የስምምነቱ አፈጻጸም. የስምምነቱን አፈጻጸም በሚመለከት የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ለማስፈጸምና ተፈጻሚነታቸውን ለመከታተል ኃላፊነቱን የሚወስድ መንግስታዊ አካል መሰየም አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ አንፃር የስምምነቱ ይዘት በወንጀል ጉዳዮች ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠትን የሚመለከት በመሆኑ የወንጀል ጉዳዮች ትብብር አካል ነዉ። በዚህ ረገድ የፌዴራል አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1263 አንቀጽ 40(1) እና የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6 (12) ) መሠረት የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በወንጀል ና በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር እንዲያደርግ ኃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ እንዲሁም በስምምነቱ አንቀጽ 2 መሠረት የስምምነቱን አተገባበር ለመከታተል የፍትሕ ሚኒስቴር እንደ ማዕከላዊ ባለስልጣን የተሰየመ በመሆኑ ይህንን ስምምነት ለማስፈጸምና ተፈፃሚነቱን ለመከታተል የፍትሕ ሚኒስቴር ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
የስምምነቱ አፈጻጸም. የስምምነቱን አፈጻጸም በሚመለከት የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ለማስፈጸምና ተፈጻሚነታቸውን ለመከታተል ኃላፊነቱን የሚወስድ መንግስታዊ አካል መሰየም አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ አንፃር የስምምነቱ ይዘት በወንጀል ጉዳዮች የሚደረግ የጋራ ህግ ትብብርን የሚመለከት በመሆኑ የወንጀል ጉዳዮች ትብብር አካል ነዉ ። በዚህ ረገድ የፌዴራል አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1263 አንቀጽ 40(1) እና የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6 (12) ) መሠረት የኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በወንጀልና በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር እንዲያደርግ ኃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ እንዲሁም በስምምነቱ አንቀጽ 7 መሠረት የስምምነቱን አተገባበር ለመከታተል የፍትሕ ሚኒስቴር እንደ ማዕከላዊ ባለስልጣን የተሰየመ በመሆኑ ይህንን ስምምነት ለማስፈጸምና ተፈፃሚነቱን ለመከታተል ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡ ስምምነቱ በይዘት የትብብር ስምምነቱ ዓላማ፣የተፈፃሚነት ወሰን፣ ጥያቄዉ ማዕከላዊ ባለስልጣናት፣ የጋራ የህግ ትብብሩ ወሰን፣ የትብብር ጥያቄዉ ፎረም እና ይዘት፣ የትብብሩ አፈጻፀም፣ ጊዜያዊ እርምጃዎች፣ የትብብር ጥያቄዉ ውድቅ ሊደረግ ስለሚችልባቸዉ ሁኔታዎች፣ የተለያዩ የትብብር ዓይነቶች ስለሚስተናገዱባቸዉ ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዙ ሃያ ስምንት (28) አንቀጾች አሉት። በስምምነቱ አንቀጽ 1 የሰምምነቱ ዓላማ በወንጀል ጉዳዮች የጋራ ህግ ትብብር ዙሪያ የትብብር ማዕቀፍ መፍጠር ሲሆን በአንቀጽ 2 መሰረትም ሀገራቱ ሰፊ ሆነ ወንጀል ህግ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸዉ ተደንግገጓል፡፡ በአንቀጽ 3 መሰረት ሁለቱ ሀገራት በወንጀል ጉዳች የጋራ የፍትህ ትብብር ለማድረግ ግዴታ የገቡ ሲሆን የጋራ ትብብሩ ወሰንም • ተጠርጣሪን ቃል መቀበል፣ ምስክር ቃል መቀበል፤ • የፋይንንስ መረጃ እና ወንጀል ሪከርድን ጨምሮ ለምርመራ የሚያግዙ መረጃዎችንና ሰነዶችን መለዋወጥ፣ • በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን እና ዕቃዎችን ማፈላለግ እና መለየት፤ • መጥሪያ ማድረስን፣ • ሰዎችን ለምስክርነት እና ምርመራን እንዲያግዙ መጥራት • በእስር ላይ የሚገኝ ግለሰብን ለምስክርት ሲፈለግ ወይም ምርመራን እንዲያግዝ ማስተላለፍ፤ • የብርበራ እና የንብረት ማገድ ትዕዛዞችን ማስፈፀም፤ • የወንጀል ፍሬዎችን ማፈላለግ፣ መያዝ እና መዉረስ • የገንዘብ ቅጣቶችን፣ የካሳ ትዕዛዞችን ማስፈፀም፤ እና ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ ትብበሮችን የሚያካትት ሲሆን ስምምነቱ ወደስራ ከመግባቱ በፊት ለተፈጸሙ ወንጀሎችም ተፈጻሚነት አለዉ፡፡ በአንቀጽ 4 መሰረትም ስለ ሀገራቱ ህግ እና የፍትህ አሰራር በአጠቃላይ መረጃዎችን ሊለዋወጡ እንደሚችሉ ተደንግጓል፡፡ አንቀጽ 5 ስምምነቱ ተፈፃሚ ስለማይሆንባቸዉ ጉዳች ሚደነግግ ሲሆን ለአሳልፎ መስጠት የሚፈለግን ሰዉ ለማሰር፣ የተጠያቂ ሀገር ህግ ከሚፈቅደዉ ዉጭ ለሆነ በጠያቂ ሀገር የተወሰኑ ፍርዶችን ለማስፈፀም፣ እስረኛን ለማስተላለፍ እና ጅምር የወንጀል መዛግብትን ለማስተላለፍ ጉዳች ተፈፃሚነት የለዉም፡፡
የስምምነቱ አፈጻጸም. የስምምነቱን አፈጻጸም በሚመለከት የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ለማስፈጸምና ተፈጻሚነታቸውን ለመከታተል ኃላፊነቱን የሚወስድ መንግስታዊ አካል መሰየም አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ አንፃር የስምምነቱ ይዘት በወንጀል ጉዳዮች የሚደረግ የጋራ ህግ ትብብርን የሚመለከት በመሆኑ የወንጀል ጉዳዮች ትብብር አካል ነዉ ። በዚህ ረገድ የፌዴራል አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1263 አንቀጽ 40(1) እና የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6 (12) ) መሠረት