ዓላማ የናሙና ክፍሎች
ዓላማ. ይህ ክፍል በተሻሻለው (በ 42 U.S.C. 14043e እና ተከታዮቹ ላይ እንደተሻሻለው) (VAWA) በ1994 የሴቶች ጥቃት ህግ ንዑስ ርዕስ N መሰረት እንዲሁም የ24 CFR ክፍል 5፣ ንዑስ ክፍል Lን በመተግበር የቤት ውስጥ ጥቃት፣ የፍቅር ጓደኝነት፣ ጾታዊ ጥቃት ወይም ማሳደድ ሰለባ ለሆኑት ጥበቃዎችን ያካትታል።
ዓላማ. የስብሰባው ተሳታፊዎች ትክክለኛ የሆነ የስብሰባ ቃለጉባኤ ጠቀሜታ፣ የቃለጉባኤ አያያዝ ሂደት እና የሰብሰባ ቃለ ጉባኤ ይዘት ያውቃሉ፡፡
ዓላማ. በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች የቢሮ እና ቅጥር ሰራተኞች አንዲሁም የማኅበሩን ሀብት አመራር በሚመለከት የሰልጣኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ፣
ዓላማ. የስልጠናው ተሳታፊዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አስተዳደር፣ በአሰራር እና ጥገና አመራር እንዲሁም በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት እና በመስኖ ኅብረት ሥራ ማኅበራት መካከል ያለውን ልዩነት ለማስገንዘብ ነው፡፡ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ምንነት፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ኃላፊነት እና ተያያዥ ተግባራት፣ እና • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የህግ ማዕቀፍ፣ ስልልጠናው የሚያካትታቸው፡- የሚመለከታቸው አጋር አካላት ባለሙያዎች፣ የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፐ ቻርት፣ ማኑዋል እና የክፍል/የቡድን ሥራ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራትን ለማቋቋምና ለማስተዳደር የወጣው አዋጅ ቁጥር 239/2008፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራትን ለማቋቋም እና የመስኖና ድሬኔጅ አውታርን ለመስራትና ለመጠገን /Operation & maintenance/ የሚያስችል የተለየ የሕግ መሰረት ተጥሏል፡፡ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበረው የሕግ ማዕቀፍ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበርን በሕጋዊ መንገድ ለማቋቋም የሚያስችል አልነበረም፡፡ በዚህም መሰረት፡- • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት በመንግስት አዋጅ የሚቋቋሙና ኃላፊነታቸውም ከመንግስት ፍላጎት ጋር የሚሄድ መሆኑ፣ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት አባልነት ግዴታ መሆኑ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት አትራፊ ባልሆኑ ተግበራት ወይም ንግድ ነክ ባልሆኑ ተግበራት ላይ የተሰማሩ ቢሆንም ለአባሎቻቸው ከሚሰጡት አገልግሎት ለምሳሌ የመስኖ ውኃ አገልግሎት ክፍያ ያሰባስባሉ፡፡ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩና በአባላት የሚመሩ ራስገዝ ድርጅቶች ቢሆኑም ተግባሮቻቸውን ሲያከናውኑ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በተወሰነ መልኩ የመንግስት ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ መንግስት በሚያወጣው አዋጅ የሚቋቋሙ ድርጅቶች ኃላፊነት ባህሪ የመንግስትን ትኩረትም ጭምር የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ኃለፊነት ለግብርና ስራ የሚውል የመስኖ ውሃ ለአበሎቻቸው መስጠት ነው፡፡ ይህ ተግባር በባህሪው የመንግስት ትኩረትም አለበት፡፡ ምክንያቱም፣ 1) የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት የመስኖ ውሃ የሚሰጡት ከፍተኛ ቁጥር ላለው ህዝብ/ማህበረሰብ በመሆኑ እና፣ 2) ማኅበራቱ በአብዛኛው በመንግስት ድጋፍ በተገነቡ የመስኖ አውታሮች የሚጠቀሙ በመሆኑ፤ ማለትም መሰረተ ልማቱ በመንግስት የተገነባና ባለቤትነቱም የመንግስት በመሆኑ መንግስት ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ የመንግስት አዋጆች ከህ-ገመንግስቱ የሚቀዱ ናቸው፡፡ የመንግስት አካላት ማለትም የማዕከላዊ መንግስት፣ የክልል እንዲሁም የተለየ የመንግስት ተግባር የሚያከናውኑ ተቋማት ለምሳሌ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሆስፒታሎች ወዘተ…. አሰራራቸውን የሚወስኑ የተለዩ አዋጆች ይዘጋጁላቸዋል፡፡ ስለሆነም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት በመንግስትና በግል ሴክተሩ መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡ ማኅበራቱ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ፣ የራሳቸውን የአገልግሎት ተመን የማውጣት፣ ውሳኔዎችን የመወሰን እንዲሁም የአሰራር ህጎችን ማውጣት ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳ በተለያዩ አካላት ድጋፍ ጭምር እንደሚቋቋሙ ቢታመንም፤ በህጋዊ መንገድ የራሳቸውን ፋይናንስ የሚያንቀሳቅሱና አብዛኛው የገቢ ምንጫቸው ደግሞ ከአባላት የሚገኝ ነው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት በመንግስት አዋጅ የተቋቋሙ እንደመሆናቸው መጠን ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ጉዳይ፤ የመክፈያ ጊዜው የደረሰ ክፍያ ለማስከፈል ከአቅማቸው በላይ በሚሆንበትና ብዙ ጊዜንና ወጭን የሚጠይቅ ሲሆን እንደሌሎች በህግ የተቋቋሙ ተቋማት ለምሳሌ እንደ ኅብረት ሥራ ማኅበራት የመንግሰትን ድጋፍ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት የተሰጣቸው ኃለፊነት የመስኖ ድሬኔጅ አውታርን በመምራት፣ በመጠቀም እና በመጠገን እንዲሁም ተፋሰሱን በመጠበቅና በመንከባከብ ላይ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ሌሎች ተግባራትን ለምሳሌ የግብርና ግብዓት ግብይት፣ በመስኖ አውታሩ የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን ግብይት ማካሄድ አይፈቀድላቸውም፡፡ እነዚህ ተግባራት ባህሪያቸው በግል የሚከናወኑ ናቸው፡፡ የግብርና ግብዓቶችንም ሆነ የግብርና ምረቶችን እንዴት እንደሚገበይ ወሳኙ ራሱ አርሶ አደሩ ነው፡፡ ይህ ምን አልባት አርሶ አደሩ በግሉ ወይም በጋራ በመሆን በግይት ኅብረት ሥራ ማኅበራት /ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ከአንድ በላይ በሆኑ ኅብረት ሥራ ማኅበራት/ ግብይቱን ሊያካሂድ ይችላል፡፡ የመስኖ ውሃ አቅርቦት ልዩ የሚያደርገው፤ በአንድ የመስኖ አውታር አንድ የመስኖ ውሃ ተጠ...
ዓላማ. በማኅበሩ የውስጥ የግጭት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮችን ለመከላከል እንዲቻል እና ማኅበሩ ጤናማ ስራ እንዲሰራ ለማድረግ አስፈላጊውን የቅጣት እርምጃዎች በሚያካትት መልኩ በውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀትና ተግባረዊ ማድረግ ስላለው ጠቀሜታ የሰልጣኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ ነው፣
ዓላማ a. ይህ በPHA እና በባለቤቱ መካከል የተደረገ የHAP ውል ነው። የHAP ውል የተገባው በአንቀጽ 8 ቫውቸር ፕሮግራም ለቤተሰብ ድጋፍ ለመስጠት ነው (የHUD ፕሮግራም ደንቦችን በ24 የፌደራል ደንቦች ህግ ክፍል 982 ይመልከቱ)።
b. የHAP ውል ተግባራዊ የሚሆነው በHAP ውል ክፍል ሀ ላይ ለተጠቀሰው ቤተሰብ እና የውል ክፍል ብቻ ነው።
c. በHAP የውል ጊዜ፣ PHA በHAP ውል መሠረት ለባለቤቱ የቤት ድጋፍ ክፍያዎችን ይከፍላል።
d. ቤተሰቡ በአንቀጽ 8 ቫውቸር ፕሮግራም ስር በመታገዝ በውሉ ክፍል ውስጥ ይኖራሉ። በPHA የሚከፈለው የመኖሪያ ቤት ድጋፍ ክፍያ ተከራይ የውል ክፍሉን ከባለቤቱ ለቤተሰቡ መኖሪያነት እንዲከራይ ይረዳል።
ዓላማ. በ ESMS ላይ መደበኛ ኦዲቶችን የማካሄድ ዓላማ የ CFM’s ESMS እና የE&S ማስተማመኛዎችን፣ የሕግ ነክና ሌሎች አስፈላጊ ሁኔታዎች (የ IFC አፈጻጸም መለኪያዎችን ጨምሮ)፣ እና በባለሐብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያስቀምጧቸውን ውስን መስፈርቶች ጨምሮ አግባብነት ባላቸው መለኪያዎች መሰረት የ E&S ስጋቶች አስተዳደር ውጤታማ አደረጃጀቶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ውጤቶቹ ለኢንቨስትመንት ኮሚቴና ለቦርዱ እና ለባለድርሻ አካላቱ በመላው ቢዝነስ ውስጥ የ E&S ስጋቶች በአግባቡና ወጥነት ባለው ደረጃ ስለመያዛቸው ማረጋገጫ ለመስጠት ይውላሉ፡፡
ዓላማ. በግብርና ኢንቨስትመንት እና በግብርና ምርት ውል (Contract Farming) ዘርፍ የተሰማሩና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ኩባንያዎችን በመለየትና በማወዳደር፣ ምርጥ ልምዳቸውን በአግባቡ በመቀመርና ለሌሎች ተጠቃሚዎች እንዲደርስ በማድርግ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳው ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ነው፡፡