ስምምነቱ በአገራችን ላይ የሚጥለዉ ግዴታ. ስምምነቱ በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ስምምነት እንደመሆኑ በአገራችን ላይ የሚጥላቸው ልዩ ልዩ ግዴታዎች አሉ። ከእነዚህ መካከልም ዋነኛው በቱርክ ሪፐብሊክ መንግስት በሚቀርብ የትብብር ጥያቄ መሠረት ስምምነቱን እና ሀገራችን ህግን መሰረት በማድረግ በወንጀል ምርመራ፣ ክስ እና የክርክር ሂደት ላይ ባሉ ጉዳዮች ሚፈለጉ ማስረጃዎችን እና መረጃዎችን የመስጠት እንዲሁም ለወንጀል መፈፀሚያነት የዋሉ፣ ሊዉሉ የታሰቡ ወይም የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችን የመያዝ፣ የማገድ እና የመዉረስ ግዴታ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ትብብሩን ለማድረግ የሚወጣው ወጪ በአገራችን በኩል እንዲሸፈን ግዴታን ይጥላል። ነገር ግን ትብብሩን ለማድረግ የሚያስፈልገዉ ወጭ መደበኛ ከሆነዉ ወጭ የተለየ እና ትብብር አድራጊ ሀገርን ከፍተኛ ወጭ የሚያስወጣ ከሆነ ወጭዉን ትብብር ጠያቂ ሀገር እንዲሸፍን ማድረግ የሚቻል መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም በአጠቃላይ የትብብር ስምምነቱ ተፈጻሚነት በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በሀገራችን በኩል በቱርክ መንግስት የሚቀርብ ጥያቄ የሚስተናገደው በቱርክ መንግስት የሚቀርብን ጥያቄ ሀገራችን በምታስተናግድበት አግባብ ይሆናል። 3.