የምዘና መስፈርቶች የናሙና ክፍሎች

የምዘና መስፈርቶች. በግብርና ኢንቨስትመንትና በግብርና ምርት ውል (Contract Farming) ተሰማርተው የተሻለ አፈፃጸም ያላቸውን ኩባንያዎች ከተቋሙና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት የሚለይ ሆኖ የመመልመያው መስፈርቱም በተወሰነ መልኩ እንደየዘርፉ ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ዝርዝር የመመልመያ መስፈርቱም የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦችን ያካተተ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ መመዘኛ የሚይዘው የነጥብ ክብደት ለሀገር ከሚያበረክቱት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ፋይዳ አንጻር የሚታይ ይሆናል፡፡