ማጠቃለያ የናሙና ክፍሎች

ማጠቃለያ. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በተርክየ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብርን አስመልክቶ የተደረገው ስምምነት ቱርክ እና ኢትዮጵያ ያላቸዉ ግንኙነት ለረጅም ጊዜ የነበረ እና በተለይም ደግሞ በአሁኑ ሰዓትም ዘርፈ ብዙ እና ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ በመምጣቱ በተለይም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸዉ ግንኙነት እየጨመረ የመጣ በመሆኑ እና በዚህም ምክንያት ኢትጵያውያን በቀላሉ ወደ ቱርክ መጓዝ መቻላቸው የወንጀል ክስ፣ ምርመራ እና ክስ ሂደት የሚስፈልጉ መረጃ እና ማስረጃዎች እንዲሁም ለወንጀል መፈፀሚያነት የዋሉ፣ ሊዉሉ የታሰቡ ወይም የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶች ሊሸሹ የሚችሉበት ዕድል ከፍተኛ ነዉ፡፡ በመሆኑም እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ለሚደረጉ ትብብሮች በሕግ ማዕቀፍ ምላሽ ለማስጠት ስምምነቱ አስፈላጊ ነዉ። ከዚህ አንጻር በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንዲጸድቅ ረቂቅ አዋጁን አያይዘን አቅርበናል።
ማጠቃለያ. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በተርክየ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በወንጀል ጉዳይ ግለሰቦችን አሳልፎ መስጠትን አስመልክቶ የተደረገው ስምምነት በሁለቱ አገሮች ሰላምን፣ ፀጥታን እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የትብብር