የአካላዊ እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው (Physical impairment) ህጻናትና ተማሪዎች የናሙና ክፍሎች

የአካላዊ እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው (Physical impairment) ህጻናትና ተማሪዎች. ተሸከርካሪ ወንበሮች • ክራች (crutch) • መራመጃ መሳሪያዎች (xxxxxx) • መተላለፊያዎችን(Ramp)ለምሳሌ ወደ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መፃህፍት ቢሮዎች፣መፀዳጃ ቦታዎች፣ የሚወስዱ መተላለፊያዎችን መስራት • በኮሪደሮችና በመፀዳጃ ቤቶች የሚያገለግሉ የእጅ መደገፊያዎች (Hand rails), • አካላዊ ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ የተመቻቹ የመፀዳጃ ቤቶች (adapted toilets)፣ የውሃ ቧንቧ፣ቤተ-መጻህፍት፣ቤተ-ሙከራዎች 5.4 የዓዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ህጻናትና ተማሪዎች • የተለያዩ የሞንቴሶሪ ኪትስ (kits) • ቴሌቪዥንና ዲቪዲ • እራስን ችሎ ህይወትን ለመምራት የሚያስችል ክሂል መማሪያ አጋዥ የሚሆኑ ማጣቀሻ መፃህፍት o መማሪያ መፃህፍት o የሙያና ቴክኒክ ስልጠና ቁሳቁሶች ናቸው፡፡ 5.5 የንግግርና የተግባቦት ችግር ላለባቸው ህጻናትና ተማሪዎች • የንግግር ችግር ላለባቸው ልጆች አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የንግግር ስልጠና ኪት (kit) መስታወትን የጨምራል፣ • በስዕላዊ መረጃ የመግባቢያ ዘዴ መጠቀሚያ (PECS) 5.6 የድጋፍ መስጫ ማእከላትን ማቋቋም የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላትን ማቋቋም • በልዩ ትምህርት ቤትም ሆነ በአካባቢያቸው አካተው በሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች (ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ጨምሮ) ተገቢው ዕገዛ ይደረግ ዘንድ አስፈላጊውን የማስተማር ልምድና ሙያዊ ድጋፍ መስጠት • ለሁሉም ተማሪዎች ማለትም ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ጨምሮ የመማር ክሂላቸው እየዳበረ ይሄድ ዘንድ ተገቢውን የምክርና የጤና አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት • ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓቶች፤ ቁሳቁሶችና የአካል ድጋፍ መርጃ መሳሪያዎች (የዓይን መነፅር፤የማድመጫ መሳሪያ ፤ የመረማመጃ መሳሪያ ወዘተ) ማሟላት • ሁሉም ተማሪዎች ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ጨምሮ ወደ ትምህርት ገበታ ማምጣት ይችሉ ዘንድ አጎራባች ትምህርት ቤቶችን በስልጠና ማገዝ፤ የትምህርት ግብዓቶችን የማዋስ፤ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መላክ፤ የተማሪዎችን ችግር የመለየትና የመዳሰስ ተግባር እንዲከናወን ተገቢውን ድጋፍ መስጠት • ለተገቢው ዕገዛና ትብብር በአካባቢው ከሚገኙ ወላጆች፤ ትምህርት ቤቶች፤ ክሊኒኮች፤ የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤትና መያዶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል መረብ መፍጠር • በድጋፍ መስጫ ማዕከሉ በተቋቋመው ኮር ቲምና በመምህራን ትብብር የተመሰረተ ትምህርት ቤት-ዐቀፍ የዳሰሳ፤ የመለያና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላክና ከሆስፒታሎች ጋር በትብብር የመስራት ሁኔታዎችን ማደራጀት ናቸው፡፡ • አካላዊ ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ የተመቻቹ የመፀዳጃ ቤቶች (adapted toilets)፣ • በየክፍል መግቢያው መተላለፊያዎች (ramps/፣ • ከክፍል ወደ ክፍልና ከህንጻ ወደ ህንጻ መተላለፊያዎች፣ • መፀዳጃ ቤቶችን እንደ አካል ጉዳታቸው እንዲጠቀሙ፣ • ከውሃ ቧንቧ እንደ ጉዳታቸው ዓይነት መጠጣት እንዲችሉ፣ • በቤተ መጻህፍት እንደ ጉዳታቸው ዓይነት መጠቀም እንዲችሉ፣ • በቤተሙከራዎችና በሌሎችም እንደ ጉዳታቸው ዓይነት መጠቀም እንዲችሉ በየትምህርት ተቋማቱ ግብዓቶች ሊሟሉላቸው ይገባል፡፡ 6. ማህበረሰቡ በት/ቤቶች ድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ ክትትል እንዲያደርግና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል የአሠራር ዘዴ ማህበረሰቡ በትምህርት ቤቶች አሰራር ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአካባቢው ማህበረሰብ በትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት አስተቃቀድና አጠቃቀም ላይ ቁልፍ ድርሻ እንዲኖረው ተደርጎ በአተገባበር መመሪያው በግልጽ ተቀምጧል። ከዚህ አንጻር፦ • በትምህርት ሚኒስቴርና እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ለክልሎች የተላከውን ጠቅላላ የገንዘብ መጠን እንዲሁም ለእያንዳንዱ ክልልና ወረዳ የሚከፋፈለውን የገንዘብ መጠን የሚያሳዩ ደብዳቤዎች ቅጂዎች በግልጽ እንዲቀመጡና ለህብረተሰቡ በሚታዩበት አግባብ ለዚሁ በተዘጋጀው የማስታወቂያ ቦርድ እንዲለጠፉ ማድረግ መኖር፡፡ • ሁሉም ትምህርት ቤቶች . በየዓመቱ ጥቅምት 21 (እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 31) ላይ የድጎማ በጀታቸውን እነዲያገኙ ማድረግና መከታተል • ወረዳዎች ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት መሣሪያዎችን በማሟላት ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ ተብሉ የተመደበውን ተጨማሪ የትምህርት ቤቶች ድጎማ በጀት እንዲደርሳቸው ማ...