ክፍል ሶስት የሆርቲካልቸር ልማት የናሙና ክፍሎች

ክፍል ሶስት የሆርቲካልቸር ልማት. የሆርቲካልቸር ኢንቨስትመንት ማለት “የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 ‘ትን መስፈርት አሟልቶ በአበባ፣ በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ ዕፀ-ጣዕምን ጨምሮ በሌሎች የሆርቲካልቸር መዓዛማ ሰብሎችን ማምርት ላይ የሚደረግ የኢንቨስትመንት መስክ ሲሆን የሚከተሉትን የምዘና (የምልመላ) መስፈርቶችና ነጥቦች የያዘ ይሆናል። እነዚህም ፦ i. የአቅርቦት እና ኤክስፖርት ገቢ አፈጻጸም (40%) ⇒ እንደ ሀገር ካሉት በዘርፉ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ ካለው የመሬት ይዞታ ጋር ተነጻጽሮ ከፍተኛ ኤክስርት ማድረግ የቻለ፤ ⇒ የማይዋዥቅ እና ወጥ የሆነ የኤክስፖርት የመጠን የሚያደርግ ወይም ከአመት አመት የኤክስፖርት መጠኑ እያደገ የመጣ፤ ⇒ የወጭ ምንዛሬን በወቅቱ በማስገባት እዳ ውስጥ የማይገባ፤ ⇒ ኩባንያው ምርቱን ለተለያዩ የገበያ መዳረሻ ለማቅርብ ያገኘው አለም አቀፍ ሰርተፍኬት ብዛት → ከላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ ከሆነ (40 ነጥብ) → በከፊል ያሟላ ከሆነ (20 ነጥብ) → በጥቂት የሚያገኝ (10 ነጥብ) → መስፈርቱን የማያሟላ ከሆነ ምንም ነጥብ አያገኝም → ነሀስ (10%) ii. የአምራቾችን የአሰራር ደንብን መተግበር (15%) → ብር (13%) → ወርቅ (15%) iii. ጥሩ የአመራረት ሂደት (Good Agricultural Practice) (15%) ⇒ የኬሚካል አጠቃቀም → የተፈቀደ/የተመዘገበ ኬሚካል በአግባቡ የሚጠቀም ከሆነ → አስፈላጊውን የኬሚካል ትጥቅ ለሰራተኞች የሚያቀርብ ከሆነ → ኬሚካል ርጭት ከተደረገ በኋላ ተመልሶ ስራ የሚጀምርበት ሰዓት እንደ ኬሚካሉ አቅጣጫ መሰረት በስርዓቱ የሚተገበር ከሆነ → አስፈላጊውን ግብአት የሚያሟላ ከሆነ (ሻወር ፤ ልብስ ማጠቢያ ቦታ ፤ የተለየ ልብስ መቀየሪያ እና ማስቀመጫ) → አስፈላጊውን ምርመራ በየ 3 ወሩ የሚያደርግና እንደ አስፈላጊነቱ ችግር የታየባቸውን ሰራተኞችን ከርጭት ክፍል የሚቀይር ከሆን → ትክክለኛ የኬሚካል እና ማዳበሪያ መጋዘን አያያዝ ካለ → ሴት ሰራተኞችን ከኬሚካል ጋር ተያያዥነት ባላቸው ስራዎች ላይ የማይመድብ ከሆነ (ስቶርኪፐርን ጨምሮ) → የኬሚካል ማስወገጃ ቦታ ካለውና በስርዓቱ የሚያስወግድ ከሆነ → በተቀናጀ የተባይ መከላከያ የሚጠቀም ከሆነ ⇒ የውሃ አጠቃቀም → የታደሰ የውሃ (የጉድጓድ ፤ የወንዝ) የመጠቀም ፍቃድ መኖሩ ⇒ የቆሻሻ አወጋገድ → አግባብነት ያለው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚከተል ከሆነ፤ የቆሻሻ ማቃጠያ ኢንሲሬተር የሚጠቀም ከሆነ → አግባብነት ያለው የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የሚተገብር ከሆነ ⇒ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ/EIA and EMP/ ሰነድ ዝግጅትና አተገባበር → ከታወቀ አማካሪ ድርጅት የአካባቢ ተጽኖ ግምገማ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የቻለ፤ → የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ መሰረት እቅድ በማውጣት የተግባር ስራ የጀመረ፤ → ለእርሻ ላይ የአካባቢ መኮንን ፤ የአካባቢ ኮሚቴ ስልጠና መሰጠቱ እና ሁሉም አባላት በስራ ላይ መሆናቸው → አመታዊ የዳሰሳ ጥናት መደረጉ ፤ እንዲሁም የመፍትሄ እርምጃዎች መወሰዳቸው ⇒ የደን እንክብካቤ → ችግኝ ጣቢያ አቋቁሞ ችግኞችን በማፍላት ለልማት አመቺ ያልሆኑ አካባቢዎችን በደን መሸፈን እና በአካባቢው ላሉ ማህበረሰብ ማሰራጨት የቻለ፣ ⇒ የአፈር መከላትን መንከባከብ → በይዞታው ላይ ለአፈር መሸርሸር ተጋላጭ የሆኑትን የመሬት አካል በመለየት ስነ ህይወታዊና ፊዚካል መከላከያዎችን መስራት ከቻለ፣ → አሰራሩን አቅርቢያ ላሉ ማህበረሰቦች በማስተማር እንሱም እንዲተገብሩት ድጋፍ ማድረግ የቻለ፣ • ከላይ የተቀመጡትን መስፈር የሚያሟላ ከሆነ (15 ነጥብ) • በከፊል የተጠቀመ (7.5 ነጥብ) • በጥቂት ካሟላ (3.5 ነጥብ) • ምንም ያልተጠቀመ ዜሮ ነጥብ የሚያገኝ ይሆናል iv. የሰራተኞች እርሻ ላይ የደህንነት አጠባበቅ (10 %) → ለእርሻ ላይ የደህንነት ጤንነት መኮንን፤እንዲሁም ለደህንነት ጤንነት ኮሚቴ አባላት ስልጠና መሰጠቱ እና ሁሉም አባላት በስራ ላይ መሆናቸው → የእርሻ ላይ አቅርቦቶች (የመጠጥ ውሃ፤ መፀዳጃ ቤት፤ ሻወር ፤ የልብስ መቀየሪያ፤ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ፤ ምግብ መመገቢያ) በበቂ ሁኔታ መኖራቸው ⇒ የሰራተኛ አያያዝ → ሰራተኞች በኢትዮጵያ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 መሰረት መስራታቸው → ለሰራተኞች አስፈላጊው ስልጠና መሰጠቱ (የሰራ ቦታ፤ የደህንነት፤ የትጥቅ አጠቃቀም) ⬤ ሙሉ በሙሉ ማዋል ከቻለ (10 ነጥብ) ⬤ ግማሹን ያዋለ (5 ነጥብ) ⬤ በጥቂት ያሟላ (2.5 ነጥብ) ⬤ ምንም ያላሟላ (0 ነጥብ) የመሬት አጠቀቃም መስፈረት...