We use cookies on our site to analyze traffic, enhance your experience, and provide you with tailored content.

For more information visit our privacy policy.

መግቢያ የናሙና ክፍሎች

መግቢያ. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቱርክ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል እ.ኤ.አ. ሜይ 10 ቀን 2022 በወንጀል ጉዳይ የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት በአንካራ ተፈርሟል። በስምምነቱ መግቢያ ላይ ስምምነቱ ወንጀልን በመከላከል እና የወንጀል ስነ-ስርዓት ሂደትን በተመለከተ ዓለም አቀፍ አሰራርን መሰረት ያደረገ ዉጤታማ የሆነ የወንጀል መከላከል ትብብር ለማድረግ ታስቦ የተፈረመ ስምምነት መሆኑን ይገልፃል፡፡ ስለሆነም ስምምነቱ በወንጀል ጉዳይ የሚፈለጉ ተጠርጣሪ ወይም ፍርደኞችን አሳልፎ በመስጠት ረገድ ለሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር የሕግ ማዕቀፍን የሚፈጥር በመሆኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንዲጸድቅ ለማስቻል ይህ መግለጫ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
መግቢያ. ለስኬት የበቁ ተቋማት ለስኬታቸው መነሻ የሆኑትን አፈፃፀሞች በዝርዝር ለቅሞ ወደ ራስ በመውሰድ ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ተግባራዊ ማድረግ ከራስ ከሚገኘው ልምድና ተሞክሮ ባሻገር ያሉ ተሞክሮዎችን በማቀናጀት ስኬታማ ከሆኑ ተቋማት የተሻለ ውጤት ማምጣት የሚቻል መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሌላ የሚገኝን የተሻለና የተለየ ውጤታማ አፈፃፀምን በመቀመር ሌሎች እንዲጠቀሙ በማድረግ ውጤታማ ከሆኑበት የበለጠ ውጤትና ስኬትን ለማምጣት የሚያስችል መንገድ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ማለትም በእንስሳትና ዓሣ፣ በሆርቲካልቸር፣ በሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት እና በግብርና ውል (Contract Farm- ing) የተሰማሩ ኩባንያዎችን ስኬታማ የሆኑበትን አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎችንና ቴክኖሎጅዎችን ሌሎች ኩባንያዎች ተጠቅመው ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር በዘርፉ ለተሰማሩ ተሞክሮውን ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ውጤታማ የሆኑ ኩባንያዎችን አሠራር በመረጃ በመደገፍ፣ በመለየትና በመቀመር በሰነድ መልክ ተዘጋጀቶ ለሌሎች በማሰራጨት ለምርትና ምርታማነት እድገት ላቅ ያለ አስተዋ ጽኦ እንዲያበረክት የማድረግ ስራ በሚፈለገው መልኩ ስላልተሰራ ውጤታማ የሆኑ ኩባንያዎች በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች በመስክ በመገኘት መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመለየት፣ ያላቸ ውን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ለሌሎች ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በግብርና ኢንቨስትመንትና በግብርና ምርት ውል ዘርፍ ተሰማርተው ውጤታማነትንና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ በቢዝነስ ፕላንና በገቡት ውል መሰረት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ጥሩ አፈጻጸም ያስመዘገቡ እና ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ድርሻ ያበረከቱ ድርጅቶችን ለስኬት ያበቋቸውን ተግባራትና ሂደቶችን በዝርዝር በመልቀም ተመሳሳይ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሌሎች ኩባንያዎች ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ እንዲያደርጉት በማድረግ ኢንቨስትመንቱ የታለመለትን ዓላማ በማሳካት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና ስላለው ምርጥ ልምድ መቀመር ራሱን የቻለ አሰራርና ግንዛቤ የሚጠይቅ ስለሆነ ምርጥ ተሞክሮን ለመቀመር የሚያስችል ማብራሪያ የያዘ የአሰራር ስርዓት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የምርጥ ተሞክሮ የቅመራ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
መግቢያ. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌደራል ሕገ-መንግስቱ መሰረት ነጻ ፌደራላዊ የመንግስት አካል ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) የተቋቋመና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበርና እና ጥበቃ የሚሰራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ነው። ኮሚሽኑ የተጣለበትን ኃላፊነቶች በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት እና በ2012 ዓ.ም. ተጀምሮ በ2013 ዓ.ም. የቀጠለዉን የለውጥና የተቋም አቅም ግንባታ በተሟላ ፕሮግራም እንዲታገዝ የሚያደርግ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ቆይቷል። ለዚሁ ዕቅድ ማስተግበሪያ የ4ኛው ዙር የፕሮግራም በጀት (2013-2015) ማዕቀፍ ላይ ተመስርቶ በየዓመቱ የተሸነሸነ መርሃ-ግብር በማዘጋጀት የተልዕኮ ስምሪቱን እየመራ ይገኛል። በዚህም መሰረት የተሻሻለውን የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት በማድረግ ተቋማዊ የለውጥ ፕሮግራም፣ የአቅም ግንባታ ስራን እንዲሁም በኃላፊነት የተሰጠውን ተግባራት አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ሪፖርት ውስጥ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት አስራ አንድ ወራት (01 ሐምሌ 2013 ዓ.ም. እስከ 30 ግንቦት 2014 ዓ.ም.) ውስጥ የኮሚሽኑ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ ቀርቧል። ሪፖረቱ የተዋቀረው በዘጠኝ የፕሮግራም መስክ ነው። እነሱም፡-