የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ የናሙና ክፍሎች

የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ. ባለፉት አስራ አንድ ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- ✓ በፌዴራል እና በክልል ማረሚያ ቤቶች በሥራ ላይ ያሉ ደንቦች እና መመሪያዎችን የማሰባሰብ ሥራ ተጠናቅቋል። ደንብ እና መመሪያዎች ላይ ጥናት በማድረግ የመነሻ ጥናት ለማከናወን የአማካሪ ቅጥር ተፈጽሟል። ሞዴል የማረሚያ ቤት አዋጅ በኮሚሽኑ በኩል የማዘጋጀት ሥራ ከተጀመረ በኋላ በፍትህ ሚኒስቴር በኩል ተመሳሳይ ሥራ ተከናውኖ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ በመታወቁ ተመሳሳይ ሥራ በሁለት ተቋማት ከማከናወን ይልቅ በፍትህ ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀውን ረቂቅ ከሰብአዊ መብቶች ስታንዳርዶች አንጻር በመገምገም እና አስተያየት በመስጠት በሁለቱ ተቋማት የጋራ ውትወታ (advocacy) ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ኮሚሽኑ ረቂቅ አዋጁን በመፈተሽ ላይ ነው። ✓ የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል መመሪያ፣ ቼክሊስቶች እና ረቂቅ የሪፖርት አዘገጃጀት ቅጾች በተቋሙ አመራሮች አስተያየት እና ግብአት ተሰጥቶባቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። ✓ በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ በኮሚሽኑ የበላይ አመራር ጸድቀው ወደ ትግበራ ይገባሉ። ✓ በፌዴራል እና በክልል ማረሚያ ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማቆያዎች ድንገተኛ እና መደበኛ ክትትል ተደርጓል። በዚህም መሰረት በመጀመሪያው ሩብ አመት በጅማ (16 ፖሊስ ጣቢያዎች)፣ በጋምቤላ (3 ማረሚያ ቤት እና 2 ፖሊስ ጣቢያዎች)፣ በጂግጅጋ (3 ማረሚያ ቤቶች እና 1 ፖሊስ ጣቢያ) የሰብአዊ መብት ክትትል ማድረግ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ በመደበኛ ዕቅድ መሠረት 6 ማረሚያ ቤቶችንና 19 ፖሊስ ጣቢያዎችን፣ እንዲሁም አቤቱታን መሰረት በማድረግ ደግሞ 1 ማረሚያ ቤት፣ 3 ፖሊስ ጣቢያዎችን እና 1 ጊዜያዊ ማቆያ ላይ በአጠቃላይ በ30 ተቋማት ላይ ክትትሎችን ለማድረግ ተችሏል፡፡ ✓ በሁለተኛው ሩብ አመት በዋናው መ/ቤት (3 ማረሚያ ቤቶች)፣ በጅማ (39 ፖሊስ ጣቢያዎችና 10 ማረሚያ ቤቶች)፣ ጋምቤላ (3 ማረሚያ ቤቶች እና 2 ፖሊስ ጣቢያዎች) በጅግጅጋ (5 ማረሚያ ቤቶች እና 8 ፖሊስ ጣቢያዎች)፣ በአሶሳ (10 ፖሊስ ጣቢያዎች) በድምሩ 21 ማረሚያ ቤቶች እና 59 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ለማድረግ ተችሏል። ✓ በሶስተኛው ሩብ አመት በዋናው መስሪያ ቤት (በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 24 ጣቢያዎች እና 5 ፌደራል ማረሚያ ቤቶች)፣ በጅማ ፅ/ቤት በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ (በ63 ፖሊስ ጣቢያዎች እና 19 ማረሚያ ቤቶች )፣ በባህርዳር ፅ/ቤት በአማራ ክልል በሚገኙ (በ25 ፖሊስ ጣቢያዎች እና 10 ማረሚያ ቤቶች)፣ በሀዋሳ ፅ/ቤት በሲዳማ እና ደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች ክልሎች በሚገኙ (9 ማረሚያ ቤቶች እና 40 ፖሊስ ጣቢያዎች)፣ የጅግጅጋ ፅ/ቤት (በ 1 ማረሚያ ቤት)፣ በአሶሳ ፅ/ቤት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ (1 ማረሚያ ቤት እና 6 ፖሊስ ጣቢያዎች) እና በጋምቤላ ፅ/ቤት (በ 7 ፖሊስ ጣቢያዎች እና 2 ማረሚያ ቤቶች) ላይ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ ተችሏል፡፡ ✓ በአራተኛው ሩብ አመት በዋናው መ/ቤት (28 ፖሊስ ጣቢያዎች እና 5 የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች) በጅማ ጽ/ቤት (1 ማረሚያ ቤት እና 8 ፖሊስ ጣቢያዎች) በጅግጅጋ ጽ/ቤት 2 ማረሚያ ቤት እና 7 ፖሊስ ጣቢያዎች) በሃዋሳ ጽ/ቤት (8 ማረሚያ ቤቶች እና 23 ፖሊስ ጣቢያዎች) በጋምቤላ ፅ/ቤት (በ 1 ማረሚያ ቤት እና 3 ፖሊስ ጣቢያዎች)፣ በአሶሳ ጽ/ቤት (በ1 ማረሚያ ቤት እና 2 ፖሊስ ጣቢያዎች)፣ ላይ የሰብአዊ መብቶች ክትትል አከናውኗል፡፡ ✓ በአጠቃላይ ኮሚሽኑ በ11 ወራት ውስጥ የሪፖርት ወቅት በመላ ሀገሪቱ 95 የማረሚያ ቤት ክትትሎች እንዲሁም ✓ በተደረጉት ክትትሎች የሰብአዊ መብቶች ማሻሻያዎች እንዲደረጉ በኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን በተደረጉ ውይይቶች በመጀመሪያው ሩብ አመት በጅማ ቅርንጨፍ ክትትል 120 ሰዎች እንዲሁም በጋምቤላ ክትትል 7 ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ለማድረግ ተችሏል፡፡ ✓ በሁለተኛው ሩብ አመት በጅማ ክትትል 196 ሰዎች እንዲሁም በጋምቤላ ክትትል 7 ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ለማድረግ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው አካላተ ጋር በመወያየት በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ሰላምበር ከተማ 37 ሰዎች በዋስ እንዲለቀቁ ማድረግ የተቻለ ሲሆን እንዲሁም የእስረኖች አያያዝ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሰዎች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እና ሌሎችም ምክረ ሃሳቦች ተሰጥተዋል። በክትትል ወቅት በሰላም በር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ከሕግ አግባብ ውጪ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ተጨማሪ 7 ሕፃናትን በተደረገው ውትወታ ከእስር ለመለቀቅ ...