ክፍል አንድ የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት. የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት ማለት “የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥርን 1180/2012 መስፈርት አሟልቶ በአገር ውስጥ ባለሀብት( Domestic Investor )፣ በውጭ ባለሀብት (Foreign In- vestor) ወይንም በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብት ጥምረት (Jointvencher) በወተት ከብት እርባታና ወተት ምርት፣ በዳልጋ ከብት ማድለብ፣ በእንቁላልና የስጋ ዶሮ እርባታ፣ በበግና ፍየል እርባታ/ማድለብ፣ በዓሳ እርባታ፣ በዘመናዊ ንብ ማነብ፣ በእንስሳት መኖ ማምርትና ማቀነባበር እንዲሁም በሌሎች ንዑስ ዘርፎች የሚደረግ የኢንቨስትመንት መስክ ሲሆን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመር/ለማወዳደር የሚያስችል የሚከተሉትን የምዘና (የመመልመያ) መስፈርቶችና ነጥቦች የያዘ ይሆናል፡፡