ቁልፍ በመጨመር
- በ ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች የስራ ክፍል ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሚናገር ሰራተኛ መቅጠር
- ለሁሉም የማህበረሰብ አገልግሎቶች የገንዘብ ድጋፍ ውሎች ለባህል ትኩረት የሚሰጡ እና በብዙ ቋንቋ ማዳረስ የሚቻሉ እንዲሆኑ ማድረግ
• ሉዶን ካውንቲ። ካውንቲው ለ 2023 ፊስካል ዓመት በጀቱ የሙሉ ጊዜ የፍትሓዊ የመኖሪያ ቤቶች አስተባባሪ ቀጥሯል። ይህ ግለሰብ፦
- ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የባለንብረት ስምሪት ቡድን ማቋቋም። ቡድኑ መረጃን ያካፍላል፣ ችግሮችን ይፈታል፣ እና መኖሪያ ቤታቸውን ለማግኘት እና ወይም ያላቸውን ለማቆየት ተጨማሪ ድጋፍ ወይም አገልግሎት ለሚፈልጉ ቤተሰቦች ይበልጥ ዕድሎች እንዲያገኙ ያደርጋል።
- ካውንቲው የሎዶውን ካውንቲ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ወይም ሌላ የማስፈጸሚያ ቡድን መፍጠር የሚያስፈልገው እንሆነ እና ማቋቋም ይችል እንደሆነ ለማወቅ የሚደረግ ጥናትን መምራት
• ሞንትጎመሪ ካውንቲ። ካውንቲው የአካታች ዞን አፈጣጠር (MPDU) ፕሮግራሙን በመቀየር እንዲጠናከር አደረገ። ለውጦቹ፦
- ለተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ገንቢዎች ማበረታቻዎች እና መስፈርቶች መጨመር
- ለትንንሽ ቤቶች እኛ ከፍተኛ ጥግግት ውስጥ ለሚገነቡ እና ህዝብ ትራንዚት በቅርብ ርቀት ውስጥ የሚገነቡ ባለብዙ አገልግሎት ህንጻ ግምባታ ይበልጥ ፈቃዶች እንዲኖሩ ማድረግ
- የንግድ ተቋማት ልማት በሚካሄድበት ጊዜ ፈቃድ ለማግኘት እና ከ ካውንቲው የ አገልግሎቶች ዕቅድ የስራ ክፍል እና ከዕቅድ ቦርዱ ጋር ለመስራትን ቀላል እንዲሆን አድርጓል
• ፕሪንስ ዊሊያም ካውንቲ። ካውንቲው የፌደራል ማህበረሰብ ልማት ብሎክ ግራንት (Community Development Block Grant (CDBG) ገንዘቦችን ለሚከተሉት ተጠቅሟል፡
- የቤት እጦት የገጠማቸውን ሰዎች ለማጓጓዝ። በመጠለያዎች፣ በሕክምና ክሊኒኮች፣ በዲቶክስ መገልገያዎች፣ በሕዝብ እርዳታ ቢሮዎች እና በሌሎች የአካባቢ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል ተጓግዘዋል። ፕሮግራሙ ለአምስት ዓመታት በየዓመቱ 350 ሰዎችን አገልግሏል።
- ቤቶች እና በበጀት እና በፋይናንሺያል አስተዳደር ላይ የሚሰጡ ትምህርቶች ምዝገባ ላላቸው ወይም መግዛት ለሚፈልጉ ለሚሰጣቸው የምክር አገልግሎት ክፍያ መፈጸም። በካውንቲው የመጀመሪያ ጊዜ የቤት ገዢ ፕሮግራም በሚጠይቀው መሰረት ትምህርቶቹ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ነው የሚሰጡት።
የፍትሃዊ መኖሪያ ቤቶች ትንተና ስነ-ህዝብ-ስለ ክልላችን ነዋሪዎች
በክልልችን ውስጥ ያለው የዘር እና የብሄር ንጽጽር በመቶኛ ከ 1990 ወዲህ ተቀይሯል። የሂስፓኒክ እና የእስያ ወይም የፓሲፊክ ደሴት ህዝብ ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የሂስፓኒክ ህዝብ ቁጥር ከእጥፍ በላይ ጨምሯል፣ ነጭ የሆነው ህዝብ ግን በመቶኛ ቀንሷል።
ቡድን | በክልላችን በመቶኛ (%) | በዩናይትድ ስቴትስ በመቶኛ (%) |
ነጭ | 45,5 | 60 |
ጥቁር | 24,8 | 12 |
ሂስፓኒክ | 15,8 | 18 |
ተወላጅ አሜሪካዊ | 10 | ከ 1 በታች |
ኤሽያ አሜሪካዊ ወይም የፓስፊክ ደሴት | እስከ 10 | 6 |
ከክልሉ ህዝብ ውስጥ 9% የሚሆኑት የአካል ጉዳት አለባቸው። እጅግ በጣም የተለመዱት የሚከተሉት ናቸው፦፡
• አምቡላቶሪ - ሰዎች ለመራመድ ወይም ደረጃዎችን ለመውጣት አስቸጋሪ የሚያደርግ
• የብቸኝነት ኑሮ- የዕለት ተግባራት ለማከናወን፣ ዕቃ ለመግዛት ወይም ወደ ዶክተር ቀጠሮ ለመሄድ ከባድ ማድረግ
• የእውቀት (ኮግኒቲቭ) እክል - ለማስታወስ, ለማተኮር ወይም ውሳኔዎችን ለመወሰን አስቸጋሪ ያደርግ ማድረግ1
በክልላችን የሚኖሩ የውጭ ተወላጆች ቁጥርም በመቶኛ ከ1990 ጀምሮ በእጥፍ ጨምሯል። የሚከተሉት ያክትታሉ፦፡
• 200,000 ኤልሳልቫዶር የተወለዱ
• 100,000 ህንድ የተወለዱ
• እስከ 75,000 የሚሆኑ ቻይና የተወለዱ
• ከ 40,000 እስከ 60,000 የሚሆኑ ከኮሪያ እና ከኢትዮጵያ የሆኑ
በሌሎች አገሮች ውስጥ የተወለዱ የክልላችን ነዋሪዎች ቁጥር እድገት ውስን የእንግሊዘኛ ችሎታ (Limited English Proficiency (LEP)) ያላቸው ሰዎች ቁጥር መጨመር አስተዋጽኦ አድርጓል። እንግሊዝኛ የመናገር፣ የማንበብ ወይም የመረዳት አቅማቸው ውስን ነው። በመላው ክልል፣ የስፓኒሽ ቋንቋ በLEP ህዝብ በብዛት የሚነገር ቋንቋ ነው። ሌሎች ከፍተኛ ተናጋሪ ያላቸው 10 LEP ቋንቋዎች በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው፦
• ሌሎች የኢንዶ-ዩሮፒያን ቋንቋዎች (ከስፓኒሽ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ውጪ)
• ቻይንኛ (ማንዳሪን እና ካንቶኒንስን ጨምሮ)
• ሌሎች ያልተለዩ ቋንቋዎች
• ኮሪያኛ
• ቬትናምኛ
• ሌሎች የኤሽያ እና የፓስፊክ ደሴቶች ቋንቋዎች
1 xxxxx://xxx.xxxxxx.xxx/xxxxxx/xxxxxx/xxxxxxxxxx/xxxxxxxx/xxxx-xxxxxxxxxx-xxx.xxxx
• ፈረንሳይኛ
• የሃይቲ ቋንቋ ወይም ካጁን
• ዓረብኛ
• ታጋሎግ ቋንቋ ( ፊሊፒኖን ጨምሮ)
እያንዳንዳቸው በዕቅዱ ውስጥ ያሉ የአከባቢ ቋንቋዎች እና መላው ክልል ውስጥ የወንድ እና የሴት ቁጥር ንጽጽር ተመሳሳይ ነው። በክልሉ ውስጥ፦
• ዕድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች (12.7 በመቶ) ከUS (15.6 በመቶ) በመጠኑ ያነሰ ነው።2
• 46.1 በመቶ የሚሆኑት ቤተሰቦች (ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሚዛመዱ እና አብረው የሚኖሩ) ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች አሏቸው።
• የ5-ዓመቱ የአሜሪካ ማህበረሰብ ጥናት (በዩኤስ የህዝብ ቆጠራ ቢሮ) ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች መቶኛ ከ2010 እስከ
2019 ባለው ጊዜ ውስጥ በመጠኑ የተረጋጋ መሆኑን አሳይቷል። አሁን ግን ከ1990 መቶኛ ያነሰ ነው።
ለተለየ የስነ-ሕዝብ ትንተና፣ ወደ የክልል ፍትሃዊ መኖሪያ ቤት እቅድ የስነ-ሕዝብ ማጠቃለያ ክፍል ይሂዱ። መለያየት
በክልላችን ውስጥ መለያየት እየጨመረ ነው። የ “ልዩነት መረጃ ጠቋሚ” በመኖሪያ ቤቶች ያለን መለያየት ይለካል። በሌላ አገላለጽ፣ ሁለት የተለያዩ ቡድኖች በከተማ አካባቢ ውስጥ ምን ያህል እኩል ባልሆነ መንገድ የተከፋፈሉ መሆናቸውን ያሳያል። የመረጃ ጠቋሚው ከፍ ባለ መጠን ሁለቱ ቡድኖች የበለጠ ተለያይተዋል ማለት ነው።
በጥቁር እና በነጭ ነዋሪዎች መካከል ከፍተኛ የመለያየት ደረጃ አለን። በሂስፓኒክ እና በነጮች መካከል ያለው ልዩነት መካከለኛ ነው። ለፓስፊክ ደሴት ነዋሪዎች እና ነጮችም ይህ ልዩነት ተመሳሳይ ነው። ነገር ግን ለሁሉም ቡድኖች፣ ከ2010 ጀምሮ የልዩነት መረጃ ጠቋሚው ከፍ እያለ ነው።
“የመነጠል መረጃ ጠቋሚ” የሚለካው በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ያህል በተመሳሳይ ቡድን ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር ብቻ እንደሚኖሩ ነው።3 መረጃ ጠቋሚው ለነጭ እና ጥቁር ነዋሪዎች ከፍተኛ ነው። እያንዳንዱ ቡድን በቡድናቸው ውስጥ ካሉት ጋር የመኖር እድላቸው ሰፊ ነው። ነገር ግን ነጭ ነዋሪዎች ከፍተኛው ክልላዊ የመነጠል መረጃ ጠቋሚ አሃዝ አላቸው። የእስያ ወይም የፓሲፊክ ደሴት ነዋሪዎች ዝቅተኛው አላቸው።
“የተጋላጭነት መረጃ ጠቋሚ” ከተለያዩ ዘር እና ጎሳዎች የተውጣጡ ሰዎች ባሉበት ማህበረሰቦች ውስጥ ምን ያህል ሰዎች እንደሚኖሩ ይለካል።4 በክልላችን ያለውን የመኖሪያ መለያየትን ስንለካ ይህ መረጃ ጠቋሚ እንደ ልዩነት እና መነጠል መረጃ ጠቋሚዎች ተመሳሳይ ውጤቶችን ይሰጣል። ለምሳሌ፣ ነጭ ነዋሪዎች ከሁሉም አናሳ ቡድኖች ጋር ሲነፃፀሩ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ተጋላጭነት አላቸው። ይህም ማለት የተለያየ ዘር ወይም ጎሳ ያሏቸው ማህበረሰቦች ውስጥ የመኖር ዕድላቸው አነስተኛ ነው።
አንድ ሰው የሚኖርበት ቦታ በአእምሮ እና በአካላዊ ጤንነት፣ በትምህርት፣ በወንጀል እና ኢኮኖሚያዊ እድል ተጋላጭነት ላይ ትልቅ ተጽእኖ አለው። በዘር እና በገቢ የተከፋፈሉ የከተማ አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች በኢኮኖሚ የማደግ እድላቸው አነስተኛ ነው። ብዙ የምርምር ጥናቶች እንደሚያሳዩት የዘር ልዩነት ይበልጥ እንዲከፋ ያደረገው የመኖሪያ መለያየት ነው። በአንድ አከባቢ ያለ ከፍተኛ የድህነት መጠን ከፍ ያለ የወንጀል መጠን እና የከፋ የጤና ውጤቶችን ሊያስከትል ይችላል።
2 xxxxx://xxxx.xxxxxx.xxx/xxxxxx/xxxxx?xxxxxxxxx%00xxxxxxxxxx%00xx%00xx%00xx%000000&xxXXX%000- Year%20Estimates%20Data%20Profiles
3 xxxxx://xxx.xxxxxx.xxx/xxxxxx/xxxxxxx/xxxxxxx-xxxxxxxx/xxxxxxxx/xxxxxxxx-x.xxxx
4 xxxxx://xxx.xxxxxxxxx.xxx/xxxxxxxxxxxx/XxxxxxxxxXxxxxxxxxxx.xxx
ሆኖም እነዚህ አካባቢዎች በሌሎች አካባቢዎች የማይገኙ እድሎችን ሊሰጡ ይችላሉ። አንዳንድ ግለሰቦች የዘር ወይም የጎሳ ክምችት ያሉባቸው ድሃ አከባቢዎችን ይመርጣሉ (ሣጥን 2 ይመልከቱ)። እነዚህ የዘር ወይም የጎሳ ክምችት ያሉባቸው ድሃ አከባቢዎች (R/ECAPs) የሚከተሉትን ያቀርቡላቸዋል፦
• የሥራ ማዕከላት።
• ሌሎች የጎሳቸውን አባላት። ይህ በተለይ ለስደተኞች አስፈላጊ ነው። የማህበረሰብ እና የድጋፍ ስሜት በዩኤስ ውስጥ ካለው ህይወት ጋር እንዲላመዱ ሊረዳቸው ይችላል።
• ባህላዊ ማንነታቸውን ለመጠበቅ የሚረዱ ንግዶች፣ ማህበራዊ አውታረ መረቦች እና ተቋማት።
• በአዲስ መኖሪያቸው ውስጥ እራሳቸውን ለማቋቋም የሚያስፈልጓቸው አገልግሎቶች።
የመኖሪያ መለያየትን ጉዳቶች በተመለከተ የምርምር ጥናቶች ዝርዝር ለማግኘት የክልል ዕቅድ አባሪውን ይመልከቱ።
ሳጥን 2
የዘር ወይም የጎሳ ክምችት ያሉባቸው ድሃ አከባቢዎች (R/ECAPs)
HUD (የቤቶች እና የከተማ ልማት መምሪያ) የትኛዎቹ አካባቢዎች እንደ R/ECAPs ለመቆጠር ብቁ እንደሆኑ ለመወሰን ቀመር ይጠቀማል። ጉልህ የሆኑ የድህነት ደረጃዎች እና የቀለም ሰዎች ሊኖሯቸው ይገባል። ቀደም ባሉት ጊዜያት የፌደራል የመኖሪያ ቤት መመሪያዎች እንደ ኮሎምቢያ ዲስትሪክት ካሉ ከተሞች ነጮች እንዲለቁ፣ በዚህም የተከፋፈሉ የከተማ ዳርቻዎች እንዲፈጠሩ አድርገዋል።
▪ በክልላችን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ R/ECAPዎች በዲስትሪክቱ እና በዋነኛነት የጥቁር ነዋሪዎች አካባቢዎች ውስጥ ናቸው።
▪ ጥቁሮች ከክልሉ ህዝብ አንድ አራተኛ ሲሆኑ 80% የR/ECAP ነዋሪዎች ናቸው።
▪ እዚያ ከሚኖሩት ቤተሰቦች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ልጆች አሏቸው።
▪ ከ 5% በላይ የሚሆኑት ነዋሪዎች ከኤል ሳልቫዶር እና ከሌሎች የመካከለኛው አሜሪካ አገሮች የመጡ ናቸው።
ምስራቃዊ ሞንትጎመሪ ካውንቲ፣ ደቡብ ምስራቅ ፌርፋክስ ካውንቲ እና ምስራቃዊ ፕሪንስ ዊሊያም ካውንቲ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ህዝቦች ያሏቸው በዘር እና በጎሳ የተለያዩ አካባቢዎች አሏቸው። ነገር ግን በእነዚህ አካባቢዎች ያለው የድህነት ደረጃ የHUDን የR/ECAPs መስፈርት በሚያሟላ መልኩ ዝቅተኛ አይደለም።
ዕድል
የክልላዊ ፍትሃዊ መኖሪያ ቤት እቅድ አንዳንድ ሰዎች በዘራቸው፣ በጎሣቸው እና በሚኖሩበት አካባቢ ምክንያት ከሌሎች ያነሰ እድል ያላቸው እንደሆን ይመለከታል። ዕድሉ የጥሩ ትምህርት ቤቶችን፣ ስራዎችን እና መጓጓዣን ተደራሽነት ያካትታል። በጤናማ፣ ዝቅተኛ ድህነት ባለባቸው አካባቢዎች የመኖር እድልም ነው።
ትምህርት ቤቶች
• በክልሉ ውስጥ ያሉ ነጮች ጥሩ ትምህርት ቤቶች የማግኘት ከፍተኛው ዕድል አላቸው፣5 በመቀጠል የሚገኙት የእስያ አሜሪካውያን ነዋሪዎች ናቸው።
• የጥቁር እና የሂስፓኒክ ነዋሪዎች፣ በተለይም ከድህነት ወለል በታች የሆኑት ጥሩ ትምህርት ቤቶችን የማግኘት እድል አነስተኛ ነው።
• የጥሩ ትምህርት ቤቶች ተደራሽነት በክልላችን በሚኖሩበት ቦታ ጭምር ይወሰናል፡
‒ የበለጠ ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸው ትምህርት ቤቶች በከተማ ዳርቻዎች ውስጥ - በተለይም በሎዶውን፣ ፌርፋክስ እና ሞንትጎመሪ ካውንቲዎች ይገኛሉ። በዚያ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአብዛኛው ነጭ ወይም በመጠኑም ቢሆን እስያዊ አሜሪካዊ ናቸው።
‒ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው ትምህርት ቤቶች ብዙ ቁጥር ያላቸው ጥቁር እና ሂስፓኒክ ነዋሪዎች ባሉባቸው የከተማ አካባቢዎች የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው። እነሱም የኮሎምቢያ ዲትሪክት እና የአሌክሳንድሪያ እና አርሊንግተን የከተማ አካባቢዎችን ያካትታሉ።
ስራዎች
• የእስያዊ አሜሪካዊ እና ነጭ ነዋሪዎች ከጥቁር፣ የሂስፓኒክ እና ተወላጅ አሜሪካኖች የበለጠ ስራ የማግኘት ወይም በንቃት ስራ የመፈለግ ዕድላቸው ሰፊ ነው።
• በዲስትሪክቱ ወይም በአጎራባች ካውንቲዎች የሚኖሩ ሰዎች በሌሎች አካባቢዎች ከሚኖሩት ይልቅ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ምክንያቶቹም ብዙ ስራዎች እና የመጓጓዣ አማራጮች መኖር ነው።
መጓጓዣ
• በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ካሉት ሰዎች የበለጠ ርካሽ የመጓጓዣ አገልግሎት ያገኛሉ።
• ነጭ ነዋሪዎች - እና በተለይም ድሆች - ዝቅተኛ ዋጋ ያለው መጓጓዣ የማግኘት ዕድላቸው ከሌሎች ያነሰ ነው። አንደኛው ምክንያት በከተማ ዳርቻዎች ውስጥ የመኖር እድላቸው ሰፊ መሆኑ ነው። እና እነዚህ አካባቢዎች ከዲስትሪክቱ ያነሰ የመጓጓዣ አማራጮች አሏቸው።
መኖሪያ ቤት
• በዝቅተኛ የድህነት አከባቢዎች ተደራሽነት ላይ ያለው ልዩነት በክልሉ እና በእያንዳንዱ በውስጡ ያሉ አካባቢዎች ተመሳሳይ ነው።
• ነጭ ነዋሪዎች ከሌሎች ቡድኖች - በተለይም ከጥቁሮች እና ከሂስፓኒኮች አንፃር በዝቅተኛ ድህነት ውስጥ የመኖር እድላቸው ሰፊ ነው።
• በዲስትሪክቱ እና በፌርፋክስ ውስጥ ለሚገኙ ጥቁር ነዋሪዎች የእነዚህ አካባቢዎች ተደራሽነት በጣም አነስተኛ ነው።
• የሂስፓኒክ ነዋሪዎች በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች ውስጥ አነስተኛው ተደራሽነት አላቸው።
ጤናማ አካባቢዎች (አነስተኛ ብክለት ያለባቸው አካባቢዎች)
• ነጭ ነዋሪዎች የክልላችን ጤናማ ቦታዎችን በብዛት ያገኛሉ። ይህም ከተወላጅ አሜሪካውያን፣ እስያዊ አሜሪካውያን ወይም የፓሲፊክ ደሴት ነዋሪዎች እና የሂስፓኒክ እና ጥቁር ነዋሪዎች ጋር ሲነጻጸር ነው።
• ይህ ተደራሽነት በሁሉም ቡድኖች በድህነት ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ተመሳሳይ ነው።
• የሉዶን እና የፕሪንስ ዊሊያም ካውንቲዎች ይበልጥ የከተማ ዳርቻ እና ገጠራማ አካባቢዎች በክልሉ ውስጥ ለመኖር በጣም ጤናማ ቦታዎች ናቸው። ነዋሪዎች በአብዛኛው ነጭ ናቸው።
• ዲስትሪክቱ፣ አርሊንግተን እና አሌክሳንድሪያ ዝቅተኛው መዳረሻ አላቸው።
5 የጥሩ ትምህርት ቤቶች ተደራሽነት፣ በግዛቱ የብቃት ፈተናዎች ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች ባሉባቸው ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተመሰረተ ነው።
• ከ2019 ጀምሮ ለሁሉም ነዋሪዎች የጤናማ አካባቢዎች ተደራሽነት በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሏል። ምክንያቱ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በተሳፋሪዎች መቀነስ ምክንያት የብክለት መጠን ያነሰ መሆኑ ሊሆን ይችላል።
ዘር እና ጎሳ በክልላችን የነዋሪዎች የማግኘት እድል ላይ ጉልህ ልዩነቶችን ይፈጥራሉ። ማጠቃለያውን ሣጥን 3 ላይ ይመልከቱ። ተደራሽነት ከነጮች ይልቅ ለጥቁር እና ለሂስፓኒክ ነዋሪዎች ሁልጊዜ ያነሰ ነው። ይህ በመጠኑም ቢሆን ለእስያዊ አሜሪካውያን እውነት ነው። ተወላጅ አሜሪካውያን ከአንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች ውጪ ብዙውን ጊዜ መካከል ላይ ያርፋሉ። ነገር ግን እነዚህ ልዩነቶች ከድህነት ወለል በታች ለሚኖሩ ሰዎች የከፉ ናቸው።
ሳጥን 3
በዘር እና በጎሳ መሰረት የእድሎች ተደራሽነት
ብዙ መዳረሻ ያሏቸው ቡድኖች ከእያንዳንዱ እድል በኋላ መጀመሪያ ተዘርዝረዋል። አነስተኛ መዳረሻ ያላቸው በመጨረሻ ተዘርዝረዋል።
▪ ትምህርት ቤቶች፦ ነጭ፣ እስያዊ፣ ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ሂስፓኒክ፣ ጥቁር።
▪ ስራዎች፦ እስያዊ፣ ነጭ፣ ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ሂስፓኒክ፣ ጥቁር።
▪ ስራዎችን የማግኘት ዕድል፦ እስያዊ፣ ነጭ፣ ሂስፓኒክ፣ አሜሪካዊ፣ ጥቁር።
▪ የመጓጓዣ መረጃ ጠቋሚ፦ (ምን ያህል ተደጋጋሚ እና ወዳጃዊ፣ በማቆሚያዎች መካከል ያለው ርቀት፣ ግንኙነቶች) ሂስፓኒክ፣ እስያዊ፣ ጥቁር፣ ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ነጭ።
▪ የመጓጓዣ ወጪዎች፦ በግምት ለሁሉም ተመሳሳይ።
▪ ዝቅተኛ የድህነት አከባቢዎች፦ ነጭ፣ እስያዊ፣ ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ሂስፓኒክ፣ ጥቁር።
▪ አካባቢ (የብክለት ደረጃ)፦ ነጭ፣ ተወላጅ አሜሪካዊ፣ እስያዊ፣ ሂስፓኒክ፣ ጥቁር።
መኖሪያ ቤት የተለመዱ ችግሮች
ከክልሉ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ቤተሰቦች ውስጥ አንድ ሶስተኛው አንድ ወይም ከዚያ በላይ እነዚህ በ HUD የተሰየሙ የቤት ችግሮች አሉባቸው፦
1. ያልተሟሉ የወጥ ቤት መገልገያዎች
2. ያልተሟሉ የቧንቧ እቃዎች
3. መጨናነቅ
4. ከፍተኛ ወጪ (የገቢን 30% ወይም ከዚያ በላይ ለቤት ወጪዎች ማውጣት)።6
6 HUSUER, CHAS: https://www.huduser.gov/portal/datasets/cp/CHAS/bg_chas.html
ቀለም ያላቸው ቤተሰቦች -- በተለይም የሂስፓኒክ እና ጥቁር ቤተሰቦች፣ የበለጠ የመኖሪያ ቤት ችግር አለባቸው። ይህ ቤተሰብ ላልሆኑ ነዋሪዎች (ዝምድና የሌላቸው፣ አብረው የሚኖሩ) እና አምስት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ቤተሰቦችም እንዲሁ እውነት ነው። ለበለጠ መረጃ ሠንጠረዥ 1ሐ ላይ ይመልከቱ። በክልል ደረጃ፣ 25% ነጭ ቤተሰቦች እና ቀለም ካላቸው ሶስት ቤተሰቦች መካከል አንዱ ቀለም ያለው ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት ችግር አለባቸው።
ይህ አካሄድ ከባድ የመኖሪያ ቤት ችግር ላለባቸው ቤተሰቦች ቀጥሏል። ሠንጠረዥ 1ሐ ላይ ይመልከቱ። ችግሮቹ የወጥ ቤት ወይም የቧንቧ አለመኖርን ያካትታሉ። በአንድ ክፍል ውስጥ ከአንድ ሰው በላይ መኖር ወይም የቤተሰብ ገቢ 50% ወይም ከዚያ በላይ የቤት ወጪዎች መኖር እንዲሁ እንደ ከባድ ችግሮች ይቆጠራሉ።
የሂስፓኒክ ቤተሰቦች በክልሉ ውስጥ ካሉ ነጮች ይልቅ ለከባድ የመኖሪያ ቤት ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው በሦስት እጥፍ ይበልጣል። ጥቁር ቤተሰቦች እና ተወላጅ አሜሪካውያን እነዚህን ችግሮች የመጋፈጥ እድላቸው ከሁለት እጥፍ ይበልጣል።
ሠንጠረዥ 1ሐ፦ ያልተመጣጠነ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች ስነ-ሕዝብ፣ ክልል
ከ 4 የቤት ችግሮች ውስጥ የትኛውም ያጋጠማቸው ቤተሰቦች | # ከችግሮች ጋር | # ቤተሰቦች | % ከችግሮች ጋር |
ዘር/ብሔር | |||
ነጭ፣ ሂስፓኒክ ያልሆነ | 290,379 | 1,146,249 | 25.33% |
ጥቁር ወይም ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 228,930 | 547,575 | 41.81% |
ሂስፓኒክ | 116,643 | 229,029 | 50.93% |
ኤሽያ ወይም የፓስፊክ ደሴቶች፣ ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 63,849 | 184,508 | 34.61% |
ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ሂስፓኒክ ያልሆነ | 1,912 | 4,987 | 38.34% |
ሌሎች፣ ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 18,138 | 48,608 | 37.31% |
አጠቃላይ | 719,855 | 2,160,990 | 33.31% |
የቤተሰብ ዓይነት እና መጠን | |||
የቤተሰብ ቤቶች፣ <5 ሰዎች | 331,440 | 1,195,683 | 27.72% |
የቤተሰብ ቤቶች፣ 5+ ሰዎች | 95,644 | 230,517 | 41.49% |
ቤተሰብ ያልሆኑ ቤቶች | 292,760 | 734,793 | 39.84% |
ከ 4 አንዱን ከባድ የሆነ የቤት ችግር እየገጠማቸው የሚገኙ ቤተሰቦች | # ከባድ ችግሮች | # ቤተሰቦች | % ከባድ ችግሮች ያሉባቸው |
ዘር/ብሔር | |||
ነጭ፣ ሂስፓኒክ ያልሆነ | 125,471 | 1,146,249 | 10.95% |
ጥቁር ወይም ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 116,013 | 547,575 | 21.19% |
ሂስፓኒክ | 68,070 | 229,029 | 29.72% |
ኤሽያ ወይም የፓስፊክ ደሴቶች፣ ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 33,791 | 184,508 | 18.31% |
ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ሂስፓኒክ ያልሆነ | 1,040 | 4,987 | 20.85% |
ሌሎች፣ ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 8,829 | 48,608 | 18.16% |
አጠቃላይ | 353,250 | 2,160,990 | 16.35% |
የመኖሪያ ቤት ዋጋ
የመኖሪያ ቤት ዋጋ በክልላችን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል። እሱም፡
• በ ጥቁር፣ ሂስፓኒክ እና ተወላጅ አሜሪካዊ የሆኑ ቤተሰቦችን ይበልጥ ከባድ የሆነ ችግር ይፈጥርባቸዋል (ሰንጠረዥ 1d)
• ብዙ ቁጥር ያላቸው የኤሽያ ወይም የፓስፊክ ደሴት ቤተሰቦች ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል
• ከሌሎች በበለጠ ቤተሰብ ያልሆኑ ቤቶች ላይ ይበልጥ ተጽዕኖ ይፈጥርባቸዋል
• ትንሽ ቤተሰብ ያላቸው ቤቶች አነስ ያለ የቤት ዋጋ ችግር ያጋጥማቸዋል።
ሠንጠረዥ 1መ ከባድ የሆነ የመኖሪያ ቤት ችግር ያለባቸው የቤተሰቦች የሰነ-ህዝብ መግለጫ፣ በክልል
ዘር/ብሔር | # ከባድ የዋጋ ችግሮች | # ቤተሰቦች | # ከባድ የዋጋ ችግሮች ያሉባቸው |
ነጭ፣ ሂስፓኒክ ያልሆነ | 112,920 | 1,146,249 | 9.85% |
ጥቁር ወይም ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 100.254 | 547,575 | 18.31% |
ሂስፓኒክ | 45,579 | 229,029 | 19.90% |
ኤሽያ ወይም የፓስፊክ ደሴቶች፣ ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 25,257 | 184,508 | 13.69% |
ተወላጅ አሜሪካዊ፣ ሂስፓኒክ ያልሆነ | 809 | 4,987 | 16.22% |
ሌሎች፣ ሂስፓኒክ ያልሆኑ | 7,588 | 48,608 | 15.61% |
አጠቃላይ | 292,407 | 2,160,990 | 13.53% |
የቤተሰብ ዓይነት እና መጠን | |||
የቤተሰብ ቤቶች፣ <5 ሰዎች | 130,274 | 1,195,683 | 10.90% |
የቤተሰብ ቤቶች፣ 5+ ሰዎች | 25,636 | 230,517 | 11.12% |
ቤተሰብ ያልሆኑ ቤቶች | 136 547 | 734,793 | 18.58% |
አከራዮች
ተከራዮች ከባለቤቶች ይልቅ ለከባድ የመኖሪያ ቤት ችግር የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው። ከአንድ ሚሊዮን በላይ በባለቤት ከተያዙ ቤተሰቦች ውስጥ፡
• ከ 75% በላይ የሚሆኑት ከባድ የመኖሪያ ቤት ችግር አይገጥማቸውም
• ከ 1% ያነሱ ሁለት፣ ሶስት ወይም አራት ከባድ ችግሮች አሏቸው
• ከ 50% በላይ የሚሆኑት ምንም አይነት ከባድ የመኖሪያ ቤት ችግር የለባቸውም
• ወደ 4% ገደማ የሚሆኑት ሁለት፣ ሶስት ወይም አራት ከባድ ችግሮች አሏቸው
• በአሌክሳንድሪያ፣ አርሊንግተን እና ሉዶን ካውንቲዎች ያሉ ተከራዮች ለከፋ የመኖሪያ ቤት ችግር የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው።
• በጋይተርስበርግ፣ በሞንትጎመሪ እና በፕሪንስ ዊልያም ካውንቲ ውስጥ ካሉ ሁሉም ተከራዮች 50% ገደማ የሚሆኑት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ከባድ የመኖሪያ ቤት ችግሮች አሉባቸው
ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው አብዛኛዎቹ የክልሉ የኪራይ ቤተች በከተማው አካባቢ ዳርቻ ላይ ይገኛሉ። እነዚህም “የድጎማ” ኪራዮችን ያካትታሉ - ተከራዩ ኪራዩን ለመክፈል የገንዘብ እርዳታ ይቀበላል። በማዕከላዊ አካባቢዎች ያሉ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶች በ R/ECAP አካባቢዎች የመሆን አዝማሚያ አላቸው።
የቤት ባለቤቶች
በክልሉ ውስጥ ቢያንስ 50% ቤተሰቦች የቤት ባለቤት ናቸው። 73% የቤት ባለቤቶች ነጭ ናቸው። እስያዊ አሜሪካውያን ቤተሰቦች በ67 በመቶ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ናቸው። በበርካታ ካውንቲ ውስጥ የሂስፓኒክ ቤተሰቦች ከጥቁር ቤተሰቦች የበለጠ የቤት ባለቤትነት መጠን አላቸው። ነገር ግን በጠቅላላው ክልል ውስጥ ዝቅተኛው ደረጃ አላቸው።
የሕዝብ የቤት ድጋፍ ትንተና
ፍላጎቱን ለማሟላት በክልሉ ውስጥ የህዝብ ድጋፍ ያላቸው በቂ ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤቶች የሉም። ይህ በተለይም ለቤተሰቦች እውነት ነው። በግምት 4% የሚሆኑ ቤተሰቦች በፌዴራል ተከራይ-ተኮር ወይም በፕሮጀክት ላይ በተመሰረቱ ድጎማዎች በሚታገዙ ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ። በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች፣ የቤቶች ምርጫ ቫውቸር መርሃ-ግብር ለተቸገሩ ቤተሰቦች ትልቁን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ያቀርባል። ግን ይህ መርሃ-ግብር ብቻውን በቂ አይደለም።
Project-Based Section 8 units ብዙም ወይም አንዳንድ ጊዜ ምንም የመኖሪያ ቤት እድሎችን ለቤተሰቦች አያቀርብም። እንዲሁም ብዙዎቹ ግንባታዎች ለአዛውንቶች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ። የሕዝብ መኖሪያ ቤት ሌላው የእርዳታ ቤት ምንጭ ነው። ነገር ግን አብዛኛዎቹ የክልላችን አካባቢዎች ምንም አይነት የህዝብ መኖሪያ ቤቶች የላቸውም።
ነዋሪዎች
ለቤቶች ምርጫ ቫውቸር መርሃ-ግብር የክልል የስነ ሕዝብ መረጃ አይገኝም።ግን ለአንዳንድ በይፋ ለሚደገፉ መርሃ ግብሮች ይገኛል። በሕዝብ፣ በ project-based Section 8 እና በሌሎች የባለብዙ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ያለው መረጃ የሚነግረን፡
• በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ከሚኖሩት ውስጥ ጥቁር ቤተሰቦች ከፍተኛው መቶኛ ናቸው።
• ነጭ ቤተሰቦች ሁለተኛውን ከፍተኛ ደረጃ ይይዛሉ።
• የሂስፓኒክ ቤተሰቦች ሶስተኛውን ከፍተኛ ደረጃ ይይዛሉ።
• የእስያ ወይም የፓሲፊክ ደሴት ቤተሰቦች የህዝብ መኖሪያ ቤቶችን የመያዝ እድላቸው አነስተኛ ነው።
አካባቢ
የሕዝብ መኖሪያ ቤት ብዙ ነጭ ሕዝብ ባለባቸው ቦታዎች የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው። እነዚህም የክልላችንን ምዕራባዊ እና ደቡባዊ ክፍሎችን ያጠቃልላል። ይልቁንም የሕዝብ መኖሪያ ቤቶች በክልሉ ምስራቃዊ ክፍል የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው።
ይህም ብዙዎቹን የህዝብ መኖሪያ ቤቶች በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ጥቁር ነዋሪዎች በከፍተኛ መቶኛ ላሉባቸው አካባቢዎች ወይም አቅራቢያዎች ቅርብ ያደርገዋል። የቤቶች ምርጫ ቫውቸር ባለቤቶችም በእነዚህ አካባቢዎች የመኖር አዝማሚያ አላቸው። እንዲሁም በዚያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ጥሩ ትምህርት ቤቶች፣ ስራዎች እና ጤናማ አካባቢዎች የማግኘት እድል አናሳ ነው።
አካል ጉዳተኝነት እና ተደራሽነት ሕጉ
የፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ህጉ ሰዎችን ከመኖሪያ ቤት ጋር በተያያዘ ከሚኖር አድልዎ ይጠብቃል። በ1988 ምክር ቤቱ አካል ጉዳተኞችን ለማካተት ህጉን አሰፋ። ይህም ሆን ተብሎ ከሚደረግ አድልዎ እና በአካለ ጎደሎነታቸው ምክንያት የበለጠ ተፅዕኖ ከሚያደርሱባቸው መመሪያዎች ይጠብቃቸዋል። ሕጉ ሦስት ነገሮችን ይጠይቃል፦
1. አንድ አካል ጉዳተኛ ሲጠይቅ እና እና ቤቱን ለመጠቀም እና ተደስቶ ሊኖርበት ሲፈልግ ተገቢ የሆኑ ማመቻቸቶችን ማቅረብ። ምሳሌ፡ በሰፊው የሚተገበረው “የቤት እንስሳ አይፈቀድም” መመሪያ ቢኖርም፣ የጭንቀት መታወክ ላለበት ሰው ስሜታዊ ድጋፍ የሚሰጠው ውሻ እንዲኖረው መፍቀድ።
2. በተጠየቀ እና ባስፈለገ ጊዜ ተገቢ ማሻሻያዎች። ምሳሌ፡ መወጣጫ መጨመር፣ የበር ፍሬም ማስፋት ወይም ሌሎች ተከራዩ የሚፈልጋቸው ለውጦች። ተከራዮች ለእነዚህ መክፈል ሊኖርባቸው ይችላል።
3. ከ1991 ጀምሮ በተገነቡ የባለ ብዙ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ አስፈላጊውን ተደራሽነት ማቅረቢያ የተወሰኑ ባህሪዎች።
ፍላጎት
ብዙ የክልላችን ነዋሪዎች ተደራሽ መኖሪያ ያስፈልጋቸዋል።
• ከ 2.5 እስከ 6.1% የሚሆኑት መራመድ ወይም ደረጃዎችን መውጣት አስቸጋሪ የሚያደርግ አካል ጉዳት አለባቸው7
• ከ2 እስከ 4% የሚሆኑት የማየት ችግር አለባቸው
• ከ2 እስከ 3 በመቶ የሚሆኑት የመስማት ችግር አለባቸው
በእነዚህ ቁጥሮች መሰረት ከ100,000 እስከ 300,000 የሚደርሱ ተደራሽ መኖሪያ ቤቶች እንፈልጋለን። አካል ጉዳተኞች ዝቅተኛ ገቢ ሊኖራቸው ስለሚችል ብዙዎቹ ባለተመጣጣኝ ዋጋ መሆንም አለባቸው። በአጠቃላይ፣ ክልሉ እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ብዙ ይቀረዋል - ይህም በጣም ትንሽ ወይም ምንም ባለብዙ ቤተሰብ ወይም የህዝብ መኖሪያ በሌሏቸው በተለይም እንደ ሉዶን እና ፕሪንስ ዊሊያም ካውንቲ ባሉ ውጫዊ የከተማ ዳርቻ ማህበረሰቦች ውስጥ እውነት ነው።
የተደራሽ መኖሪያ ቤት መስፈርቶች
በፌዴራል ዶላሮች የሚደገፉ አንዳንድ የቤት ፕሮጀክቶች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተወሰኑ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። ለምሳሌ ያህል፦
• በፌዴራል የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ውስጥ 5% የሚሆኑት ቤቶች የእንቅስቃሴ እክል ላለባቸው ግለሰቦች ተደራሽ መሆን አለባቸው
• 2% የሚሆኑት የመስማት ወይም የማየት እክል ላለባቸው ግለሰቦች ተደራሽ መሆን አለባቸው
በፌዴራል የዝቅተኛ ገቢ የመኖሪያ ቤት ታክስ ቅናሽ የሚደገፉ ፕሮጀክቶች አነስተኛ የተደራሽነት መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። እነዚህ መመዘኛዎች በፌዴራል የገንዘብ እርዳታ ከሚደገፉ ሌሎች የመኖሪያ ቤት ዓይነቶች ያነሱ ናቸው።
7 https://www.census.gov/topics/health/disability/guidance/data-collection-acs.html
በክልላችን ውስጥ ተደራሽ መኖሪያ ቤቶች
ከ 2000 ጀም ሮ አምስት ወይም ከዚያ በላይ ክፍሎች ባሉት ሕንፃዎች ውስጥ ወደ 156,637 ክፍሎች ተገንብተዋል። ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት ለማረጋገጥ የፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ህግን ንድፍ እና የግንባታ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
ነገር ግን በክልላችን ውስጥ ያሉ አንዳንድ የቆዩ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ተደራሽ እንዲሆኑ ለውጦችን ሊፈልጉ ይችላሉ። በ1980 እና 1999 መካከል 176,137 ክፍሎች ተገንብተዋል። በ1991 ውስጥ ወይም በኋላ ምን ያህል እንደተገነቡ አናውቅም። የሕጉ መመዘኛ መስፈርተች ተግባራዊ የሆኑት በዚህ ጊዜ ነበር። ከእነዚህ ክፍሎች አንዳንዶቹ የፌዴራል የገንዘብ እርዳታ እንደተቀበሉ እናውቃለን። የተደራሽነት ከፍተኛ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ይጠየቁ ነበር።
አብዛኛው የሕዝብ መኖሪያ ቤት በኮሎምቢያዲስትሪክት ውስጥ ነው። እና የህዝብ መኖሪያ ቤቶች ተደራሽ የሆኑ ክፍሎች ሊኖራቸው የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው። ነገር ግን ዲስትሪክቱ፣ የፌርፋክስ ካውንቲ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ይበልጥ የተለያዩ፣ የተዋሃዱ ማህበረሰቦችን ለመገንባት እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። ይህ በክልል ደረጃ የበለጠ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ ቤቶችን መፍጠር ጀምሯል። እያንዳንዱ የቤት ልማት ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች ተመጣጣኝ የሆኑ አዳዲስ ክፍሎችን በመቶኛ መመደብ አለበት።
የአእምሮ፣የእድገት እና የስነ-ልቦና እክል ያለባቸውን ነዋሪዎች መለያየት
ቨርጂኒያ፣ ሜሪላንድ፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት እና ሌሎች መንግስታት እ.ኤ.አ. እስከ 1960ዎቹ እና 1970ዎቹ ድረስ እነዚህን አካል ጉዳተኞች በመንግስት በሚተዳደሩ ትላልቅ ተቋማት ውስጥ አስቀመጡ። ትንሽ ነፃነት የነበራቸው ሲሆን አካል ጉዳተኛ ካልሆኑ ሰዎች ጋር የመገናኘት እድላቸው ውስን ነበር። የትምህርት እና የስራ እድልም አልነበራቸውም።
በ 1991 በአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ህግ እና በ 1999 የዩኤስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ምክንያት ይህ ለብዙዎች ተለውጧል። አሁን ላይ የክልል እና የአካባቢ መንግስታት የአእምሮ እና የእድገት እክል ያለባቸውን ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲኖሩ ለመርዳት አገልግሎት መስጠት አለባቸው።
ዲስትሪክቱ አካል ጉዳተኞችን የሚያገለግሉ የህዝብ ተቋማቱን ዘጋ። አሁን ያሉት የመንግስት እና የግል ተቋማት ከ15 ያልበለጡ ጎልማሶች አሏቸው። በ St. Elizabeth’s Hospital የሚቀሩትን ግለሰቦች ቁጥር ዲስትሪክቱ ቀስ በቀስ ቀንሷል። Pathways to Housing DC የአእም ሮ ችግር ያለባቸውን ከተቀናጀ ቤት ጋር የሚያገናኘውን የ Housing First ሞዴልን ለመከተል የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ዲስትሪክቱ ደግፏል። ይህ በአጠቃላይ 666 አልጋዎች ያሉት 99 የማህበረሰብ መኖሪያ ተቋማትን ያጠቃልላል። ነገር ግን ቋሚ የድጋፍ መኖሪያ ቤት እና የቤት እጦት ችግር ያለባቸውን ለመርዳት የተቀመጡ ቫውቸሮች ፍላጎቶቹን አያሟሉም።
ሜሪላንድ ጭምር ብዙ እነዚህ አካል ጉዳተኞችን ከተቋማት አንቀሳቅሳለች። አሁን በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ይደግፏቸዋል። ነገር ግን ሁለት ተቋማት - በሳልስበሪ የሚገኘው Holly Center እና በሃገርስታውን የሚገኘው የ Potomac Center - ይቀራሉ። ምንም እንኳን ሜሪላንድ የስነ-ልቦና አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ግለሰቦች አሁንም የመንግስት ሆስፒታሎች ቢኖሯትም የቨርጂኒያን ያህል በእነሱ የምትመካ አይመስልም። በሁለቱም በሜሪላንድ እና በዲስትሪክቱ፣ ከቨርጂኒያ ይልቅ በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች በአረጋውያን መንከባከቢያ ቤቶች ይኖራሉ።
በ 2012 ፣ የቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ከዩኤስ የፍትህ ዲፓርትመንት ጋር በዩኤስ ቪ ቨርጂኒያ ውስጥ የ sweeping ስምምነት አድርጓል። ክሱ፣ የአዕምሮ እና የዕድገት እክል ያለባቸው ነዋሪዎች የማሰልጠኛ ማዕከላት በሚባሉ ትልልቅ ተቋማት ውስጥ ተለይተው
መቀመጣቸውን ተቃውሟል። ግዛቱ በፌርፋክስ የሚገኘውን የሰሜን ቨርጂኒያ ማሰልጠኛ ማእከልን በ 2016 ዘግቷል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁሉንም የስልጠና ማዕከላት ዘግተዋል፣ነገር ግን አሁንም የስምምነት አዋጁን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።8
ግዛቱ የእድገት እና የአዕምሮ እክል ላለባቸው ሰዎች የማህበረሰብ ውህደትን ማሳደጉን ቀጥሏል። ነገር ግን የቋሚ መኖሪያ ቤት እና የኪራይ እርዳታ እጥረት፣ አካል ጉዳተኞች ያሏቸው አማራጮች በቡድን ቤቶች እና በአረጋውያን መንከባከቢያ ቤቶች እንዲገደብ ያደርጋል። ቨርጂኒያ አሁንም በ Falls Church ውስጥ እንደሚገኘው የሰሜን ቨርጂኒያ የአእምሮ ጤና ተቋም ዓይነት ባሉ መጠነ- ሰፊ በመንግስት በሚተዳደሩ የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታሎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ትመካለች። የግዛቱ ከፍተኛ የእስራት መጠን እንዲሁ በግዛቱ እስር ቤቶች ውስጥ ለረጅም ጊዜ በብቸኝነት ታስረው የነበሩት አካል ጉዳተኞችን ለማዋሃድ እንቅፋት ነው።
አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ነዋሪዎች እንቅፋቶች
አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ነዋሪዎች የተለያዩ አይነት የመንግስት እና የግል መኖሪያ ቤቶች አሉ። ነገር ግን የተደራሽነት ደረጃዎችን ወይም ጥገናን አለማክበር የአካል ጉዳተኞችን እኩል ያልሆነ አያያዝ ያስከትላል። የክልሉ ህዝብ እድሜ ሲጨምር ይህ በጣም አስፈላጊ ይሆናል። ለአካል ጉዳት እና ተደራሽነት ጉዳዮች አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ምክንያቶች በሣጥን 4 ውስጥ ተዘርዝረዋል። ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦:
• በደንብ ያልተጠበቁ የእግረኛ መንገዶች የመንቀሳቀስ እክል ላለባቸው ሰዎች ተደራሽነታቸውን ሊገታ ይችላል። እነሱም መራመጃ ወይም ተሽከርካሪ ወንበሮች የሚያስፈልጋቸውን ያካትታል። በክልሉ ውስጥ ያሉ ብዙ የእግረኛ መንገዶች በአሜሪካውያን የአካል ጉዳተኞች ህግ የተቀመጡትን ደረጃዎች አያሟሉም።
• አሳንሰሮች አካል ጉዳተኞች የሜትሮ ባቡር ጣቢያዎችን የሚያገኙበት ዋና መንገድ ናቸው። የአሳንሰር ችግሮች ለእነዚህ ተጓጓዦች የትራንስፖርት አገልግሎትን ይገድባሉ። የሜትሮ ባቡር አሳንሰሮች እየተበላሹ እንደመሆናቸው ደንበኞችን ውስጥ ይዘው ሊያስቀሩ ይችላሉ።9 ብዙ መግቢያዎች ባሉባቸው ጣቢያዎች፣ ወደ አሳንሰሮች የሚወስዱትን መንገድ የሚያሳዩ ምልክቶች ብዙ ጊዜ ስለማይገኙ ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል።10
• የፕሪንስ ዊልያምስ ካውንቲ OmniRide፣11 የሉዶን ካውንቲ የአካባቢ አውቶቡስ አገልግሎት፣12 እና የፌርፋክስ ካውንቲ አያያዥ 13 እና የ CUE አውቶቡሶች የተሸከርካሪ ወንበሮች አሏቸው። ነገር ግን የአውቶቡስ ኦፕሬተሮች ዋና ዋና መገናኛዎችን፣ ምልክቶችን እና የመተላለፊያ ነጥቦችን ማስታወቅ ያለባቸው እንደሆን ድህረ-ገጾቻቸው አይናገሩም።14 የአሌክሳንደሪያ DASH አውቶቡስ ስርዓት የተሸከርካሪ ወንበር አለው ነገር ግን አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት ስርዓቱ ሌሎች እርምጃዎችን ስለመውሰዱ የስርአቱ ድህረ ገጽ አይገልጽም።15
• WMATA ለአካል ጉዳተኞች ክልላዊ ከቤት ወደ ቤት የመጓጓዣ አገልግሎት የሆነውን MetroAccess ን ያካሂዳል። አሌክሳንድሪያ፣ አርሊንግተን ካውንቲ፣ ሎዶውን ካውንቲ እና MDOT ተመሳሳይ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። ነገር ግን እነዚህ
8 Donald J. Fletcher, Report of The Independent Reviewer on Compliance with the Settlement Agreement United States v. Commonwealth of Virginia, December 2021 https://dbhds.virginia.gov/assets/doc/settlement/indreview/211213-final-19th-report-to-the-court.pdf
9 Wheelchair Travel, Washington, D.C. Public Transportation, https://wheelchairtravel.org/washington-dc/public- transportation/
10 Id.
11 OmniRide፣ ተደራሽነት፣ https://omniride.com/about/accessibility/
12 የሉዶን ካውንቲ የመጓጓዣ እና የተጓዥ አገልግሎቶች፣ የአካባቢ ቋሚ መስመር አውቶቡስ አገልግሎት፣ https://www.loudoun.gov/3302/Local- Bus
13 የፌርፋክስ ካውንቲ አገናኝ፣ የተጓዥ መመሪያ፣ https://www.fairfaxcounty.gov/connector/new-rider
14 የፌርፋክስ ካውንቲ CUE አውቶቡስ ስርዓት፣ ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች መጓጓዣ፣ https://www.fairfaxva.gov/government/public- works/transportation-division/cue-bus-system/transportation-for-seniors-and-persons-with-disabilities
15 የአሌክሳንድሪያ የመጓጓዣ ኩባንያ DASH፣ ተደራሽነት፣https://www.dashbus.com/node/52
አገልግሎቶች በተመሳሳይ ቀን ቦታ ማስያዝን አይፈቅዱም። እንዲሁም ዋጋዎች ውድ ሊሆኑ ይችላሉ።16 WMATA ለ MetroAccess ብቁ ለሆኑ ሰዎች የተመሳሳይ ቀን መጓጓዣ የሚሰጠውና ይበልጥ ውድ የሆነውን አገልግሎት፣ Abilities Rideን ያቀርብ ነበር። ሆኖም በኮቪድ-19 የተነሳ ፕሮግራሙ ታግዷል። የሮክቪል ከተማ ከ60 ዓመት በላይ ለሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ተመሳሳይ መርሃ-ግብር አለው።17
የቤት ባለቤትነት እንቅፋቶች
አካል ጉዳተኞች ቢያንስ ሁለት ዋና ዋና መሰናክሎች ያጋጥሟቸዋል፦
1. አካል ጉዳተኞች ካልሆኑት ጋር ሲነፃፀር ያነሰ ገቢ ይኖራቸዋል። ይህ በተለይም የአከባቢው ከፍተኛ ዋጋዎች ከግምት ውስጥ ሲገቡ መግዛት የሚችሏቸው ቤተች ላይ ገደብ ይፈጥራል።
2. ብዙውን ጊዜ ገዢዎች የነጠላ-ቤተሰብ ቤቶችን ይመርጣሉ። ነገር ግን በፍትሃዊ የቤቶች ህግ ንድፍ እና የግንባታ ደረጃዎች የተሸፈኑ አይደሉም። ይህም የመንቀሳቀስ እክል ላለባቸው ሰዎች ተደራሽ የመሆን እድላቸውን ይቀንሳል።
ሳጥን 4
ለአካል ጉዳት እና ተደራሽነት ችግሮች አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ምክንያቶች ማጠቃለያ
ስለ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት አፈጻጸም፣ የማዳረስ አቅም እና ግብዓቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የእቅዱን አባሪ ይመልከቱ።
◼ ለአካል ጉዳተኞች የሚከተሉት ተደራሽነት
‒ ብቃት ያላቸው ትምህርት ቤቶች
‒ በህዝብ የሚደገፍ መኖሪያ ቤት
‒ መጓጓዣ
◼ ተደራሽ ያልሆኑ
‒ የመንግስት ተቋማት ወይም አገልግሎቶች
‒ የህዝብ ወይም የግል መሠረተ ልማት
◼ ዕጥረት
- በከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ወጪዎች የተነሳ የዕድል ተደራሽነት
- በተመጣጣኝ ዋጋ በቤት ውስጥ ወይም በማህበረሰብ ላይ የተመሰረቱ የድጋፍ አገልግሎቶች
- ተደራሽ መኖሪያ ቤቶች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተለያዩ መጠኖች
- የድጋፍ አገልግሎት ለሚፈልጉ ግለሰቦች ተመጣጣኝ፣ የተቀናጀ የመኖሪያ ቤት
- የመኖሪያ ቤት ማሻሻያዎችን በተመለከተ እገዛ
- ከተቋማዊ አከባቢዎች ወደ የተቀናጀ መኖሪያ ቤት ለመሸጋገር እገዛ
- አካባቢያዊ ወይም ክልላዊ ትብብር
◼ የመሬት አጠቃቀም እና የዞን ክፍፍል ህጎች
16 WMTA፣ የMetroAccess የደንበኛ መመሪያ፣ https://wmata.com/service/accessibility/metro-access/ upload/MetroAccess- Customer-Guide-2021.pdf
17 https://www.infomontgomery.org/search-results/?id=59463344
◼ የብድር አድልዎ
◼ ተደራሽ መኖሪያ ቦታ
◼ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ማጣት
◼ የመኖሪያ ደንቦች እና ገደቦች
◼ ለአካል ጉዳተኞች የመኖሪያ ቤት እና የድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት የቁጥጥር እንቅፋቶች
◼ የገቢ ምንጭ አድልዎ
◼ አካል ጉዳተኞች በአፓርታማዎች፣ በቤተሰብ ቤቶች፣ የድጋፍ ቤቶች እና ሌሎች የተቀናጁ ቦታዎች እንዳይኖሩ ተስፋ የሚያስቆርጡ የክልል ወይም የአካባቢ ህጎች፣ መመሪያዎች ወይም ልምዶች
ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤቶች አፈጻጸም፣ የማዳረስ አቅም እና ግብዓቶች
የኮሎምቢያ ዲትሪክት፣ የሜሪላንድ ግዛት እና የቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ሁሉም የራሳቸው ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ህጎች አሏቸው። በፌዴራል ሕግ ከተሰጡት ላይ ጥበቃዎችን ይጨምራሉ። ይህ ሰንጠረዥ እነዚያን የተጨመሩትን ጥበቃዎች ያመለክታል።
በክልል ውስጥ በአካባቢ የመኖሪያ ቤት አድልዎ ህጎች ጥበቃ የሚደረግላቸው ቡድኖች
ዲሲ | ሜሪላንድ | ቨርጂንያ | |
ዕድሜ (18 ወይም ከዚያ በላይ) | • | ||
አካል ጉዳተኝነት | • | • | • |
አረጋዊነት | • | ||
የቤተሰብ ሁኔታ | • | • | • |
የቤተሰብ ኃላፊነቶች | • | ||
ጾታዊ ማንነት / መገለጫ | • | • | • |
የጋብቻ ሁኔታ | • | • | |
ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ መግባት | • | ||
ወታደራዊ ሁኔታ | • | ||
ብሄራዊ መነሻ | • | • | • |
ውጫዊ ገጽታ | • | ||
የመኖሪያ ወይም የንግድ ቦታ | • | ||
የፖለቲካ አቋም | • | ||
ዘር ወይም ቀለም | • | • | • |
ኃይማኖት | • | • | • |
ጾታ | • | • | • |
ጾታዊ ዝንባሌ | • | • | • |
የገንዘብ / የገቢ ምንጭ | • | • | • |
የቤት ውስጥ ብጥብጥ ሰለባ የመሆን ሁኔታ | • |
የሜሪላንድ የሰብአዊ ግንኙነት ህግ የህዝብ መኖሪያ ቤት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ አድልዎን ይከለክላል። የሚከተሉትን መሰረት በማድረግ መኖሪያ ሊከለከሉ አይችሉም፡
• ዘር
• ቀለም
• ኃይማኖት
• ጾታ
• የቤተሰብ ሁኔታ
• ብሄራዊ መነሻ
• የጋብቻ ሁኔታ
• ጾታዊ ዝንባሌ
• ጾታዊ ማንነት
• አካል ጉዳተኝነት
• የገቢ ምንጭ።
የቨርጂንያ የሰብአዊ መብቶች ህግ እንዲሁ የህዝብ መኖሪያ ቤት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ አድልዎን ይከለክላል። ከቤተሰብ ሁኔታ ውጪ ዝርዝራቸው ከሜሪላንድ ጋር ተመሳሳይ ነው፡ ቨርጂኒያ የሚከተሉትንም ያጠቃልላል፡
• ጾታዊ ዝንባሌ
• እርግዝና፣ ወሊድ፣ ወይም ተዛማጅ የሕክምና ሁኔታዎች
• ወታደራዊ ሁኔታ
በ2016፣ ዲስትሪክቱ ለቤቶች ፍትሃዊ የወንጀል ማጣሪያ ህግን አሳልፏል። የመኖሪያ ቤት አመልካቾችን የወንጀል ታሪክን ለሚያጣሩ የኪራይ ቤቶች አቅራቢዎች መስፈርቶችን ያካትታል።
በክልላችን ውስጥ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት መረጃን፣ ተደራሽነትን እና አፈጻጸሞችን የሚያቀርቡ ኤጀንሲዎችን ሳጥን 5 ላይ ይመልከቱ።
ሳጥን 5
ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት መረጃ፣ ተደራሽነት እና አፈጻጻም የሚያቀርቡ ኤጀንሲዎች
◼ DC Office of Human Rights (የዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ)
◼ Equal Rights Center (የእኩልነት መብቶች ማዕከል)
◼ Housing Opportunities Made Equal of Virginia (የቨርጂንያ Housing Opportunities Made Equal)
◼ Maryland Commission on Civil Rights (የሜሪላንድ የሲቪል መብቶች ኮሚሽን)
◼ Montgomery County Office of Human Rights (የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ)
◼ Virginia Department of Professional and Occupational Regulation’s Fair Housing Board (የቨርጂኒያ የባለሙያ እና የሙያ ደንብ ፍትሃዊ የቤቶች ቦርድ መምሪያ)
◼ Washington Lawyers’ Committee for Civil Rights and Urban Affairs (የዋሽንግተን ጠበቆች ለሲቪል መብቶች እና የከተማ ጉዳዮች ኮሚቴ)
ፍትሐዊ የመኖሪያ ቤት ግቦች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች
በዚህ እቅድ ውስጥ የሚሳተፉት ስምንቱ የአካባቢ መንግስታት የጋራ ክልላዊ ግቦች እና ስልቶችን መርጠዋል። እንደ ክልል እንዴት ወደፊት እንደምንራመድ በእነዚህ ገፆች ላይ በተሰበሰበውና በተጠቃለለው መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ መረጃ ከሚከተሉት የሚገኝ ሰፊ መረጃን፣ የነዋሪዎችን ግብአት እና መመሪያን ያካትታል፦
• የአካባቢ እና የፌዴራል መንግስታት
• የህዝብ መድረኮች
• የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ
• የግለሰብ ቃለመጠይቆች
• የዳሰሳ ጥናቶች
• የማህበረሰብ አማካሪ ኮሚቴ
በእነዚህ ስልቶች ላይ በጋራ በመስራት የሚከተሉትን ግቦቻችንን ማሳካት እንችላለን፦
• የመኖሪያ ቤት አድልዎን መቀነስ
• የዘር ክፍፍል የድግግሞሽ ታሪክን ወደኋላ መቀልበስ
• ለሁሉም የአሁን እና የወደፊት የዋሽንግተን ክልል ነዋሪዎች የእድሎችን ተደራሽነት ማሻሻል
ግቦች እና ስልቶች
1. የአካባቢውን መካከለኛ ገቢ (AMI) 60% ወይም ከዚያ በታች ለሚያገኙ ቤተሰቦች - በተለይም ምንም ባልነበረበት ቦታ ላይ ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን መጨመር።
ይህንን ግብ ለማሳካት ብዙ መንገዶች አሉ:
• ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን የሚጨምሩ መመሪያዎችን እና መርሃ- ግብሮችን ማጥናት። የመኖሪያ ቤት ቦንዶች፣ የሪል እስቴት ዝውውር ግብሮች እና በሚፈቀድበት ጊዜ የግዴታ ተካታች ቤቶችን ያካትታሉ።
• ከ AMI 80% ይልቅ 60% ወይም በታች ገቢ ለሚያገኙ ሰዎች አዲስ የኪራይ ቤት መፍጠር። ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ቤተሰቦች ሥር የሰደደ የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት የ AMI 50% ወይም ከዚያ በታች ለሚያገኙ የመኖሪያ ክፍሎች መገንባት።
• በተመጣጣኝ ዋጋ ADUs (ተጨማሪ መኖሪያ ክፍሎችን) በንብረታቸው ላይ መገንባት ለሚፈልጉ የቤት ባለቤቶች በዝቅተኛ ወለድ ብድር መስጠት። (ለምሳሌ: በአንድ ጋራዥ ላይ ያለ አፓርታማ)።
2. ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ተደራሽነትን ለማስፋት የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን መቀየር። አቅምን ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት ልማትን፣ ጂኦግራፊያዊ ስርጭትን እና አቅርቦትን ማሳደግ።
በክልል ውስጥ ለነጠላ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች የሚደረግ የዞን ክፍፍል በተመጣጣኝ ዋጋ የመኖሪያ ቤቶች ማዘጋጀትን አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይህንን ለመቀየር የአካባቢው መሪዎች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
• እንደ ተጨማሪ የመኖሪያ ክፍሎች ዓይነቶችን ለመፍቀድ የዞን ክፍፍል ደንቦችን መከለስ
• ተጨማሪ አቅምን ያገናዘቡ የመኖሪያ ቤቶች በአዲስ የቅይጥ ገቢ ህንጻ ውስጥ እንዲፈጠሩ ለማስቻል የአካታች የዞን ክፍፍል ማበረታቻዎችን ማሳደግ ወይም ገንቢዎች ወደፊት የሆነ ጊዜ፣ሌላ ቦታ ላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን ለሚገነባ ሰው የሚከፍሉትን ክፍያ መጨመር
• አቅምን ያገናዘቡ ቤቶች ልማትን ቀላል ለማድረግ የዞን ክፍፍል ለውጦችን ተቀብሎ መተግበር
• ጉልህ የሆኑ የመልሶ ማቋቋም ሀሳቦች እና የተወሰኑ እቅዶች ግምገማ ወቅት ትክክለኛ የመኖሪያ ቤቶች ፍትሐዊነት ትንተናን ማካተት
3. ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመጠበቅ እና የነዋሪዎችን መፈናቀል ለመከላከል መመሪያዎችን መተግበር። በክልላችን ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸውን ነባር የኪራይ ቤቶችን ማቀየት።
ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶችን አጥተናል። ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ነገሮች አንዱ የተጣራ ዜሮ ለውጥ መሆን አለበት። በሌላ አነጋገር፣ አዲስ በመገንባት ወይም ያሉትን በመጠበቅ ኪሳራውን ማካካስ አለብን። ይህንን ለማድረግ የሚከተሉትን ማድረግ አለብን:
• አሁን ላይ ያሉትን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን መኖሪያ ቤት መከታተል እና መደገፍ
• ተከራዮች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ቡድኖች እና የአካባቢ መስተዳድሮች የሚሸጡ አፓርታማዎችን እና ቤት መስሪያ መሬቶችን እንዲገዙ የብድር ገንዘብ ማቋቋም
4. በክልሉ ውስጥ ያሉ የቤት ባለቤቶችን ቁጥር መጨመር እንዲሁም ከአድልዎ በህግ የሚጠበቁ አባላት ቤት እንዳይገዙ የሚያደርገውን እኩል ያልሆነ አያያዝ እና አድሎአዊ ድርጊቶችን መቀነስ።
ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ገዢዎች ቤቶችን ለመግዛት እድሎችን ማሳደግ እንችላለን፡
• በትብብር የቤት ባለቤትነት ሞዴሎች እና የማህበረሰብ መሬት ባለአደራዎች
• ከፍ ያለ ጥግግት፣ አነስ ያሉ/ተጨማሪ መኖሪያ ክፍሎችን እና ባለ ሁለትዮሽ ቤቶችን በመፍቀድ እና በማበረታታት
• በአዳዲስ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ውስጥ አንዳንድ የድጎማ ቤቶችን ለይቶ በማስቀመጥ
እንዲሁም አናሳ ዘር እና ጎሳ ውስጥ የሚካተቱ የቤት ባለቤቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ እና አረጋውያንን በሚከተሉት መርዳት እንችላለን፡
• ለቤት ጥገና፣ መልሶ ማቋቋሚያ እና እድሳት የሚከፍሉ መርሃ-ግብሮች እና ምርቶች
• የመገልገያ ወጪዎችን ለመቀነስ ኃይል ቆጣቢ ማሻሻያዎችን የሚያቀርቡ መርሃ-ግብሮች
• የቤት እገዳን ለማስወገድ እንዲረዳቸው ማማከር እና ህጋዊ ሪፈራሎች
ፍትሃዊ ያልሆነ የቤት ገዢ ልማዶች በነጭ ቤተሰቦች እና ቀለም ባላቸው ቤተሰቦች መካከል ያለውን የሀብት ልዩነት የከፋ ያደርገዋል። የሚከተሉትን ለማድረግ እርምጃዎችን መውሰድ አለብን፡
• የግምገማ አድሎአዊነትን መቀነስ - በባለቤቱ ማንነት ላይ ተመስርቶ ለንብረት ዋጋ መስጠት
• አድልዎ ለመለየት ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ግምገማን መጨመር
• አመልካቾች በእኩልነት መያዛቸውን ለማረጋገጥ አበዳሪዎችን እና የሪል እስቴት አካላትን መቆጣጠር
5. ጥበቃ የሚደረግላቸው ቡድኖች አካል የሆኑ ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት መብቶችን መጠበቅ። ለምሳሌ፣ ቀለም ያላቸው ሰዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና አዛውንቶች።
ማፈናቀል እና የቤት ኪራይ መጨመር እነዚህ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ያስገድዳቸዋል። ይህ በአብዛኛው የሚከሰተው በጥቁር እና በሂስፓኒክ ነዋሪዎች እና በአካል ጉዳተኞች ላይ ነው። ወረርሽኙ ለተከራዮች እና ለተወሰኑ የዘር እና የጎሳ ቡድኖች ሁኔታውን አባብሷል። እነዚህን ነዋሪዎች መኖሪያቸውን ይዘው እንዲቆዩ ለመርዳት፣ የሚከተሉትን ማድረግ እንችላለን፡
• ለቤቶች ቫውቸሮች የአከባቢ የገንዘብ ድጋፍን ማስፋፋት። በክልሉ ውስጥ ሕጋዊ ማድረግ።
• የቤቶች ተንቀሳቃሽነት መርሃ ግብሮችን መጠን እና ስፋት መጨመር
• አከራዮች ለቫውቸር ያዢዎች የማመልከቻ ክፍያዎችን እንዲቀንሱ፣ እንዲያስወግዱ ወይም እንዲያካክሱ በማበረታታት የኪራይ ቤቶችን እንቅፋቶች መቀነስ።
• በተከራይ የወንጀል ታሪክ ማጣሪያ ወቅት የHUD መመሪያዎችን መከተል
• የማማከር መብት መርሃ-ግብርን ማስጀመር። ተከራዮች ከአከራያቸው ጋር ለሚነሱ አለመግባባቶች የህግ ውክልና ያገኛሉ።
• ለፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ተደራሽነት፣ ትምህርት፣ ስልጠና፣ ግምገማ እና ማስፈጸሚያ ድጋፍን መጨመር
6. የማህበረሰብ ውህደትን በመጨመር የአካል ጉዳተኞች የመኖሪያ ቤት እንቅፋቶችን መቀነስ።
አሁን ያለው የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ የአካል ጉዳተኞች በማኅበረሰባችን ውስጥ ራሳቸውን ችለው መኖር እንዲችሉ የሚያስፈልጋቸውን መኖሪያ ቤት ለመፍጠር በቂ አይደለም። ክልሉ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል:
• የቋሚ መኖሪያ ቤቶችን አቅርቦት ለመጨመር ሌሎች የገንዘብ ምንጮችን መጠቀም። ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት ቦንዶች፣ ተመጣጣኝ የቤቶች የባለአደራ የገንዘብ ድጋፍ፣ የንግድ ትስስር ክፍያዎች እና የሪል እስቴት ዝውውር ታክሶችን ያካትታሉ።
• ከመንግስት የገንዘብ ድጋፍ በሚቀበሉ አዳዲስ ባለብዙ ቤተሰብ ግንባታዎች ውስጥ ተደራሽ ክፍሎችን የሚጠይቁ የንድፍ መስፈርቶችን መቅረጽ ። ከሁሉም ክፍሎች 10% የሚሆኑት የመንቀሳቀስ እክል ላለባቸው እና ቢያንስ 4% የሚሆኑት ደግሞ የመስማት እና/ወይም የማየት እክል ላለባቸው ሰዎች ተደራሽ መሆን አለባቸው።
• ለአካል ጉዳተኞች የኪራይ ድጋፍ መርሃ-ግብሮች ተጨማሪ ድጋፍ እና ግብዓቶችን ማቅረብ
• አካል ጉዳተኞችን በሚረዱ የጉዳይ አስተዳዳሪዎች ተለይተው የቀረቡ መሰናክሎችን ለመመርመር ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ግምገማ ማካሄድ
• የፍትሃዊ ቤቶች ህግ የተገቢ መስተንግዶ ግዴታን በወንጀለኛ መቅጫ ታሪክ ማጣራት ላይ ስለመተግበር ትምህርት መስጠት
• በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ የሆኑ ክፍሎችን መከታተል እና ካርታ መስራትን ማሻሻል። በዙሪያው ያሉ መንገዶች እና የእግረኛ መንገዶች ምን ያህል ተደራሽ እንደሆኑ ማካተት።
7. ጥበቃ ለሚደረግላቸው ክፍሎች አባላት የህዝብ ማመላለሻ በቀላሉ እንዲገኝ እና አቅምን ያገናዘበ እንዲሆን ማድረግ።
በክልሉ ያለው ከፍተኛ የቤት ወጪ ብዙ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ከሥራቸው እና ከሚተማመኑበት የህዝብ ማመላለሻ ርቀው እንዲሄዱ አስገድዷቸዋል። ይህ ጥበቃ የሚደረግላቸው ክፍሎች አባላትን ያካትታል። ይህንን ለመፍታት ክልሉ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፡
• ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የነጻ ወይም የቅናሽ ዋጋ አውቶቡስ እና ሌሎች መጓጓዣዎችን ለማስፋፋት ግብዓቶችን መለየት
• እነዚህ ነዋሪዎች በሌሎች አካባቢዎች ሥራ ያገኙ ዘንድ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማጥናት በክልሉ ውስጥ ባሉ ድንበሮች ላይ ያሉ የአውቶቡስ መስመሮችን ለማሻሻል፣ ለማስፋት እና ለማስተባበር ምክረ-ሃሳቦችን መስጠት
ከእነዚህ ክልላዊ ግቦች በተጨማሪ፣ በሣጥን 6 ውስጥ ያለውን የአካባቢ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ግቦች ዝርዝር ይመልከቱ። ለበለጠ መረጃ በክልላዊ ፍትሃዊ የቤቶች እቅድ ውስጥ የእያንዳንዱን ስልጣን ክፍል ይመልከቱ።
ሳጥን 6
ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ግቦች እና ስልቶች
ከክልላዊ ዓላማዎች በተጨማሪ፣ እያንዳንዱ የአካባቢ አስተዳደር በማህበረሰቡ ውስጥ ይበልጥ ፍትሃዊ የሆነ የመኖሪያ ቤቶችን ለማረጋገጥ የራሱ ግቦች እና ስልቶች አሉት። በእነዚህ ግቦች ላይ ተጨማሪ ዝርዝሮች (ከዚህ በታች የተዘረዘሩት) እንዲሁም እነሱን ለማሳካት የሚውሉ ስልቶች በእያንዳንዱ የክልል ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት እቅድ ውስጥ ይገኛሉ።
የአሌክሳንድሪያ ከተማ
▪ ለተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ለሕዝብ መሬት ቅድሚያ መስጠት።
▪ ተጨማሪ የመኖሪያ ክፍሎቻቸውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ተከራዮች ለሚያከራዩ የቤት ባለቤቶች ከፊል የግብር ቅነሳዎችን ማቅረብ።
▪ በቨርጂኒያ ኮድ § 15.2-2304 መሠረት። በተወሰኑ አከባቢዎች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የመኖሪያ ክፍል ድንጋጌዎች፣ ከተማ አቀፍ የሆነ የግዴታ ማካተት የዞን ክፍፍልን ለማቋቋም እና እንደ ጥግግት ጉርሻ፣ ልዩ አከፋፈል፣ የተፋጠነ ማፅደቅ፣ የክፍያ መተው እና የግብር ማበረታቻዎችን የመሳሰሉ ማበረታቻዎችን ለማቅረብ ደንብ ወስደው ይተገብራሉ።
▪ በ R-20 ዞን ውስጥ ያለውን ዝቅተኛውን 20,000 ካሬ ጫማ መጠን መቀነስ ወይም በዚህ ዞን ውስጥ ባለ ሁለትዮሽ ቤቶችን መፍቀድ።
አርሊንግተን ካውንቲ
▪ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች አቅምን ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን መጨመር
▪ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫ ተደራሽነትን ለማስፋት ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ ጂኦግራፊያዊ ስርጭት እና አቅርቦት በማሳደግ የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን ማሻሻል
▪ መፈናቀልን ለመከላከል የተነደፉ መመሪያዎችን መተግበር
▪ የግለሰቦች የመኖሪያ ቤት መብቶችን መጠበቅ እና ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ትምህርትንማጠናከር
▪ የአካል ጉዳተኞች የማህበረሰብ ውህደትን መጨመር
▪ ለበለጠ ፍትሃዊ መኖሪያ ቤት የነባር መርሃ-ግብሮችን ውጤታማነት መጨመር
የኮሎምቢያዲስትሪክት
▪ ቤቶችን ለመገንባት የቅድመ ክፍያ እርዳታ እና የገንዘብ ድጋፍ ማቅረብ
▪ መጠለያዎችን አቅምንወዳገናዘቡ ቋሚ መኖሪያ ቤቶች መለወጥ
▪ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫ ተደራሽነትን ለማስፋት የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን ማሻሻል። አቅምን ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት ልማት፣ ጂኦግራፊያዊ ስርጭት እና አቅርቦትን ማሳደግ።
▪ ጥበቃ ለሚደረግላቸው ቡድኖች የግለሰቦችን የመኖሪያ ቤት መብቶችን መጠበቅ
ፌርፋክስ ካውንቲ
▪ የገቢ መስፈርቶችን በመቀነስ እና ከ Tysons ውጪ ለሚገኙ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተለየ መመሪያ በመፍጠር የካውንቲውን ለሽያጭ የሚውል የሰው ኃይል መኖሪያ ቤት መመሪያን ማሻሻል
▪ ጥበቃ ለሚደረግላቸው ቡድኖች የግለሰቦችን የመኖሪያ ቤት መብቶችን መጠበቅ
ጌይተርስበርግ
▪ ተመጣጣኝ እና የቤተሰብ መጠን ያላቸውን ክፍሎች ለመገንባት እና ለማቆየት የቤቶች የተነሳሸነት የገንዘብ ድጋፍ መጠቀም
▪ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫዎችን ለማስፋት የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን ማሻሻል
▪ አቅምን ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት ልማት፣ ጂኦግራፊያዊ ስርጭት እና አቅርቦትን ማሳደግ ሉዶን ካውንቲ
▪ ወቅታዊ መርሃ-ግብሮች እና ተነሳሽነቶችን ማስፋፋት።
▪ ከ Unmet Housing Needs Strategic Plan ስልታዊ እቅድ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ
▪ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫ ተደራሽነትን ለማስፋት የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን ማሻሻል። አቅምን ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት ልማት፣ ጂኦግራፊያዊ ስርጭት እና አቅርቦትን ማሳደግ።
▪ ለፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ተደራሽነት፣ ትምህርት እና አፈጻጸም ድጋፍን ማስፋት እና ማሳደግ
ሞንትጎመሪ ካውንቲ
▪ በ Housing Initiative Fund፣ HOME እና CDBG ብድሮች ለተወሰኑ የገቢ ደረጃዎች የተሰጡ ቤቶችን ጠብቆ ማቆየት እና ማምረት።
▪ በካውንቲ ባለቤትነት የተያዘ መሬት ላይ እነዚህን ቤቶች ለመፍጠር ቅድሚያ መስጠት። ይህም ሁሉም ብቁ ግንባታዎች መጠነኛ ዋጋ ያላቸው የመኖሪያ ክፍሎች (MPDUs) መጠነኛ የቤተሰብ ገቢ ላላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎች መያዛቸውን ያረጋግጣል።
▪ የማህበረሰብ መልሶ ኢንቨስትመንት ህግ ብድሮችን መጠቀም። እነዚህ ባንኮች በማህበረሰባቸው ውስጥ የሚያደርጓቸው ኢንቨስትመንቶች ናቸው- ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰፈሮች ጨምሮ።
▪ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫዎችን ለማስፋት የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን ማሻሻል። በካውንቲው ውስጥ ተጨማሪ እነዚህን ቤቶች ይገንቡ።
▪ ጥበቃ ለሚደረግላቸው ቡድኖች የግለሰቦችን የመኖሪያ ቤት መብቶችን መጠበቅ
▪ የህዝብ ማመላለሻ ተደራሽነትን ማስፋፋት እና አቅማቸውን ያገናዘበ እንዲሆን ማድረግ። ፕሪንስ ዊሊያም ካውንቲ
▪ የቤቶች የባለ አደራ የገንዘብ ድጋፍ መፍጠር። በጣም ዝቅተኛ እና እጅግ በጣም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ተመጣጣኝ
መኖሪያ ቤት ለማምረት እና ለማቆየት እርዳታ ይሰጣል።
▪ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ምርጫዎችን ለማስፋት የዞን ክፍፍል እና የመሬት አጠቃቀም መመሪያዎችን ማሻሻል።
አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ሁኔታዎች
“አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ሁኔታዎች” የአንድ ወይም ከዚያ በላይ ፍትሃዊ የቤት ችግሮችን ይፈጥራሉ፣ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ፣ እንዲቀጥል ያደርጋሉ ወይም ይጨምራሉ። በክልል ፍትሃዊ የቤቶች እቅድ ውስጥ ያሉ ግቦች አንድ ወይም ከዚያ በላይ አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ሁኔታዎች እና ተዛማጅ ፍትሃዊ የቤት ችግሮችን ለመግታት የታለሙ ናቸው።
በዚህ ማጠቃለያ ውስጥ በክልሉ ውስጥ ያሉ ፍትሃዊ የቤት ችግሮች ተብራርተዋል። ለበለጠ መረጃ፣ የክልላዊ ፍትሃዊ የቤቶች እቅድ ምዕራፍ VIIን ይመልከቱ።
ማጠቃለያ
ይህ ክልላዊ ፍትሃዊ መኖሪያ ቤት ዕቅድ ለዋሽንግተን ክልል ትልቅ ምዕራፍ ነው። ከ1997 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት የአካባቢ መስተዳድሮች በጋራ በመሆን ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤቶች መሰናክሎችን በክልል ደረጃ ለመገምገም ተባበሩ።
በክልላችን ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ከተማ እና ካውንቲ የራሱ ልዩ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ያጋጥመዋል። ስለዚህ የፕሮጀክት ቡድኑ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ወጥነት ያለው መሆን ነበረበት፦
• የማህበረሰብ አባላትን እንዴት እንዳሳተፈ
• የተተነተነ መረጃ
• የእቅዱን ግቦች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ማቅረብ
ይህ ክልላዊ አካሄድ የጋራ ጭብጦችን እንድንለይ አስችሎናል። ለምሳሌ፣ ክልሉ ለሚከተሉት እንዴት ትልቅ ፍላጎት እንዳለው፡
• ከአካባቢው መካከለኛ ገቢ 60% እና ከዚያ በታች ለሆኑ ለቤተሰቦች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው መኖሪያ ቤት - በተለይ ጥበቃ ለሚደረግላቸው ክፍሎች አባላት
• ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መኖሪያ
• ሁሉም ነዋሪዎች የሚያገኙት እና አቅማቸውን ያገናዘበ መጓጓዣ
ለችግሮቻችን የአካባቢ መፍትሄዎች እንፈልጋለን። ነገር ግን ክልሉ በጋራ ራዕይ እና አካሄዶች ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በከተማ እና በካውንቲ ድንበሮች የተገደቡ አይደሉም። የዋሽንግተን ክልል በብዙ ቦታዎች ተወስደው ሊተገበሩ የሚችሉ ብዙ የውጤታማ መመሪያዎች እና መርሃ-ግብሮች ምሳሌዎች አሉት። አካታች የዞን ክፍፍል እና የቤቶች ምርት ትረስት የገንዘብ ድጋፍ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ናቸው።
ይህንን ክልላዊ ፍትሃዊ የቤቶች እቅድ ማዘጋጀት የጋራ ጥረት የነበረ ሲሆን አብረን መስራታችንን እንድንቀጥል ይረዳናል። በክልሉ ውስጥ ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤት ግቦችን በቋሚነት በመተግበር፣ ክልሉን ቤት ብለው ለሚጠሩ በሙሉ ሁሉን አቀፍ የሆነ ማህበረሰብ መፍጠር እንችላለን።