ሐምሌ 29 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ
የሰበር መ/ቁ 25287
ሐምሌ 29 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ
Aቶ ሐጐስ ወልዱ ወ/ት ሂሩት መለሰ Aቶ መድህን ኪሮስ Aቶ በላቸው Aንሺሶ
Aመልካች፡- ሜድሮክ Iትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር Aልቀረበም ተጠሪ፡- Aቶ በዛወርቅ ሺመላሽ ቀረቡ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ፍ ር ድ
ጉዳዩ የተጀመረው በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የክርክሩን Aመጣጥ በተመለከተ የAሁን ተጠሪ የሥር ከሣሽ መጋቢት 18 ቀን 1993 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ ከግንቦት 24 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ Eስከ ጥቅምት 20 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ በሕግ Aገልግሎት ሃላፊነት ተቀጥሬ ያገለገልኩ ሲሆን በፌደራል ፍ/ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ Aሰጣጥን ምዝገባ Aዋጅ ቁጥር 199/92 መሠረት ለተከሳሹ Aገልግሎት ለመስጠት በመቸገሬ ምክንያት ተከሣሹ ሁኔታውን Eንዲያሻሽል ብጠይቅ ተከሣሹ የሥራ ውሌን Aቋርጧል፡፡ የተከሳሹ ሥራ Aስኪያጅ በብር 5,000 /Aምስት ሺህ ብር/ ደመወዝና የመኪና Aበል (በተጨማሪነት) የቀጠሩኝ ቢሆንም ይህ ክፍያ ሣይከፈለኝ የቆየ በመሆኑ የ43 ወራት የAገልግሎት ቀሪ ክፍያ ብር 76,411፣ የመኪና ማካካሻ ክፍያ ብር 43,000፣ የትራንስፖርት Aበል ብር 21,500፣ E.ኤ.A. ህዳር 23 ቀን 1999 በተፃፈ ደብዳቤ የታመነ ብር 1,349.74፣ ዳላስ ሄጄ የተመለስኩበት የውሎ Aበል ብር 5,049፣ የAውሮፕላን ትኬት ክፍያ ብር 2,607፣ የ3 ወር ያልተከፈለ Aበል ብር 19,500፣ የ3 ዓመት ወለድ ብር 30,495፣ በድምሩ ብር 199,911.74
(Aንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ Aስራ Aንድ ብር ከሰባ Aራት ሳንቲም) Eንዲከፈለኝ ወደ ሥራም Eንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ክስ Aቅርበዋል፡፡
ተከሳሽም ጥቅምት 14 ቀን 1994 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ የከሣሽ የክፍያ ጥያቄዎች በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 162 መሠረት በይርጋ የታገዱ ናቸው፤ ሊከፈላቸው የሚገባ ደመወዝ ላይ የተደረገ
ስምምነት የለም፣ ደመወዛቸው ሲከፈላቸው Eንደቆየው ነው፣ ፈርመው ሲቀበሉት በነበረው ገንዘብ ላይ ክርክር መፍጠራቸው Aግባብ Aይደለም፤ ዳላስ ሄደው የተመለሱበት የውሎ Aበል ተከፍሏቸዋል፤ ብር 1,349.74 ሊከፈላቸው Aይገባም፤ የAውሮፕላን ትኬቱን በተመለከተ ብር 2,607 ለመክፈል ፈቃደኛ ሆነን Eያለ ከሣሽ ጥያቄ ባለማቅረባቸው Eድሉ Aልፏቸዋል፤ ከሣሽ የሶስት ወር ደመወዝና Aበል ያሉት የመቼ Eንደሆነ ያልተገለፀ ከመሆኑም ሌላ ከሣሽ Eስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ያለ የሚገባቸው ደመወዝና Aበል ተከፍሎAቸዋል፤ ከሣሽ የተሰናበቱት በAግባቡ ነው፤
የሚከፈላቸው ወለድም የለም በማለት ከተከራክሯል፡፡
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ከሣሽ ያቀረቡት የAውሮፕላን ትኬት፣ የውሎ Aበልና የብር 1,349.74 ክፍያ መከፈል ከነበረበት ጊዜ Aንስቶ ክስ Eስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ሲሰላ Aንድ Aመት ያለፈበት Eንደመሆኑ ክፍያው በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 162 መሠረት በይርጋ የታገደ ነው፤ የደመወዝ ጥያቄውም Eንደዚሁ ክስ ከቀረበበት ጊዜ Aንድ Aመት ወደኋላ በመቁጠር ሲታይ ጊዜ ያለፈበት በመሆኑ በAዋጅ Aንቀጽ 162(1) መሠረት በይርጋ ቀሪ መሆን የሚገባው ነው፤ በሌላ በኩል ተከሣሽ ከሣሽን ከሥራ ያሰናበተበት ምክንያት Aቶ ዳንኤል ተገኑ ከፃፉት ሪፖርት በመነሳት Eንጂ ሌላ ተከሣሽ Aልሰራም ያሉ ስለመሆናቸው የሚያሳይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ሥንብቱ ሕጋዊ Aይደለም፡፡ በመሆኑም የተከሣሽ ወደ ሥራ መመለስ ለሥራ ግንኙነቱ የማይመች ሊሆን ስለሚችል
ከሣሽ ለከሣሽ የሥራ ስንብት፣ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያና የስድስት ወር የካሣ ክፍያ በመክፈል ከሣሽን Eንዲያሰናብት፤ ከይርጋ የተረፈውን ክፍያ በተመለከተ የከሣሽ የደመወዝ ብር 5,000 ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ
ባለመኖሩና ከሣሽ የጠየቁት የሶስት ወር ክፍያም የመቼ Eንደሆነ ተብራርቶ
ስላልቀረበ የሶስት ወር ደመወዝ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም፤ ኃላፊዎቹ በመጻጻፍ ሒደት ላይ ስለነበሩ የከሣሽ ደመወዝ ብር 5,000 Eንዲሆንላቸው ተወስኖ ሊሆን Eንደሚቻል ተገንዝበናል፡፡ ልዩነቱን የይርጋ ጊዜ ከሚጀምርበት መጋቢት 21 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ Eስከተሰናበቱበት ጥቅምት 20 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ ያለውን የስምንት ወር ልዩነት ተከሳሽ ለከሳሽ Eንዲከፍል በማለት ወስኗል፡፡
የAሁን Aመልካች የፌ/መ/ደፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ Aቅርቧል፡፡ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በድርድር ላይ ያለ ደመወዝ Eንደተወሰነ ደመወዝ ተደርጐ ሊወሰድ Aይችልም፣ የሠራተኛው ደመወዝ ብር 4,524 ነው፡፡ ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት የሠራተኛው ደመወዝ ብር 5,000 ነው ያለው በAግባቡ Aይደለም፡፡ ሰራተኛው Eስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ ደመወዛቸውን ሲያገኙ የቆዩ በመሆናቸው የስምንት ወር የደመወዝ ልዩነት ይከፈላቸው ተብሎ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔም ተቀባይነት የለውም፡፡ የስንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያ ለሰራተኛው Eንዲከፈላቸው የተባለውም በAግባቡ Aይደለም፡፡ ስንብቱ ሕገወጥ በመሆኑ ድርጅቱ የስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ለሰራተኛው ሊከፍላቸው Eንደሚገባ ግልጽ ቢሆንም ድርጅቱ ይህን ክፍያ መፈፀሙን በስንብት ደብዳቤው ስለገለፀና ሠራተኛውም ይህ ክፍያ Aልተከፈለኝም ብለው ስላልተከራከሩ ድጋሚ ሊከፈላቸው Aይገባም በማለት ድርጅቱ በብር 4,524 የደመወዝ ሒሳብ Aስልቶ ካሣ ለሰራተኛው ይክፈል በማለት በፌ/መ/ደ/ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በመቀጠልም Aመልካች የፌ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለዚህ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት Aቤቱታውን Aቅርቧል፡፡ ቅሬታውም ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት የተቀጠሩበትን ሥራ Aልሰራም በማለታቸው ነው፡፡ ተጠሪው ሥራውን Aልሰራም ያሉትም ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ ወይም ደግሞ የኩባንያው ሸሪክ (ባለAክሲዮን) Aድርጐ ካላስመዘገበኝ ሥራ መስራት Aልችልም፡፡ ከሠራሁ በወንጀል የሚያስጠይቀኝ በመሆኑ ሁኔታው ሊመቻችልኝ ይገባል በማለት ነው፡፡ Eንዲህ የሚል ሐሳብ ስለማቅረባቸው ራሳቸው የፃፋት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡ Aቶ ዳንኤል ተገኑ የፃፉት ደብዳቤም ተጠሪው Aልሰራም ማለታቸውን ያረጋግጣል፡፡ Eንደዚሁም Aቶ ዳንኤል ተገኑ በመከላከያ ምስክርነት ቆጥረናቸዋል፡፡ የሥር ፍ/ቤቶች
ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የወሰኑትም የቀረቡትን ማስረጃዎችና የተደረገውን ክርክር ባለመገንዘብና በመከላከያ ምስክርነት የቆጠርናቸውን Aቶ ዳንኤል ተገኑን ምስክርነት ባለመሰማት ነው፡፡ በመሆኑም ተጠሪው የተቀጠሩበትን ሥራ Aልሰራም በማለታቸው በAዋጅ ቁ. 42/85 Aንቀጽ
26(1) Eና 28 መሠረት የተሰናበቱ ናቸው፡፡ ስንብቱ ሕጋዊ ሆኖ ሳለ የስር
ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የAዋጁን ድንጋጌ የሚፃረር በመሆኑ ውሳኔቸው መሠረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበትና ሊታረም የሚገባው ነው የሚል ነው፡፡
ተጠሪው ደግሞ በሰጡት መልስ የፌ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ
የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ በመሆኑ Aመልካች ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ ነበረበት፡፡ ይህን Aልፎ ለሰበር ችሎት Aቤቱታ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡ ድርጅቱ የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ ሥራ Aልሰራም Aላልኩም ባለAክሲዮን Aድርጐ ካላስመዘገበኝ የምክር Aገልግሎት Aልሰጥምም Aላልኩም፡፡ Aመልካች Aልተሰማልኝም ያሉት ምስክር የሚያውቀውን በጽሑፍ ስለገለፀ ለምን ቀርቦ Aልመሰከረም Aይባልም፡፡ ተፈጠረ ላልኩት ችግር መፍትሄ ሳይሰጥበት ድርጅቱ Eኔን ማሰናበቱ ተገቢ
Aይደለም፡፡ የፌ/ከ/ፍ/ቤት ድርጅቱ ለችግሩ መፍትሄ ሳይፈለግ የተወሰደው የሥራ ስንብት Eርምጃ ሕገወጥ ነው በማለት የወሰነው በAግባቡ ነው፡፡ በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የሌለበትና በAግባቡ የተሰጠ በመሆኑ ሊፀናልኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡
ግራ ቀኙ ያደረጉት የቃል ክርክርም በመቅረፀ ድምፅ ከተሞላው ካሴት ወደ ጽሑፍ ተመልሶ ጽሑፉ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡ Aመልካች ያቀረበው የመልስ መልስም Eንደዚሁ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡
በበኩላችን ደግሞ Aመልካች ኩባንያ ተጠሪውን ያሰናበታቸው
በሕገወጥ መንገድ ነው ወይስ Aይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል፡፡
መዝገቡን Eንደመረመርነውም ተጠሪው ሐምሌ 7 ቀን 1992 ዓ.ም ለAቶ ንጉሴ Aበራ በፃፉት ደብዳቤ Aዋጅ ቁጥር 199/92 በAንቀጽ 31 የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት የሚፈልግ ሰው ከፍትህ ሚኒሰቴር የጥብቅና ፈቃድ ማግኘት Eንዳለበት ደንግጓል፣ Eንደዚሁም የግል ድርጅት ወይም ኩባንያ ኃላፊ ወይም ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ የሆኑ ሰዎች የጥብቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት Eንደሚችሉ በAዋጁ Aንቀጽ 31(1) ሥር ተደንግጓል፣ Eኔ Eነዚህን መስፈርቶች ስለማላሟላ የጥብቅና Aገልግሎት ብሰጥ በሕጉ Eቀጣለሁ፣ የድርጅቱን ወይም የኩባንያውን ጥቅም
ለማስጠበቅ በፍርድ ቤት መከራከር ሕጋዊ የውክልና ሥልጣን የተሰጠው ሰው፣ የኩባንያ ኃላፊ፣ ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ፍ/ሚኒሰቴር የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጠው የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ላልሆነ ሰው
Eንጂ ለሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ Aይደለም፡፡ በመሆኑም መመርያችሁን
Eጠብቃለሁ ማለታቸውን ተመልክተናል፡፡ የዚህ ደብዳቤ ይዘት ደግሞ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሆኜ መስራት ብቀጥል የጥብቅና ፈቃድ ስለማይሰጠኝ የጥብቅና ፈቃድ ማግኘት Aልችልም፡፡ ያለ የጥብቅና ፈቃድ ለመስራት የሚቻልበት ሌላው Aማራጭ ደግሞ የኩባንያው ሐላፊ ባለAክሲዮን ወይም
ሸሪክ በመሆን ቢሆንም Eኔ ባለAክሲዮን ወይም ሸሪክ ወይም ደግሞ የኩባንያው ኃላፊ ባለመሆኔ የጥብቅና Aገልግሎት መስጠት Aልችልም፡፡ ፈቃድ ሳይወጣልኝ ወይም ባለAክሲዮን ሆኜ ሳልመዘገብ የሕግ Aገልግሎት ለኩባንያው ብሰጥ በወንጀል የምቀጣ በመሆኑ መፍትሄ Eስከሚፈለግልኝ ጊዜ ድረስ የተቀጠርኩበትን ሥራ Aላከናውንም የሚል ነው፡፡
ተጠሪው መጋቢት 18 ቀን 1993 ዓ.ም ባዘጋጁት የክስ ማመልከቻና ታህሳስ 17 ቀን 94 ዓ.ም ባቀረቡት የመልስ መልስ የጥብቅና Aገልግሎት ለመስጠት በቅድሚያ የጥብቅና ፈቃድ Eንደሚያሻ፣ ፈቃድ ሳይኖር Aገልግሎት መስጠት በወንጀል Eንደሚያስጠይቅ፣ ለግል ኩባንያም ቢሆን ያለ ጥብቅና ፈቃድ Aገልግሎት መስጠት የሚችሉት የድርጅት ሃላፊ ወይም ሸሪክ መሆን Eንደሚያስፈልግ የጠበቆች Aዋጅ ይደነግጋል፤ ላይሰንስ (የጥብቅና ፈቃድ) የማገኝበት መንገድ ሳይቀየስና ፈቃድ ሳይኖረኝ ብሰራ በወንጀል Eንደምቀጣ Eየታወቀ Aቶ ዳንኤል ተገኑ ሆራ ሆቴል በሚመለከት የሕግ Aገልግሎት Eንድሰጥ ማዘዛቸው Eኔን ለማስወንጀል ወይም ደግሞ የተመደበበትን ሥራ Aልሰራም ብሏል በማለት Eርምጃ ለማስወሰድ የታሰበ
ነበር በማለት ያቀረቡት ክርክርም ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ ወይም ደግሞ የባለAክሱዮንነት ምዝገባ ካላደረገልኝ ሥራውን Aልሰራም ማለታቸውንና ሆራ ሆቴልን የተመለከተውን ሥራም ሳያከናውኑ
መቅረታቸውን በማመን የተከራከሩ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው፡፡
Aቶ ዳንኤል ተገኑ ሰኔ 7 ቀን 1993 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ Aቶ በዛወርቅ ሽመላሽ የሆራ ሆቴል ኮንትራትን በተመለከተ የሕግ Aስተያየት Eንዲሰጡ Eንደነግራቸው በተሰጠኝ መመሪያ መሠረት ብነግራቸውም Aዲሱ ሕግ Aይፈቅድልኝም በማለት የሕግ Aስተያየታቸውን ለመሰጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል በማለት የሰጡትን መግለጫ ተጠሪው በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስና የመልስ መልስ ከጠቀሷቸው የመከራከሪያ ነጥቦች ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው ተጠሪው በኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ የማገኝበት
ሁኔታ ካልተመቻቸልኝ Eና ፈቃዱን ካልያዝኩኝ በስተቀር ለድርጅቱ የሕግ Aገልግሎት Aልሰጥም በሚል Aቋማቸው መሠረት ሆራ ሆቴልን የሚመለከት የሕግ Aስተያየት ሳይሰጡ የቀሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሆኖ Aግኝተነዋል፡፡
Eንደዚሁም ተጠሪው ነሐሴ 9 ቀን 1992 ዓ.ም ለAቶ ንጉሴ በፃፉት ደብዳቤ ሆራ ሆቴልን የሚመለከት የሕግ Aስተያየት Eንድሰጥ በAቶ Aልፍሬድ መመሪያ መሰጠቱን Aቶ ዳንኤል ነግሮኛል Eንዲህ ዓይነት የሕግ Aስተያየት (ምክር) መስጠት በAዲሱ Aዋጅ ሊያስጠይቅ ይችላል Eያልኩኝ Eየወተወትኩኝ Eንደዚህ ዓይነት መመሪያ ለምን Eንደተሰጠ Aልገባኝም፣ Aሁንም ቢሆን በቅድሚያ የጥብቅና ፈቃድ የማገኝበት መንገድ Eንዲቀየስ Aሳስባለሁ ማለታቸው ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ስላላስወጣልኝ ሥራውን Aላከናውንም በማለት የሕግ Aገልግሎት ሳይሰጡ መቅረታቸውንና
ለወደፊቱም ድርጅቱ ፈቃዱን ካላስወጣላቸው በስተቀር የተመደቡበትን የሕግ
Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Eንደማያከናውኑ የሚያስረዳ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ተጠሪው በስር ፍ/ቤቶች ባደረኩት ክርክር Aመልካች /የሥር ተከሳሽ/ ኩባንያው ለቀጠራቸው የሕግ ባለሞያዎች የጥብቅና ፈቃድ የማስወጣት ግዴታ ያለበት መሆኑንና ይህን ግዴታውን መወጣት ሲገባው ሳይወጣ የቀረ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ Aላቀረቡም፡፡ ኩባንያው ይህ ዓይነቱ ግዴታ ያለበት መሆኑን የሚደነግግ ሕግ Aለ ብለው Aልጠቀሱም Aልተከራከሩምም፡፡ ኩባንያው ሰዎችን በባለAክሲዮንነት የሚመዘግብ ከሆነም የኩባንያውን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በማድረግ ከሚጠይቁ በስተቀር ተጠሪው የሕግ Aገልግሎት Eንዲሰጡ ተብሎ በባለAክሱዮንነት ወይም በሸሪክነት ሊመዘግባቸው የሚገደድበት ምክንያት የለም፡፡ ተጠሪም በፃፉት ደብዳቤ በምሳሌነት ጠቀሱት Eንጂ ኩባንያው በባለAክሲዮንነት ወይም በሸሪክነት Eንዲመዘግባቸው በግልጽ የጠየቁ ባለመሆኑ ይህን ነጥብ Aመልካች በክርክሩ ውስጥ ማካተቱ ተገቢ Aይደለም፡፡
ከዚህ በላይ በተዘረዘረው ሁኔታ ተጠሪው የጥብቅና ፈቃድ በኩባንያው Aማካኝነት ካልወጣልኝ በስተቀር የተመደብኩበትን የሕግ Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም በማለት ሥራ ማቆማቸው
ራሳቸው ባደረጉት ክርክር ያመኑበትና ከግራ ቀኙ በቀረቡት የጽሑፍ ማስረጃዎች የተረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪው የተቀጠርኩበትን ሥራ Aልሰራም Aላልኩም በማለት ለሰበር Aቤቱታው በሰጡት መልስና በቃልም ባደረጉት
ክርክር መግለፃቸው ተቀባይነት የለውም፡፡
ሌላው ቁምነገር ደግሞ ተጠሪው ኩባንያው የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ የሕግ Aገልግሎት ሥራ Aልሰራም፣ ከሠራሁኝ በወንጀል Eቀጣለሁ የሚሉት ቀደም ብለው የወሰዱትን የጥብቅና ፈቃድ ሳይመልሱና የሕግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችም በውክልና የሕግ ባለሞያዎችን Eንዳያሰሩ በAዋጅ ባልተከለከለበት ጊዜ ነው፡፡ የጥብቅና ፈቃድ Eያላቸው በውክልናም መሥራት Eየቻሉ ለኩባንያው የሕግ Aገልግሎት ብሰጥ በወንጀል Eቀጣለሁ ማለታቸውም ግልጽ Aይደለም፡፡
Aመልካች ለቀጠራቸው የሕግ ባለሞያዎች ከፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፈቃድ የማስወጣት ግዴታ ሳይኖርበትና ተጠሪው ለAመልካች የጥብቅና ማለትም የሕግ Aገልግሎት ቢሰጡ በወንጀል የሚቀጡበት የሕግ ምከንያት በሌለበት ጊዜ ተጠሪው ድርጅቱ የጥብቅና ፈቃድ ካላስወጣልኝ በስተቀር የተቀጠርኩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም የሚሉበትና Aመልካች ደግሞ ተጠሪው ምንም ሥራ ሳይሰሩ ሰራተኛዬ ናቸው በማለት ደሞዝ Eየከፈለ የሚቆይበት ምከንያት የለም፡፡ ተጠሪው በAዋጅ ቁጥር 42/85 Aንቀጽ 13(2) ሥር የተደነገገው የAሠሪውን ትEዛዝ የመቀበል ግዴታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ Aመልካች በAዋጁ Aንቀጽ 26(1) መሠረት ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ቅጥር ውሉን ለማቋረጥ ይችላል፡፡ Aመልካች የሥራ ውሉን በAዋጁ Aንቀጽ 26 Eና 28 መሠረት ማቋረጡና ተጠሪውን ማሰናበቱም በAግባቡ ነው፡፡
በመሆኑም Aመልካች ተጠሪውን ከሥራ ያሰናበታቸውን የተቀጠሩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተጨባጭ የሥራ ትEዛዝን Aልቀበልም በማለታቸው ምክንያት መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠና ተጠሪም ያመኑበት ሆኖ Eያለ የሥር ፍርድ ቤቶች ስንብቱ ሕገወጥ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪው ካሣ ይከፈል በማለት ውሳኔ መስጠታቸው Aግባብ ሆኖ Aላገኘነውም፡፡ ፍርድ ቤቶቹ የግራ ቀኙን
ክርክርና የቀረበላቸውን ማስረጃ በሚመለከት ውሳኔ መስጠት ሲገባቸው የቀረበላቸው ማስረጃ የሚያስረዳውን ቁምነገር በመተውና ተጠሪው በክርክራቸው ያመኑትን ከግምት ውሰጥ ባለማስገባት የተጠሪውን የግል ማህደር በማስቀረብ ተጠሪው የተቀጠሩበትን ሥራ ለማከናወን ፈቃደኛ
Aለመሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከማሕደራቸው ስላላገኘን ለመስራት
ፈቃደኛ ስላለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ የለም፣ ስንብቱ ሕገወጥ ነው፣ Aመልካች ለተጠሪው ካሣ ይከፈል በማለት የሰጡት ውሳኔም የAዋጅ ቀጥር 42/85 ዓላማን የሳተና ለተጠሪው የማይገባቸውን መብት ያጐናፀፈ በመሆኑ ውሳኔው መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትና መታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ው ሳ ኔ
1. የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/08459 ህዳር 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 43679 ሚያዝያ 17 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሠረት ተሽረዋል፡፡
2. ተጠሪው ከሥራ የተሰናበቱት ድርጅቱ /ኩባንያው/ የጥብቅና ፈቃድ ካላወጣልኝ በስተቀር የተቀጠርኩበትን የሕግ ምክር Aገልግሎት የመስጠት ሥራ Aላከናውንም በማለታቸውና በተጨባጭም ሆራ
ሆቴልን የተመለከተ የሕግ Aስተያየት Aልሰጥም በማለታቸው ምክንያት መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ስንብቱ ሕጋዊ ነው፡፡ የሥራ ስንብት ክፍያ ሊከፈላቸው Aይገባም በማለት ወስነናል፡፡ ፍፃፍ፡፡
3. ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ወጪና ኪሣራ ይቻሉ ብለን መዝገቡን ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል፡፡
የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት
ፀ/መ
¨< ` e