የሴቶችና የሕፃናትመብቶች. ባለፉት አስራ አንድ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት/ ክንውኖች፡- አብይ ተግባር1፤በሴቶችና ሕፃናት መብቶች ክፍተቶች ዙሪያ ጥናት ግፊት በማድረግ ውጤታማ የሆኑ መፍትሄዎች ላይ የጉትጎታና የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት • ኢሰመኮ በሕግና አፈጻጸም ላይ ያሉ የሕፃናት መብቶች አጠባበቅና አተገባበር ረገድ ክፍተቶችን ከዓለም አቀፍና አህጉራዊ መስፈርት አንጻር ለመዳሰስ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ ደረጃ በደረጃ ጥናት ሲያካሄድ ቆይቷል። በዚህም መሰረት በተያዘው የበጀት ዓመት መረጃና ተጨማሪ ግብዓት ለመሰብሰብ ከባለድርሻ አካላት ጋር ከተካሄደው አጠቃላይ ውይይትና የተሞክሮ ልውውጥ መድረክ እንዲሁም ከቃለ-መጠይቅ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ጥናት ቀርቦ በስራ ክፍሉ ግብዓት ተሰጥቶበት ረቂቁን የማዳበር ስራ ተከናውኗል። • የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ጥናቱ በተለያዩ ባለሞያዎች ግብአት ተሰጥቶበትና ተገቢው ክለሳ ተደርጎበት የሰነዱን ዝግጅት ለማጠናቀቅ በተያዘው እቅድ መሰረት በጥናቱ በመጀመሪያው ዙር የሕፃናት የማንነት መብት፣ የሕፃናት ጥበቃ እና በሕፃናት ላይ የሚደረስ ጥቃት፣ ቤተሰብ ሁኔታ እና አማራጭ እንክብካቤ እና ወንጀል ውስጥ የገቡ ሕፃናት መብቶችን የሚመለከቱ ሕጎች፣ ፓሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች መሰረት በማድረግ ያሉትን ክፍተቶች አስመልክቶ ጥናቱን ለማዳበርና ግብዓት ለማሰባሰብ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ዘርፈ ብዙ ከሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ አዱላላ ሪዞርት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና የኮሚሽኑ ፅ/ቤት ባለሙያዎችና ሀላፊዎች 19 ወንድና 15 ሴት በአጠቃላይ 34 ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩም ጥናቱን ለማዳበር የሚያስችሉ ግብዓቶች ለማሰባሰብ ተችሏል ። • በተጨማሪም በመጀመሪያው ደረጃ ያልተካተቱ የሕፃናት መብቶች ዘርፎችን ለማካተት የሁለተኛ ዙር የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ግልፅ ጨረታ ወጥቶ ተጫራቾች የመለየት ስራ እየተሰራ ይገኛል። • በሶማሌ ክልል ረቂቅ የቤተሰብ ሕጉ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት እንዲሁም በሁሉም የክልሉ ባለድርሻ አካላት እየተሠሰሩ ያሉትን ስራዎች ለማየት እና ወደፊት በሚሰሩ ስራዎች ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከባለድርሻ አካላት ጋራ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሴቶች ማኅበራት በአጠቃላይ 21 (12 ወንዶች 9 ሴቶች) ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ወደፊት በሚሰሩ ስራዎች ላይ በተለይም በባለድርሻ አካላት መካከል ቅንጅት እንዲፈጠርና ስራውን በባለቤትነት የሚመራ አካል እንዲሮር ለማስቻል የክትትል ኮሚቴ እንዲቋቋም ምክረ ሐሳብ ተሰጥቷል። በምክረ ሐሳቡ መሰረት ከክልሉ ፍትሕ ቢሮ ጋር ውይይቶች ተደርገው ቀጣይ ሂደቶችን ለመከታተል ጥረት ተደርጓል፡፡ የተደረጉ ጥረቶች ውስንነታቸውን በመገንዘብ በተጨማሪም በ2014 ዓ.ም ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ረቂቅ የቤተሰብ ሕጉ ዙሪያ ያከናወናቸውን ሥራዎችና ቀጣይ መደረግ ባለባቸው ረቂቅ ፅሁፍ ተዘጋጅቷል። አብይ ተግባር 2፡ ባለግዴታዎች የሴቶችና ሕፃናት መብቶችን እንዲያከብሩ እና እንዲያስጠብቁ የተሻለ ግንዛቤ ማስጨበጥ • በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት የጉልበት ብዝበዛን ጨምሮ በሴቶችና በሕፃናት ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሚመለከት ያለውን ክፍተትና ተገቢውን የግንዛቤና የጉትጎታ ስራ ለመለየት ከባለድርሻ አካላት ተጨማሪ ሰነዶችን በመሰብሰብ የወፍ በረር ምልከታ ለማካሄድ ተሞክሯል። በዚህም መሰረት የሕገ- ወጥ የሰዎች ዝውውርና ፍልሰትን ለመቆጣጠር በአዋጅ ቁጥር 1178/2020 በተቋቋመው ከተቋቋመው ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ምክር-ቤት ጋር በመቀናጀት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ክፍተቶችንና አስፈላጊ እርምጃዎችን ከሴቶች አና ከሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንፃር ለመቃኘት የምክክር መድረክ ለማካሄድ በተነደፈው ዕቅድ መሰረት ከጥምረት ም/ቤቱ ጽኅፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚመለከታቸውን የባለድርሻ አካላትን 17 ወንድና 4 ሴት በአጠቃላይ 21 ተሳታፊዎች በማሳተፍ የምክክር መድረክ ተካሂዷል ። በመድረኩ ሕገ- ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ማሻገርን በተመለከተ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔና በአፈፃፀም ረገድ እያጋጠሙ ያሉ ወቅታዊ ችግሮችን የሚዳስሱ ፁሁፎች ቀርበዋል፡፡ በዚህም መሰረት ሕገ- ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር ያጋጠሙየአፈፃፀም ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመከላከልና ምላ...