የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ያለበት ሁኔታ የናሙና ክፍሎች

የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ያለበት ሁኔታ. እ.አ.አ. በ2011 በአለም ጤና ድርጅት (WHO) የተደረገ ጥናት እንደሚጠቅሰው በዓለም ላይ በማንኛውም ማህበረሰብ ካለው ህዝብ ውስጥ 15 በመቶ የሚሆነው ልዩ ፍላጎት ያለው ነው። በመሆኑም በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም እንደተቀመጠው በሀገራችን እድሜያቸው ከ4-18 ዓመት የሆኑ ህጻናት 33.5 ሚሊዮን እንደሆኑና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ወደ 5 ሚሊዮን እንደሚገመቱ ተጠቅሷል። በመቀጠልም በ2006 ዓ.ም 77,850 ህጻናት ከ1ኛ-12ኛ ክፍል ባሉ የትምህርት ደረጃዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። በተጨማሪም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መማር ከሚገባችው ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ውስጥ 4 በመቶ ብቻ በመማር መሆናቸውን ያሳያል። በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ሰነድ ላይ እንደተዘረዘረው ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናትን ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይመጡ ከሚያደርጉ ተግዳሮቶች ውስጥ፦ • በልዩ ፍላጎት ትምህርት ላይ የህብረተሰቡ ግንዛቤ አናሳ መሆን • ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ባሉት መዋቅሮች የትምህርት አመራርሮች በልዩ ፍላጎት ትምህርት ላይ የታቀዱ ተግባራትን ለመተግበር ያላቸው የዕውቀት፣ የክህሎትና የተነሳሽነት ሁኔታ ማነስ • ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅና አመቺና ውጤታማ የሆኑ ስልቶችን ለመንደፍ ተዓማኒነት ያለው መረጃ ዕጥረት • ከፈደራል እስከ ወረዳና ት/ቤት ድረስ ባለው የትምህርት መዋቅር የልዩ ፍላጎት ትምህርትና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ዙርያ በቅንጅትና በትብብር ሊያሰራ የሚችል ግልጽ የሆነ መዋቅርና የአሰራር ስርዓት አለመኖር • የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርትን ለመደገፍ የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍና አሰራር ያለመኖር • የት/ቤቶች መሰረተ ልማትና የአገልግሎት መሳሪያዎች ደካማ መሆን፣ ለልዩ ፍላጎት ትምህርት የተዘጋጀ የመማር ማስተማር ስልት ያለመኖር፣ እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ መመሪያዎችና ስታንዳርዶች ያለመኖር • የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን የማስተማር ክህሎት ጠንካራ ያለመሆን • በልዩ ፍላጎት የሪሶርስ ማዕከላትና በሳተላይት ትምህርት ቤቶች ለሚሰሩ ተዘዋዋሪ መምህራንን ለመደገፍ የተዘረጋ የደረጃ ዕድገት ስርዓት ያለመኖር ተጠቃሽ ናቸው። 3. ልዩ ፍላጎት ላላቸው ህፃናት የተመደበ ተጨማሪ የት/ቤቶች ድጎማ በጀት ልዩ ፍላጉት ያላቸውን ህፃናት በትምህርት ድጋፍ ለማድረግና አመቺ የትምህርት አካባቢ እንዲኖራቸው ለመርዳት እንዲሁም የት/ቤቶች መገልገያዎች ለእነዚህ ህፃናት አመቺ እንዲሆኑ ለማድረግ ከትምህርት አመራር መረጃ ስርዓት በተገኘ መረጃ መነሻነት በ2008 በጀት ዓመት ክልሎች ከሚደርሳችው ጠቅላላ በጀት አንድ በመቶ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች እንዲውል ተመድቦ የነበረ ሲሆን ክልሎች በክልላቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ተግባራዊ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በዚህም መሰረት በት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም አተገባበርና በት/ቤት ድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ በተከናወነ ጥናት እንዲሁም ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በተከናወነ የጋራ ግምገማና ክልላዊ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በአንዳንድ ክልሎች በመመሪያው መሰረት ልዩ ፍላጎት ያላቸው ት/ቤቶችንና የተማሪዎችን ቁጥር በመለየት ባለድርሻዎችን በማሳተፍ ለተማሪዎቹ አስፈላጊ የትምህርት መሳሪዎች በመግዛት ተማሪዎቹ እንዲጠቀሙባቸው አድርገዋል። በሌላ በኩል አንዳንድ ክልሎችና ወረዳዎች ከመመሪያው ውጪ ለተማሪዎች ቀጥታ የኪስ ገንዘብ የሰጡበት ሁኔታ ታይቷል። በመሆኑም ውጤታማ በሆነ መልኩ ያከናወኑ ክልሎችና ወረዳዎችን ልምድ በመውሰድ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በ2009 በጀት ዓመት ለሁሉም ክልሎች ተጨማሪ 2% የት/ቤቶች ድጎማ በጀት እንዲመደብ ተደርጓል፡፡ 4. ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የተመደበውን የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት አጠቃቀምን በሚመለከት በየደረጃው መከናወን ያለባቸው ተግባራትና ሀላፊነቶች የክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶችና ት/ቤቶች ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የተመደበውን የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት አጠቃቀም በሚመለከት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነትና ተግባራት ተገንዝበው በጀቱን በመመሪያው መሰረት ተማሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያደርግ መልኩ ስራ ላይ እንዲውል ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ተግባራትና ሀላፊነቶቻቸው በሚከተለው መልኩ ቀርበዋል። 4.1 የክልል/ ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ተግባራትና ሀላፊነቶች • ከት/ቤት ጀምሮ እስከ ክልል ያሉ አካላት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ቁጥርና አይነት ለይተው...