ማጠቃለያ እና አበይት ምክረ ሃሳቦች/የእርምት እርምጃዎች የናሙና ክፍሎች

ማጠቃለያ እና አበይት ምክረ ሃሳቦች/የእርምት እርምጃዎች. ማጠቃለያዎችና ምክረ ሃሳቦችን፣ እንደዚሁም ማናቸውንም ክፍተቶች ወይም እልባት ያላገኙ ጉዳዮችን በጊዜ የተገደበ የእርምት ድርጊት መርሃ ግብርን ከአበይት እርምጃዎች፣ የተመደበ የሰው ሐይል፣ የመዝጊያና የበጀት የጊዜ ሰሌዳ አጠር ባለ መልኩ ማጠቃለል፡፡ የሚጠበቁ ውጤቶች - ከ RAP የሚጠበቁ ውጤቶች በግልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ሊካተቱ ይችላሉ፡ • የሰፈራ የድርጊት መርሃ-ግብር • የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ዕቅድ • የኦዲት ፕሮግራም ስነዳ • የቅሬታ አቀራረብ ሒደቶች የፕሮፖዛል መስፈርቶች - ይህ ክፍል ተፈላጊ የሥራ መርሃ ግብር፣ ማናቸውም የፋይናንስ መስፈርቶችን (ለምሳሌ፡ የበጀት ጣሪያ፣ የመጫረቻ ገንዘብ፣ የወጪ ክፍፍል ዝርዝሮች፣ የተለያዩ የፋይናንስና የንግድ ፕሮፖዛሎች)፣ የሚጠበቅ ድርጅታዊ ልምድ፣ የተጠቆመ የፕሮጄክት ቡድን ጥንቅርና ልምድ፣ እና አግባብነት ሲኖረውም የአካባቢ ይዘት/የአካባቢ ንዑስ ኮንትራክተር መስፈርቶችን መዘርዘር አለበት፡፡ ቅጥያ 10 የሃገር በቀል ሕዝቦች ዕቅድ የማነጻጸሪያ ነጥቦች አጠቃላይ መግለጫ ይህ ቅጥያ የሃገር በቀል ሕዝቦች ዕቅድ (IPP) የማጣቀሻ ነጥቦችን የሚዘረዝር ሲሆን ዕቅዱም በአካባቢና ማሕበራዊ ተጽእኖ ግምገማ (ESIA) ሒደት ወቅት በተለዩ ተጽእኖዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ IPP ለሚያስፈልጉት ለእያንዳንዱ ፕሮጄክት፣ CFM ከጋራ አልሚው ጋር በመተባበር የ IPP የማነጻጸሪያ ነጥቦችን ያዘጋጃል፡፡ IPP መዘጋጀት ያለበት እንደሁኔታው ተለዋዋጭ በሆነና ነገሮችን ባገናዘበ መልኩ ሲሆን የፕሮጄክቱን ዝርዝር ሁኔታና የውጤቶቹን ባህርይ ያማከለ መሆን አለበት፡፡ የ IPP ዓላማ ከባሕል አንጻር አግባብነት ባለው መንገድ በሃገር በቀል ሕዝቦች ላይ የሚደርሱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ እና/ወይም ለመካስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መግለጽ ነው፡፡ በ IFC መምሪያ ማስታወሻ 7 መሰረት፣ በአካባቢያዎ ተጨባጭ ሁኔታዎች መሰረት፣ ራሱን ችሎ የሚቆም ሊዘጋጅ ይችላል፣ ወይም በጉዳዩ የተነኩ የሃገር በቀል ሕዝቦች ማህበረሰቦች በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር በተመሳሳይ ቦታ የሚኖሩበት ወይም ሃገር በቀል ሕዝቦች በስፋት በጉዳዩ በተነካ ሕዝብ ውስጥ የሚዋሃዱበት ሰፊ የማህበረሰብ ልማት ዕቅድ አካል ሊሆን ይችላል፡፡ የ IPP የማነጻጸሪያ ነጥቦች አነስተኛ መስፈርቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡ መግቢያ እና ዳራ - የፕሮጄክት መግለጫ፣ እስካሁን ምን ዓይነት የተጽእኖ ግምገማ ስራ እንደተሰራና ምን ዓይነት የሃገር በቀል ሕዝቦች ጉዳዮች እንደተለዩ የሚያሳይ መግለጫ፡፡ የመጨረሻ ESIA ከተዘጋጀ፣ ይኸው መቅረብ አለበት፡፡ የተሟላ ESIA ዝግጁ ካልሆነ፣ በጉዳዩ የተነኩ ማህበረሰቦችን ግልጽ መገለጫ፣ መተዳደሪያቸውንና ሁኔታዎቻቸውን በተመለከተ በቂ ዝርዝር መቅረብ ያለበት ሲሆን በሃገር በቀል ህዝቦች ላይ ጥገኛ የሆኑ የተፈጥሮ ሐብቶችን እንደዚሁም ሊያስከትሉ የሚችሏቸውን ተጽእኖዎች መግለጽና በቁጥር ማስቀመጥ ይገባል፡፡ የ IPP መለኪያዎች - በዚህ ውስጥ መካተት ያለባቸው የ IFC የአፈጻጸም መለኪያዎች 7 እና የመምሪያ ማስታወሻ 7፣ እንደዚሁም የአካባቢ ፖሊሲና ሕግ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የተገኘ ካልሆነ፣ የማነጻጸሪያ ነጥቦች በ IFC የአፈጻጸም መለኪያዎችና በአካባቢ መለኪያዎች መካከል ባለው ልዩነት ላይ የክፍተት ትንተና የማካሄድን አስፈላጊነት ያካትታል፡፡ ከመስፈርቶቹ ሁሉ ጥብቅ የሆነው በ IPP ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ CFM እና የጋራ አልሚው ፕሮጄክቱ ከ IFC የአፈጻጸም መለኪያ 7 ወይም የአካባቢ መለኪያዎች ባሻገር እንዲሄድ በሚጠይቁበት ወቅት፣ ይኸው በግልጽ መመልከት አለበት፡፡ የአገልግሎቶች ወሰን - ይህ ክፍል የተግባሩን አጠቃላይ ዓላማዎችና ወሰን ይገልጻል፡፡ በአፈጻጸም መለኪያ 7/ በመምሪያ ማስታወሻ 7 መሰረት፣ እነዚህ ተግባራት ማካተት ያለባቸው፡ • የመነሻ ሁኔታዎችን ማጠቃለል፡ በ ESIA ውስጥ በቀረበው መሰረት የፕሮጄክቱን ሃገር በቀል ሕዝቦች የሚመለከት የመነሻ መረጃን ማጠቃለል፡፡ በጉዳዩ የተነኩ ማህበረሰቦችን ግልጽ መገለጫ፣ መተዳደሪያቸውንና ሁኔታዎቻቸውን በተመለከተ በቂ ዝርዝር መቅረብ ያለበት ሲሆን በሃገር በቀል ህዝቦች ላይ ጥገኛ የሆኑ የተፈጥሮ ሐብቶችን መግለጽና በቁጥር ማስቀመጥ ይገባል፡፡ • ሃገር በቀል ሕዝቦችን በተመለከተ የ ESIA ግኝቶችን ማጠቃለል፡ ከ ESIA የተገኙ ተጽእኖዎች፣ ስጋቶችና መልካም አጋጣሚዎችን በማጠቃለል ተጽእኖዎችን ለማቃለል፣ አዎንታዊ ጎኖችን ለማሳደግና ዘላቂ የማህበረሰብ ልማት ላይ ለመድ...