ክፍል አራት፡ የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት የናሙና ክፍሎች

ክፍል አራት፡ የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት. የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት ማለት “የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012’ትን መስፈርት አሟልቶ በብዕርና በአገዳ ሰብል፣ በቅባት ህሎችና በሌሎች ንዑስ ዘርፎች ማምርት ላይ የሚደረግ የኢንቨስትመንት መስክ ሲሆን የምዘና መስፈርቱም የሚከተሉትን ነጥቦች የሚይዝ ይሆናል፡- የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት የልማት እንቅስቃሴ መመዘኛ መስፈርት/ነጥብ አሰጣጥይህ የፍረጃ መመዘኛ የመሬት ልማት እንቅስቃሴ መሻሻል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ በዚሁ መሰረት የለማ መሬት፣ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት፣ የካምፕ አደረጃጀትና የሠራተኛ አያያዝ፣ የሠራተኛ ቅጥር ለኢንቨስትመንቱ ባላቸው ወሳኝ ሚና አንፃር ታይቶ ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችና ነጥቦች ለፍረጃ ተወስደዋል፡፡ i. በገባው ውል መሠረት የለማ (በሰብል የተሸፈነ) መሬት መጠንና ምርታማነት (42 ነጥብ) በሰብል የተሸፈነ መሬት መጠንና የምርታማነት ሥራዎችን ለመመዘን በሁለት መመዘኛ ቀርበዋል፣ እነሱም፡- ሀ) የለማ (በሰብል የተሸፈነ) መሬት መጠን (30%) ፡- በዚህ ንኡስ መመዘኛ ስር የሚካተቱ ተግባራት ⇒ አንድ ኩባንያ በውሉ መሰረት ማልማት ከሚጠበቅበት የመሬት መጠን ውስጥ ያለማውን መሬት መቶኛ በመውሰድ ለዚህ መገምገሚያ መስፈርት የተሰጠውን ነጥብ ውስጥ ተሰልቶ የሚቀመጥለት ይሆናል፡፡ በዚህም፡- → ሙሉ በሙሉ ማዋል ከቻለ (30 ነጥብ) → ግማሹን ያዋለ (15 ነጥብ) → በጥቂት ያሟላ (7.5 ነጥብ) → ምንም ያላሟላ (0 ነጥብ) ለ) የሰብል ልማት ኩባንያው ለማልማት በገባው ውል (በቢዝነስ ፕላኑ) መሰረት ምርታማነቱ የሚታይ ይሆናል (20 ነጥብ)፡- ⇒ የኩባንያው ምርትና ምርታማነት የሚገመገመው በቢዝነስ ፕላኑ ላይ ከተቀመጠው አንፃር ሲሆን ምርታማነት ተገምግሞ አማካዩ ነጥብ የሚቀመጥለት ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት፡- → የተመዘገበው ምርታማነት በቢዝነስ ፕላኑ 95 – 100 % መሰረትና ከዚያ በላይ ከሆነ (20 ነጥብ) → ምርታማነቱ ከእቅዱ ከ 85% - 94% የተመዘገበ ከሆነ (16 ነጥብ) → ከእቅዱ ከ75% - 84% የተመዘገበ ከሆነ (14 ነጥብ) → ከእቅዱ ከ55%- 75% የተመዘገበ ከሆነ (10 ነጥብ) → ከእቅዱ ከ 40 % - 54% የተመዘገበ ከሆነ (8 ነጥብ) → 40 % በታች (2 ነጥብ ይሆናል) ii. የአከባቢ ጥበቃና አያያዝ (20 ነጥብ) የባለሀብቶች የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ለመመዘን ሰባት መመዘኛ ቀርበዋል እነሱም፡-