ሚዲያና ኮሚኒኬሽን. በለፉት አስራ አንድ ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- የኮሚሽኑ አምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ በመጀመሪያ ዓመት አፈጻጸሙ ለተቋማዊ አቅም ግንባታ ትኩረት በመስጠት፣ ለዚሁም እንዲረዳ 17 የተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፎች ለይቷል። ከእነዚህም መካከል በተለይም የሚድያና ኮሙኒኬሽን ስራ ክፍሉን በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የሚመለከቱ ዘርፎች በማስፈጸም ረገድ የስራ ክፍሉ እስከ 2014 ዓ.ም. አስራ አንድ ወራት ማብቂያ ድረስ ያከናወናቸው ተግባራት እንደሚከተለው ጠቅለል ባለ መልኩ ሪፖርት ተደርገዋል። • ከመስከረም 1 ቀን እስከ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ብቻ ኮሙሽኑ 145 የተለያዩ የኮሙኒኬሽን ውጤቶችን (ማለትም ሪፖርቶች፣ መግለጫዎች፣ የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች መልዕክቶችንና ግንዛቤ ማስጨበጫ ይዘቶች የያዙ ቪድዮዎችና የጽሑፍ ሰነዶች ወዘተ) በኮሚሽኑ ድረ ገጽና ማኅበራዊ ሚድያ ተሰራጭተዋል፣ በተመሳሳይ መልኩ ከመስከረም 1 ቀን እስከ ነሃሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቋሙ 70 መሰል ሰነዶችን ያሰራጨ ከመሆኑ አኳያ የ2014 ዓ.ም. አፈጻጸም ቢያንስ በ100% እድገት ያሳየ ነው፣ • የኮሚሽኑ ድረ ገጽ በስራ ላይ ከዋለና ለሕዝብ ከተዋወቀ ጀምሮ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ ለምሳሌ በግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. የተደረገው የክትትል ሪፖርት እንደሚያሳየው የኮሚሽኑን ድረ ገጽ የሚጎበኙ ተጠቃሚዎች ከግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. አንጻር የ70% እድገት በማሳየት 8000 ደርሷል፣ የኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ተከታዮች ቁጥር ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም አንጻር በ55% በመጨመር 180,000 ገደማ የደረሰ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የኮሚሽኑ ትዊተር ገጽ 100 ሺህ ገደማ ደርሷል፣ በታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም. በነበሩት አራት ሳምንታት ውስጥ በፌስቡክ ገጽ ብቻ 160 ሺህ ሰዎችን መድረስ ተችሏል፣ • የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ውጤቶች የጥራት ደረጃ ከፍተኛ እንዲሆን የኮሙኒኬሽን ውጤቶች ሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ቅርጽና ሞዴል ተዘጋጅቶ ተፈጻሚ ሆኗል፣ ማንኛውም ረቂቅ ሰነድና ቪድዮ በሰፊ የአርትዖት ሂደት አሰራር እንዲያልፍ ይደረጋል፣ የዚህ የአርትዖት ሂደት ተዘርግቶና መመሪያ ተዘጋጅቶ በተለይም የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ተግባራዊ እንዲያደርጉት ተደርጓል፣ ሰነዶችና ሌሎች የኮሙኒኬሽን ውጤቶች በዚህ የአርትዖት እንዲያልፉ ማድረግና ይህንንም የአርትዖት ሂደት በአግባቡ መከታተል የስራ ክፍሉ ከሚያከናውናቸው ቋሚ ተግባራት መካከል ናቸው፣ ለተቋሙ የኮሙኒኬሽን ውጤቶች ከፍተኛነት አመላካችነት ሊወሰድ ከሚችሉ ነጥቦች መካከል የኮሚሽኑ ድረ ገጽና ማኅበራዊ ሚድያ ተከታዮች/ተጠቃሚዎችና ከሌሎች ተቋማት የሚሰጡት አስተያየቶች፣ ይዘቶች በአብዛኛው በመገናኛ ብዙኃንና በሌሎች ተቋማት ተጨማሪ ማሻሻያ ሳይስፈልጋቸው እንዳሉ የሚወጡ መሆናቸው፣ የኮሚሽኑ ሪፖርቶችና መግለጫዎች በሌሎች ተቋማት እንደ ተዓማኒ ምንጭ መጠቀሳቸውና በተለይም በማኅበራዊ ሚድያ የሚሰራጩ የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ውጤቶች በሌሎች በርካታ ተቋማት መጋራታቸው፣ ለምሳሌ በግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. በትዊተር የተሰራጨ አንድ ሰነድ አማካይ የስርጭት/የመጋራት ደረጃ ከ150 በላይ ነበር፣ • የተቋሙ ድረ ገጽና ማኅበራዊ ሚድያ ስርጭትና ተከታይ ቁጥር መብዛት ለሁሉም የኮሙሽኑ የስራ ክፍሎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ይፋ የሚደረጉ ሰነዶችና የኮሙኒኬሽን ውጤቶች በአጠቃላይ የሰብአዊ መብቶችን ግንዛቤ በማስፋትና ሀገራዊው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከማድረግ አኳያ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው፣ ስለሆነም በተለይ የማኅበራዊ ሚድያው ቴክኖሎጂና መድረክ በሚሻሻልበት ፍጥነትና በየጊዜው የሚደረጉ ማሻሻያዎችን ለመከታተልና እኩል ለመራመድ ቋሚ የክትትል ስራ ይሰራል፣ አዲስ መድረኮችን ለመቀላቀል በሚያስፈልግበት ግዜ ዳሰሳ ተደርጎ በከፍተኛ አመራር እንዲጸድቅ ይደረጋል፣ በዚህም መሰረት ለምሳሌ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. ኮሚሽኑ የመጀመሪያውን የዩትዩብ ቻናል በመፍጠር ተግባራዊ አድርጎ ወደ አዳዲስ የማኅበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለመሆን ችሏል፣ 1.1 የተሻሻለ የሰብአዊ መብት መረጃ፣ ቁሳቁስ /ማቴሪያል/ እና አገልግሎት ማግኘት o የብራንዲንግ ስትራቴጂ ያካተተ ረቂቅ የኮሙኒኬሽን (ግንኙነት) ስትራቴጂ ተዘጋጅቷል፣ በ3ኛው ሩብ ዓመት ለኮሚሽነሮች ጉባዔ ቀርቦ ይጸድቃል፣ የኮሚሽኑ ድረገጽ (xxx.xxxx.xxx) በስራ ላይ ከዋለ 17 ወራት አስቆጥሯል፣ በዚህ ሩብ ዓመት በይዘትና በቅርጽ የማሻሻል ስራ ተሰርቷል፣ አስተዳደሩም ያለምንም ተግዳሮት እየተከናወ...