የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ አቀራረብ የናሙና ክፍሎች

የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ አቀራረብ. 5 8. የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ቅመራ ስልትና የሚከናወኑ ተግባራት 5 9. የምዘና መስፈርቶች 6 9.1 ክፍል አንድ የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት 6 9.2 ክፍል ሁለት የግብርና ምርት ውል (Contract Farming) 13 9.3 ክፍል ሶስት የሆርቲካልቸር ልማት 24 9.4 ክፍል አራት የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት 29 10. የሚወሰዱ እርምጃዎች 38 11. የአፈጻጸም አቅጣጫ 40 12. ማጠቃለያ 40 1.
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ አቀራረብ. ምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ተቀምሮ የሚቀርብባቸው በርካታ መንገዶች በኖሩም፤ በዋነኛነት ሁለት ዓይነት መንገዶች በሰፊው ይተገበራሉ። እነዚህም፡- 1. በትረካ (Case Study)፡- አንድን ወሳኝ ውጤት የተገኝበትን ዝርዝር ሁኔታ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ በትረካ መንገድ በማስቀመጥ ተሞክሮውን ለሌሎች የምናካፍልበት አቀራረብ ነው። 2. በሥዕል (በፎቶ ግራፍ እና በቪዲዮና ድምፅ)፡- አንድን ወሳኝ ውጤት የተገኝበትን ዝርዝር ሁኔታ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ በፎቶገራፍና በምስል ቀረጻ በማስደገፍ ተሞክሮውን ለሌሎች የምናካፍልበት አቀራረብ ነው። ምርጥ ተሞክሮ/ልምድ አንድ ወሳኝ ውጤት የተገኘበትን ሁኔታ በትረካ መንገድ በቅደም ተከተል አስቀምጦ ሌሎች ምርጥ ልምዱን ወስደው ተግባራዊ ለሚያደርጉ በፎቶግራፍና በቪዲዮ አስደግፎ ማቅረቡ የበለጠ ለመረዳት አመቺ ሊሆን ስለሚችል ሁለቱንም አዋህዶ መጠቀሙ የተሻለ ይሆናል፡፡ 8. የምርጥ ተሞክሮ/ልምድ ቅመራ ስልትና የሚከናወኑ ተግባራት የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ሲካሄድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦችን ያካተተ አካሄድ መከተል ውጤታማ ያደርጋል፡- ⇒ ዘርፉን በሚደግፈው ክፍል አስተባባሪነት በግብርና ሚኒስቴር ስር ከሚገኙ የስራ ክፍሎችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ማዋቀር፤ ⇒ በየደረጀው ምርጥ ልምዶችን አስመልክቶ የተዘጋጁ (የተቀመሩ) ሰነዶችን መመልከት እና የምርጥ ተሞክሮ ልምድ አዘገጃጀት የድርጊት መርሃ-ግብር ማዘጋጀት፤ ⇒ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ከዘርፉ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ስለ ስራው አላማና አፈፃፀም በመወያየት የጋራ ማድረግ፡፡ ⇒ ለምርጥ ተሞክሮ ቅመራ የተለዩ ኩባንያዎች ጋር በመወያየት በሚሰሩ ስራዎች ላይ መግባባት መፍጠር፣ ⇒ የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ሟሟላት፣ ⇒ ምርጥ ልምድ የሚገኝባቸውን ኩባንያዎች፣ ሰራተኞች እና የኩባንያዎች ወኪሎችን በማነጋገር ውጤቱ የተገኘበትን ዝርዝር ሂደት መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል ቸክ- ሊስቶችን ማዘጋጀትና ማፀደቅ እንድሁም የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በቸክ-ሊስቱ በዝርዝር ማስቀመጥ፤ 9.