ፕሮግራምና አጋርነት. ባለፉት አስራ አንድ ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- o የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በገንዘብ ሚኒስትር በተመደበለት የ2014 በጀት ዓመት አመታዊ በጀት ላይ በመንተራስ የአመታዊ ዕቅድ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህ አመታዊ ዕቅድ በየሩብ ዓመቱ የተከፋፈለ፣ የፋይናንስ ምንጩ የተለየ እንዲሁም ውጤት ተኮር እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። o በግማሽ ዓመቱ ላይ ኮሚሽኑ ሂደቱንና የሁኔታዎችን መለዋወጥ ግምት ውስጥ በማስገባት የ2014 ዓመታቂ እቅዱን በመከለስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለገንዘብ ሚኒስቴር አስገብቷል o በሶስተኛው ሩብ ዓመት የመጨረሻ ወር ላይ ደግሞ በ2013-2-15 አራተኛው ዙር የፕሮግራም በጀት ማእቀፍ መሰረት የ2015 በጀት ዓመት የኮሚሽኑን የፕሮግራም በጀት አዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለገንዘብ ሚኒስቴር አስገብቷል። የ10 ወር ሪፖርት ለተከበረው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቅርቡዋል፤ እንዲሁም ም/ቤቱ ባዘጋጀው የበጀት ስሚ (budget hearing) ላይ በመገኘት የኮሚሽኑን የ2015 የፕሮግራም በጀት ለበጀት፤ አቅርቦ ለተነሱለት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፤ o ሃብት ለማሰባሰብ በተደረገ ጥረት፡- o ለኢስት አፍሪካ ኦፕን ሶሳይቲ ፋዉንዴሽን 1 የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ የተላከ ሲሆን ይህም ፕሮፖዛል በድጋፈ ሰጪዉ ድርጅት ተቀባይነት አግኝቶ የ6,981,397.76 ብር ድጋፍ ተገኝቶበታል o ከዳኒሽ የሰብአዊ መብቶች ኢንስቲትዩት ጋር በተደረገው የአራት ዓመት የትብብር ስምምነት ተጨማሪ ድጋፍ ከኔዘርላንድ መንግስት EUR 200,000 ተገኝቷል። ለጀርመን ኢምባሲ በተላከ የፕሮጀከት ፕሮፖዛል መሰረት ኢምባሲዉ በዴኒሽ የሰብአዊ መብቶች ኢንስቲዉት በኩል ለሚደረገዉ ድጋፍ 1,500,000 ዩሮ ለሦስት ዓመት የሚሆን ድጋፍ ተገኝቷል። ተጨማሪ ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥረቶች ቀጥለዋል። o ከፍትሕ/ዩኤስኤድ የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው የተደረገው ጥረት ተሳክቶ ቀጣይ ድጋፍ ተገኝቷል፤ o ከተ.መ.ድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት (OHCHR) ጋር የሚሰራዉን የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙሪያ የሚደረገዉን ክትትል እና ምርመራ በጋራ ለመስራት የሚያሰችል ድጋፍ ከጽ/ቤቱ ተገኝቷል። ከዚህም በተጨማሪ በኮሚሽኑ በቀጥታ ለሚተገበሩ ስራዎች 60,000 የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል o በ2013 ዓ.ም. በ“The Governance and Democratic Participation Programme (GDPP)” ስር ለኮሚሽኑ የሚደረገው ድጋፍ እንዲቀጥል ተደርጓል፣ ከተ.መ.ድ. የሕጽናት ፈንድ (UNICEF) እና የሕጻናት አድን ድርጅት (Save the Children) ጋር የተደረጉ የድጋፍ ስምምነቶችን ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማድረግ ተችሏል o ኢሰመኮ ግማሽ ዓመቱ ሊገባደድ ሲል አስቀድመው አጋር የነበሩና ድጋፍ ለመስጠት ቃል ለገቡ ሁለት አጋር ድርጅቶች (አይርሽ ኤድና የተ.መ.ድ. የልማት ፕሮግራም (UNDP) ፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች በማዘጋጀት 350000 ዩሮ ድጋፍ ተገኝቷል። በተጨማሪም የተ.መ.ድ. የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) የፕሮጀክት ጽንሰ ሃሳብና በጀት ተዘጋጅቶ ስምምነት ላይ ተደርሷል። o ኢሰመኮ በየአመቱ የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የሲዊዘርላንድ ኢምባሲይ በጅግጀጋ ከተማ በ2015 ዓ.ም ለማክበረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎትና ተነሳሽነት በመግለጻቸው መንሻ ሃሳብ ፕሮፖዛል (Concept Note) ተዘጋጅቶ ተልኳል። በዚህም መሰረት ከሲዊዘርላንድ ኢምባሲ የ 1,875,000 ETB ብር ድጋፍ ተገኝቶል። o የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖረት አዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለገንዘብ ሚኒስቴር ልኳል። ሪፖርቱ የሚሸፍነው ወቅት ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከናወኑ ተግባራትን ነው። የአፈጻጸም ሪፖርቱ የኮሚሽኑን አመታዊ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ነው። የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖረት ጨምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ መንፈቅ ሪፖርት አጠናቅሮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለገንዘብ ሚኒስቴር ልኳል። የመንፈቀ ዓመቱ ሪፖርቱ የሚሸፍነው ወቅት ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከናወኑ ተግባራትን ነው፡፡ የመጀመሪያውን ግማሽ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖረት ጨምሮ የዓመቱን የዘጠኝ ወር ሪፖርት አጠናቅሮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና...